የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/94 ገጽ 2
  • የሰኔ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሰኔ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሰኔ 6 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 13 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 20 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 27 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 6/94 ገጽ 2

የሰኔ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ሰኔ 6 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 215

10 ደቂቃ: የጉባኤው ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በመጪው ቅዳሜና እሁድ በምናደርገው አገልግሎት የሚበረከቱ ጽሑፎችን እንዲወስዱ አድማጮችን አሳስብ።

20 ደቂቃ፦ “በበረከት እየዘራህ ነውን?” ጥያቄና መልስ። ጊዜ ካለህ አገልግሎታቸውን በተመለከተ ተጨማሪ ጥረት በማድረጋቸው ምን በረከት እንዳገኙ ተሞክሯቸውን እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።

15 ደቂቃ፦ “ትርጉም ያለው የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንቀጽ 3⁠ን በምትወያዩበት ጊዜ በመጪው ቅዳሜና እሁድ ለአገልግሎት የምንጠቀምባቸውን አንድ ወይም ሁለት መግቢያዎች ምክንያቱን ማስረዳት ከተባለው መጽሐፍ ጥቀስ። አንቀጽ 5⁠ን በምትወያዩበት ጊዜ በመስክ አገልግሎት ላይ በአካባቢው የታየ ችግር ካለ ጥቀስ። ችግሩ ስለሚቃለልበት ሁኔታ በደግነት ምክር ስጥ።

መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 155

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ የተላከለት መዋጮ የደረሰው መሆኑን ገልጾ ከሆነ ጨምረህ አቅርብ። ለጋስ ሰው እንዴት በረከት እንደሚያገኝ የሚገልጽ አጠር ያለ ሐሳብ አክል። — ምሳሌ 11:24 የ1980 ትርጉም

15 ደቂቃ፦ “በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ያለውን ስሜት ቀስቃሽ መልእክት አውጅ።” (የመጋቢት 1994 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4⁠ን ተመልከት።) ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። ጥሩ ዝግጅት ያደረጉ አስፋፊዎች ከአንቀጽ 2–4 ላይ ያሉትን አቀራረቦች በትዕይንት እንዲያሳዩ አድርግ። ከእያንዳንዱ ትዕይንት በኋላ አድማጮች ከአቀራረቡ ስላገኙት ትምህርት ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። በዚህ ወር ሁሉም የራእይ መደምደሚያ የተባለውን መጽሐፍ እንዲያበረክቱ አበረታታቸው።

20 ደቂቃ፦ “የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት ለትምህርት መስጫ እንቅስቃሴዎች ድጋፍ ይሰጣል።” የመጽሐፍ ጥናት መሪ የሆነ አንድ ወንድም ከአድማጮች ጋር በመወያየት ያቀርበዋል። ትምህርቱ (1) በመጽሐፍ ጥናት ጊዜ የተሰብሰቢዎች ቁጥር እንዴት ከፍ ማለት እንደሚችል፣ (2) በጥናቱ ወቅት ብዙ ሰዎች ሐሳብ መስጠት የሚችሉበትንና (3) ለመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ የተሻለ ድጋፍ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ እንዴት እንደሚያበረታታ ጎላ አድርግህ ጥቀስ።

መዝሙር 136 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።

10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። አለዚያም በግንቦት 8, 1989 ከወጣው የእንግሊዝኛ ንቁ! መጽሔት በገጽ 12–14 ላይ “ምን ዓይነት ቋሚ ሥራ መምረጥ ይኖርብኛል?” በሚለው ርዕስ ላይ ንግግር አቅርብ።

10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት። በተጨማሪም በዚህኛው የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ “ማስታወቂያዎች” በሚለው ሥር ያለውን የመጨረሻ ማስታወቂያ ጥቀስ።

15 ደቂቃ፦“የአምላክን ፈቃድ እያደረግህ ነውን?” በመጋቢት 1, 1994 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28–30 ባሉት ሐሳቦች ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 174

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። በመጪው ቅዳሜና እሁድ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት በቅርቡ የወጡ መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል አጠር ባለ ትዕይንት አሳይ።

20 ደቂቃ፦ “ወጣትነትህ ” የተባለውን መጽሐፍ ልንጠቀምበት የምንችለው እንዴት ነው? ይህን መጽሐፍ ሀ) በ16 ዓመት አካባቢ ለሚገኝ አንድ ወጣት ለ) በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ልጆች ላሉት አንድ ወላጅ እንዴት ማበረከት እንደሚቻል የሚያሳዩ አጠር ያሉ ትዕይንቶችን አቅርብ። ከዚያም አንዲት እናት አለባበስንና የሰውነት አያያዝን በተመለከተ በገጽ 50–53 አንቀጽ 1–7 ላይ በቀረቡት ሐሳቦች በአሥራዎቹ ዕድሜ መጀመሪያ ላይ (11–14 ዓመት) የሚገኙ ሁለት ሴቶች ልጆቿን ለአሥር ደቂቃ ያህል ስታወያያቸው የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ። ትዕይንቶቹን የወጣቶችን ልብ በሚነካ፣ ሕያው በሆነና ሊያጋጥም በሚችል መንገድ ለማቅረብ ጥረት አድርግ። ሁሉም ይህን አስደሳች መጽሐፍ በደንብ እንዲጠቀሙበት አበረታታ።

15 ደቂቃ፦ በሐምሌ ወር ስለሚበረከቱ ጽሑፎች ማብራሪያ ስጥ።

መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ