በተገቢው ጊዜ የሚቀርብ ምግብ
በጥር የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በማስታወቂያ እንደተነገረው የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር በአብዛኞቹ ጉባኤዎች ሚያዝያ 10 ቀን ይሰጣል። የንግግሩ ርዕስ “እውነተኛው ሃይማኖት ለሰብአዊው ኅብረተሰብ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ያሟላል” የሚል ነው። በመጋቢት 26 በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙትን ሰዎች ለመጋበዝ ልዩ ጥረት ሊደረግ ይገባል።