ማስታወቂያዎች
◼ የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በኅዳር፦ ወጣትነትህ። በታኅሣሥ፦ ራእይ መደምደሚያው። በጥር፦ ጉባኤው ያለው ማንኛውም ከ1982 በፊት የታተመ መጽሐፍ። በየካቲት፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ይህ መጽሐፍ ከተበረከተ በኋላ ተመላልሶ መጠየቅ ሊደረግ ይገባል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመርም ጥረት መደረግ አለበት። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን የዘመቻ ጽሑፎች እስከ አሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (s(d)–14–AM) መጠየቅ አለባቸው። ከላይ የተጠቀሱት ከ1982 በፊት የታተሙ ጽሑፎች በብሩክሊን አይገኙም።