የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/94 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 6/94 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ሰኔ፦ በማስታወቂያ ይነገራል። ሐምሌ፦ በጉባኤ ወይም በግል የሚገኙ ቀለሙ እየደበዘዘ ወይም እየለቀቀ በሚሄድ ወረቀት የታተሙ የቆዩ መጻሕፍት። እንደ ታላቁ አስተማሪ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚገኙትን ዘላለማዊ ዓላማ፣ ሕይወት ይህ ብቻ ነውን?፣ መንፈስ ቅዱስ፣ የሰው ልጅ መዳንና የሺህ ዓመት ግዛት የሚሉትን መጻሕፍት በ1 ብር ማበርከት ይቻላል። የየጉባኤዎቹ ጸሐፊዎች በአስፋፊዎች ወይም በአቅኚዎች ለተወሰዱት መጻሕፍት S-20-AM በተባለው ቅጽ ላይ የዋጋው ልዩነት እንዲቀነስላቸው መጠየቁን መዘንጋት የለባቸውም። በተጨማሪም አረንጓዴ ቀለም ያለው የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም በ5 ብር ሊበረከት ይችላል። ነሐሴ፦ ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማናቸውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ እነሆ፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊ ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች። መስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ማሳሰቢያ:- ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ጊዜ በሚልኩት ወርኃዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S-14-AM) ላይ ማዘዝ ይችላሉ።

◼ መሪ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው ሰኔ 1 ወይም ከዚያ ብዙ ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።

◼ በጣሊያን አገር በዓመት አራት ጊዜ የሚታተመው የአማርኛ ንቁ! መጽሔት ዋጋ እንደ መጠበቂያ ግንብ 1 ብር ነው። እያንዳንዱ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጠበቂያ ግንብ ትእዛዙ ልክ የንቁ! መጽሔት ይላክለታል። እንዲላክላችሁ የምትፈልጉት ብዛት እንዲለወጥላችሁ ከፈለጋችሁ የሚበረከት መጽሔት በምታዙበት ቅጽ (M-AB-202-AM) ላይ ሞልታችሁ ላኩልን። በዓመት አራት ጊዜ የሚታተመውን የአማርኛ ንቁ! መጽሔት ኮንትራት ለማስገባት የሚያስችል ዝግጅት የለም።

◼ በአዲስ አበባ ለሚደረገው “አምላካዊ ፍርሃት” የወረዳ ስብሰባ የወጣ ጊዜያዊ ፕሮግራም:- ጥቅምት 21–23, 1994

◼ አዲስ የመጡ ጽሑፎች:-

በእንግሊዝኛ፦ የ1994 የዓመት መጽሐፍ፣ የ1993 የመጠበቂያ ግንብ ጥራዝ፣ የ1993 ንቁ! ጥራዝ።

በአማርኛ፦ አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት፣ ወጣትነትህን ከሁሉ በተሻለ መንገድ ተጠቀ ምበት።

◼ አስፋፊዎች የሆናችሁ ሁሉ ወደ መስክ አገልግሎት ስትሄዱ መታወቂያ ካርዳችሁን መያዙ ጥበብ መሆኑን ልናስታውሳችሁ እንፈልጋለን። “ደም አልወስድም” የሚለውንም ካርድ መያዝ እንዳለብን ግልጽ ነው። ተቃዋሚዎች ሲያጋጥሙን በ2 ጢሞቴዎስ 2:24, 25፤ በምሳሌ 15:1፤ እና በምሳሌ 17:14 ያለውን ምክር መከተሉ ጥሩ ነው። እስራት ወይም ሌላ ከበድ ያለ ችግር ካጋጠማችሁ በሽማግሌዎቻችሁ በኩል ሪፖርት ሊደርግልን ይገባል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ