ተመላልሶ መጠየቆችን በማድረግ ለሰዎች ያላችሁን አሳቢነት አሳዩ
1 ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ መፈለግ ሌሎች የመንግሥቱን መልእክት እንዲሰሙ አጋጣሚ ለመፍጠር ያላችሁን ፍላጎት ያሳያል። ስለዚህ ለሰዎች ያላችሁን አሳቢነት የምታሳዩበት አንዱ መንገድ ይህ ስለሆነ በጥር ወር ጽሑፍ ያበረከታችሁላቸው ሰዎች ያሳዩትን ፍላጎት ተከታትላችሁ እርዱ።
2 ሰዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ስናነጋግር ጥሩ ማሳታወሻ መያዛችን የተሳካ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ መሠረት ይሆነናል። የተወያያችሁበትን ርዕስ፣ ያበረከትከውን ጽሑፍና ተመልሰህ ስተመጣ የምትወያዩበትን ርዕስ ጻፍ። ከዚያም ከትራክት፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የውይይት አርዕስት ከተባለው ቡክሌት፣ ማመራመር ወይም ለዘላለም መኖር ከተባለው መጽሐፍ ተስማሚ ሐሳብ ተዘጋጅ። በብሮሹሮችም መጠቀም ይቻላል። እንደ አስተዋጽኦ አድርገህ ለመጠቀም እንድትችል በእነዚህ ጽሑፎች ውስጥ የሰፈሩትን ነጥቦች ልታሰምርባቸው ወይም ራስህ ትንሽ ማስታወሻ ልትይዝ ትችላለህ። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግ ከመጠን በላይ ብዙ የሆነ ትምህርት ለመሸፈን ወይም ሁሉንም ጥያቄዎች ለመመለስ አትሞክር፤ ከዚህ ይልቅ በተመላልሶ መጠየቁ መደምደሚያ ላይ ለወደፊቱ ለጥናት የሚሆን አንድ ጥያቄ ጠይቀህ ወይም ርዕስ አስተዋውቀህ በእንጥልጥል ተወው።
3 “ታላቁ አስተማሪ” የተባለውን መጽሐፍ አበርክተህ ከነበረ ለተመላልሶ መጠየቅ የሚሆን አንዱ አቀራረብ የሚከተለው ሊሆን ይችላል:-
◼ “እንደገና በመገናኘታችን ደስ ብሎኛል። በቅርቡ ልጆችን ለማሳደግ ኢየሱስን እንደ ሞዴል አድረጎ ስለመጠቀም ያደረግነውን ውይይት እንደሚያስታውሱ ተስፋ አደርጋለሁ። ዛሬ ልጆችን እንዴት ማሠልጠን እንደሚቻል የሚጠቁሙ አንዳንድ ጥቅሶችን ተዘጋጅቻለሁ። [በውይይት አርዕስት ቁጥር 38ሐ ላይ “ጋብቻ” በሚለው ርዕስ ሥር ባሉት ጥቅሶች በኤፌ. 6:4፤ ምሳሌ 22:6, 15፤ 23:13, 14 ተጠቀም።] ከዚያም በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት ከተባለው ትራክት ላይ ጥቂት አንቀጾችን ልትወያዩ ትችሉ ይሆናል፤ ቀሪውን አብረህ ለማጥናት ደግሞ ተመለሰህ ልትሄድ ትችላለህ።
4 ሌላው አቀራረብ ይህ ሊሆን ይችላል:-
◼ “ባለፈው ጊዜ ባደረግነው ውይይት ስለ ኢየሱስ ትምህርቶች ትክክለኛ እውቀት የማግኘትን አስፈላጊነት ተነጋግረን ነበር። ኢየሱስ ከሰጣቸው አስደሳች ተስፋዎች አንዱ ታላቁ አስተማሪ በተባለው መጽሐፍዎት ምዕራፍ 44 ላይ በሚገኘው ‘ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ’ በሚለው ርዕስ ሥር ይገኛል። እስካሁን እዚህ ምዕራፍ ላይ ላይደርሱ ስለሚችሉ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉትን ዋና ዋና ነጥቦችና ጥቅሶች ላነብልዎት እሻለሁ።”
5 “አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?” የተባለውን ብሮሹር አበርክተህ ከነበረ ሰዎች ያሳዩትን ፍላጎት ለመከታተል እንዲህ ልትል ትችላለህ:-
◼ “ከዚህ በፊት ‘አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?’ የሚል አንገብጋቢ ጥያቄ የሚያነሳውን የዚህን ብሮሹር ቅጂ ትቼልዎት ሄጄ ነበር። ይህን ብሮሹር ካነበቡ በኋላ ምን መደምደሚያ ላይ ደረሱ? [መልስ እንዲሰጥ እድል ስጠው።] ቅዱሳን ጽሑፎች በሰላም ስለምንኖርባት ገነት የሆነች አዲስ ዓለም የሚሰጡትን ተሰፋ ሲያነቡ እንደተደሰቱ የታወቀ ነው። [በገጽ 3 እና 4 ላይ ያሉትን ሥዕላዊ መግለጫዎች አሳየውና ከአዲሱ ዓለም ማራኪ ገጽታዎች አንዳንዶቹን ጠቁም።] እርስዎም ሆኑ የሚወዷቸው ሰዎች እንደዚሀ ባለው ዓለም ውስጥ ለመኖር እንደምትፈልጉ እርግጠኛ ነኝ። በገጽ 31 ላይ ያለው 16ኛው አንቀጽ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል ልብ ይበሉ።” አንቀጹን አንብብና ይሖዋን መፈለግ ማለት መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ስለ እሱና ስለ ዓላማዎቹ የበለጠ ማወቅ ማለት እንደሆነ ግለጽ።
6 ይሖዋ በጎቹን እንደሚጠብቅ አፍቃሪ እረኛ በመሆን ፍጹም ምሳሌ ትቶልናል። (ሕዝ. 34:11–14) የእሱን ፍቅራዊ አሳቢነት ለመምሰል የምናደርገው ልባዊ ጥረት ፍቅራችንን ከማሳየቱም በላይ ለሌሎች በረከቶችን ያስገኝላቸዋል።