የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/95 ገጽ 2
  • የጥር የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥር የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥር 2 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 9 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 16 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 23 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 30 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 1/95 ገጽ 2

የጥር የአገልግሎት ስብሰባዎች

ጥር 2 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

22 ደቂቃ፦ “ጉባኤው የተደራጀውና የሚመራው እንዴት ነው?”— አገልግሎታችን መጽሐፍ ምዕራፍ 4 በጥያቄና መልስ ይቀርባል። ቲኦክራሲያዊውን ድርጅት መቀበል ማለት ከድርጅቱ ቀድሞ መሄድ ማለት እንዳልሆነ በሚገባ አብራራ።

13 ደቂቃ፦ “በቆዩ መጽሐፎቻችን በጥሩ መንገድ መጠቀም።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። ጉባኤው የትኞቹ የቆዩ መጻሕፍት እንዳሉ እንዲያውቅ አድርግ፤ ሁሉም ለአገልግሎት የሚጠቀሙባቸውን የቆዩ መጻሕፍት እንዲወስዱ አበረታታ። በተሰጡት አቀራረቦች በመጠቀም አንድ ወይም ሁለት አጫጭር ትዕይንቶችን አዘጋጅ።

መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 9 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 174

7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

25 ደቂቃ፦ “ለመንጋው እረኞች የሆኑ የበላይ ተመልካቾች።” መሪ የበላይ ተመልካቹ ከአገልግሎታችን መጽሐፍ ከገጽ 28–30 እና ከገጽ 39–41 (የላይኛው ክፍል) ያለውን ሐሳብ ይከልሳል። ከዚያም ከገጽ 30–39 (የላይኛው ክፍል) ያለውን ስለ ሽማግሌ ብቃቶች የሚናገር ክፍል በመመርኮዝ የቤተሰብ ኑሮን፣ ምክንያታዊነትንና የማስተማር ችሎታን በተመለከተ እድገት ከሚያሳይ አንድ ዲያቆን ጋር ይወያያል።

13 ደቂቃ፦ እምነታችሁን ሊፈታተኑ የሚችሉ የሕክምና ሁኔታዎችን ለመቋቋም ተዘጋጅታችኋልን? በቅድሚያ የተሰጠውን የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገውን ሰነድ እና የመታወቂያ ካርድ አስፈላጊነት ወንድሞች እንዲገነዘቡት የሚረዳ ችሎታ ባለው ሽማግሌ የሚቀርብ ከበድ ተደርጎ የሚታይ ግን ቀስቃሽ የሆነ ንግግር። ለዚህ ብቁ የሆኑና የሚፈልጉ ሁሉ ካርዶቹን በመሙላት ይህን መከላከያ ማግኘት እንዲችሉ የአምናውን የጥር ፕሮግራም በድጋሚ አቅርብ። ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በጥር 1994 የመንግሥት አገልግሎታችን በገጽ 2 ላይ “ጥር 10 የሚጀምር ሳምንት” በሚለው ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ ተመልከት።

መዝሙር 191 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 16 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 155

7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በቅርቡ ከወጡ መጽሔቶች የተወሰዱ የመነጋገሪያ ነጥቦችን አብራራ። ሁሉም በብሔራዊ በዓላት ቀኖችና በፊታችን ቅዳሜና እሑድ በሚደረገው አገልግሎት እንዲሳተፉ አበረታታ።

10 ደቂቃ፦ “ለሌሎች አሳቢነትን አሳዩ— ክፍል 1።” ጥያቄና መልስ። ሽማግሌዎች የስብስባ ቦታዎች በንጽሕና መያዛቸውን በመቆጣጠር ረገድ በቅርብ ተባብረው የመሥራታቸውን አስፈላጊነት አሳስብ።— የካቲት 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 5 ላይ ያለውን የጥያቄ ሣጥን ክፍል 2 ተመልከት። ለጉባኤው እንደሚስማማ አድርገህ አቅርብ።

13 ደቂቃ፦ “እርስ በርስ ለመረዳዳት ያለብን ኃላፊነት።” በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት።

15 ደቂቃ፦ “ተመላልሶ መጠየቆችን በማድረግ ለሰዎች ያላችሁን አሳቢነት አሳዩ።” ሦስት ወይም አራት አስፋፊዎች ሆነው ተመላልሶ መጠየቆች የሚደረግበትን ዓላማና የተመላልሶ መጠየቅን አስፈላጊነት ይወያያሉ። ጥናቶችን ለማግኘት ግብ የማድረግን አስፈላጊነት አጉላ። የተሰጡትን አቀራረቦች ከልስ። ሦስት ወይም አራት አስፋፊዎች በቡድን ሆነው አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን እንዲያሳዩና ምስጋናና የማሻሻያ ሐሳቦችን እንዲለዋወጡ አድርግ።

መዝሙር 13 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 23 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 79

5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

25 ደቂቃ፦ “ፍቅራዊ ጥበቃ።” አገልግሎታችን የተባለውን መጽሐፍ በመመርኮዝ የጉባኤው የመጽሐፍ ጥናት መሪ (ከገጽ 43–5) እና ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች (ገጽ 47–52) ስለሚጫወቱት ሚና እንዲሁም በገጽ 54 ላይ ያለው የመደምደሚያ አንቀጽ በውይይት ይቀርባል።

15 ደቂቃ፦ “ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ የሆነው የግል ጥናት።” ጥያቄና መልስ። ከመጠበቂያ ግንብ 6–106 ከገጽ 7–9 ላይ የተመረጡ ሐሳቦችን አክለህ አቅርብ።

መዝሙር 180 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 30 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 34

6 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።

10 ደቂቃ፦ “ቲኦክራሲያዊ ቤተ መጻሕፍት ማደራጀት የሚቻለው እንዴት ነው?።” በኅዳር 1, 1994 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 28–31 ላይ ባለው ሐሳብ ላይ የተመሠረተ ንግግር።

17 ደቂቃ፦ “ሁልጊዜ ሥራ ይብዛላችሁ።” ጥያቄና መልስ። እንደ ሽማግሌ፣ የቤት እመቤት ወይም አቅኚ ካሉት በሥራ የተጠመዱ አስፋፊዎች ጋር የሚደረጉ ሁለት ወይም ሦስት ቃለ ምልልሶችን አዘጋጅ፤ ፕሮግራማቸው የተጣበበ ቢሆንም እንዴት ደስተኛ ሊሆኑ እንደቻሉ እንዲገልጹ ጠይቃቸው።

12 ደቂቃ፦ በየካቲት ወር ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። ሰዎች በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያለው እውቀት ለምን እንደሚያስፈልጋቸው ግለጽ። (መጠበቂያ ግንብ 7–109 ገጽ 18 አንቀጽ 17, 18⁠ን ተመልከት።) መጽሐፉን ያነበቡት የገለጹትን አድናቆት የሚጠቁሙ ተሞክሮዎችን በአጭሩ ተናገር። (የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1, 1989 ገጽ 32 እና የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1, 1991 ገጽ 32 ተመልከት።) ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ አበርክተንላቸው ፍላጎት ካሳዩ ሰዎች ጋር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እንዴት መጀመር እንደሚቻል የሚያሳዩ ጥቂት ሐሳቦችን ጠቁም። ብቃት ያለው አንድ አስፋፊ አንድ አቀራረብ በትዕይንት እንዲያሳይ አድርግ።

መዝሙር 177 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ