የኅዳር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ኅዳር 7 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎችና በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከወጡት ማስታወቂያዎች ውስጥ ተስማሚዎቹን አቅርብ። በቅርብ ጊዜ ውስጥ የወጡትን መጽሔቶች ስናበረክት ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን አንድ ወይም ሁለት መነጋገሪያ ነጥቦችን ጥቀስ። ሽፋኑ አረንጓዴ የሆነው አዲሲቱ ዓለም ትርጉም በ5:00 ብር ሊበረከት እንደሚችል ጥቀስ።
18 ደቂቃ፦ “የአምላክ ቃል ኃይል አለው።” በጥያቄና መልስ። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር— 1994 በተባለው ቡክሌት መቅድም ላይ የተመሠረተ ዘወትር መጽሐፍ ቅዱስ የማንበብን አስፈላጊነት የሚያጎላ አስተያየት ጨምር።
17 ደቂቃ፦ “በችግር በተሞላው ዓለም ውስጥ የመጽናናትና የተስፋ ምንጭ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። የተጠቆሙልንን የአቀራረብ ዘዴዎች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ትዕይንቶችን አዘጋጅ።
መዝሙር 177 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 172
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ የጉባኤው መዋጮ የደረሰው መሆኑን የገለጸበት ማስታወቂያ ካለ ጨምረህ አቅርብ። ለመስክ አገልግሎት የተደረገውን ዝግጅት ጠቁም።
17 ደቂቃ፦ “ምን ዓይነት መንፈስ ታሳያላችሁ?” ንግግር። በታኅሣሥ 1977 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 1 አንቀጽ 4, 5 የተሰጠውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።
18 ደቂቃ፦ “የመንግሥት ስብከታችንን ለማሻሻል የምንችልባቸው መንገዶች።” በጥያቄና መልስ። የመንግሥት አገልግሎታችን የሚሰጣቸው ሐሳቦች እንዴት ጥሩ ውጤት እንደሚያስገኙ የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 191 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 21 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚሰጥ ንግግር። ትምህርቱን ለጉባኤው እንደሚሠራ አድርገህ አቅርበው።
20 ደቂቃ፦ “ክርስቶስ በአምላክ ዝግጅት ውስጥ ያለውን ሚና መቀበል።” አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ላይ የተመሠረተ ንግግር። ማጠቃለያ ጥያቄዎችን አክል።
15 ደቂቃ፦ “‘ሌላ ጊዜም’ እንዲሰሙ እርዷቸው።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። ጥናት ስናስጀምር መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳዩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሁለት ጥሩ ትዕይንቶችን አቅርብ።
መዝሙር 33 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 28 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
17 ደቂቃ፦ “ከሌሎች ጋር በማገልገል የሚገኙ በረከቶች።” በጥያቄና መልስ። ሁሉም አስፋፊዎች ሁልጊዜ ከሌሎች ጋር በግል ተቀጣጥረው ከመሄድ ይልቅ የጉባኤውን የመስክ አገልግሎት ዝግጅት እንዲደግፉ አበረታታ። ከጉባኤው ጋር ማገልገል ተጨማሪ በረከት ከማስገኘቱም በላይ አገልግሎታችን ይበልጥ እንዲሳካልንና እርስ በእርስ እንድንበረታታ ያስችላል።
18 ደቂቃ፦ በታኅሣሥ ወር ራእይ መደምደሚያው የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። ይህን መጽሐፍ ስለማበርከት አዎንታዊ አመለካከት ያዙ። በገንዘብ እጥረት ምክንያት የሚበረከት አዲስ መጽሐፍ መያዝ ካልቻልክ የራስህን ቅጂ ያዝና ሌላ ቅጂ ማግኘት ከሚፈልጉ ትእዛዝ ተቀበል። ይህን ወቅታዊ ውድ ሀብት ስታበረክቱ የጋለ ስሜት ይኑራችሁ። ለምን? ምክንያቱም ይሖዋ በመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሆነው በዚህ መጽሐፍ አማካይነት ለዘመናችንና ለወደፊቱ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ስለገለጸ ነው። ያለነው “በጌታ ቀን” ውስጥ ነው። (ራእይ 1:10) ሌላው ቀርቶ በመግቢያህ ላይ ለዘመናችን በጣም አስፈላጊ የሆነ ትንቢት ልታሳየው እንደምትፈልግ ልትገልጽና ራእይ 12:7–10, 12ን ወይም ራእይ 6:2, 4, 5, 8ን ልትገልጥ ትችላለህ። እርግጥ አንዳንድ አስፋፊዎች ራእይ 21:3–5ን ቢጠቀሙ ይበልጥ እንደሚቀላቸው ይሰማቸው ይሆናል። በራእይ 1:3 ላይ ያሉት ቃላትም በሆነ መንገድ ተቀነባብረው ሊቀርቡ ይችላሉ። እነዚህን ጥልቅና ዐበይት ትንቢቶች ለማጉላት እንደ ራእይ መደምደሚያው ያለ አንድም መጽሐፍ እንደሌለ ልንተማመን እንችላለን። አንድ ብቃት ያለው አስፋፊ አንዳንዶቹን ነጥቦች በትዕይንት እንዲያሳይ አድርግና በታኅሣሥ ወር ሁሉም ይህን መጽሐፍ እንዲያበረክቱ አበረታታ።
መዝሙር 114 እና የመደምደሚያ ጸሎት።