በቆዩ መጽሐፎቻችን በጥሩ መንገድ መጠቀም
1 ይሖዋ የተትረፈረፈ ምርጥ መንፈሳዊ ምግብ ሰጥቶናል። ከእነዚህ እውቀቶች አብዛኞቹ በቅርብ ዓመታት በታተሙት ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት ውስጥ ይገኛሉ። በጥር ወር ከ1982 በፊት የታተሙትን ማናቸውንም ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት እናበረክታለን። ከእነዚህ መጽሐፎች መካከል አንዳንዶቹ አሁንም ቤትህ በጥሩ ሁኔታ ይገኛሉ? በጉባኤስ ይገኛሉ? እነዚህ መጻሕፍት ካሉ ይዘታቸውን መከለስና ሰዎችን ስታነጋግሩ የምትጠቀሙባቸውን የመነጋገሪያ ነጥቦች መምረጥ ጥሩ ነው።
2 “ዘላለማዊ ዓላማ” የተባለውን መጽሐፍ የምትጠቀም ከሆነ እንዲህ በማለት ልትጀምር ትችላለህ:-
◼ “[ሰላምታ።] ከአምላክ ቃል አንድ የሚያበረታታ ሐሳብ ልናካፍልዎት እንፈልጋለን። ኢየሱስ እንዲህ ብለን እንድንጸልይ ለምን እንዳስተማረን ጠይቀው ያውቃሉ:- [ማቴዎስ 6:9, 10ን ጥቀስ።] ምንም እንኳን በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም ያነጋገርናቸው ብዙ ሰዎች ስለ አምላክ ስም ሰምተው አያውቁም። አንድ አጭር አንቀጽ እንዳነብልዎት ቢፈቅዱለኝ። [ገጽ 16 አንቀጽ 21ን ግለጥ።] በቅርቡ ዘላለማዊ ዓላማው ሲፈጸም የአምላክ ስም ይቀደሳል። ይህም ከአምላክ መንግሥት ጋር የተያያዘ ነው። በሞዴል ጸሎቱ ላይ ስለሚገኙት የኢየሱስ ቃላት ከዚህ መጽሐፍ ብዙ መማር ይችላሉ።”
3 “ታላቁ አስተማሪ” የተባለውን መጽሐፍ የምታበረክት ከሆነ ይህን አቀራረብ ልትሞክር ትችላለህ:-
◼ “[ሰላምታ።] በዚህ ወቅት ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስን ይጠቅሳሉ። ብዙ ሰዎች ገና ሕፃን ወይም ሊሞት የሚሠቃይ ሰው አድርገው ይመለከቱታል። ስለዚህ በዚያን ወቅት የሚያስቡት ስለ ልደቱ ወይም ስለ ሞቱ ነው። ብዙውን ጊዜ እሱ ያደረጋቸውና የተናገራቸውን አስደናቂ ነገሮች ይዘነጋሉ። በዮሐንስ 17:3 ላይ ስለ እሱ ትክክለኛ እውቀት ማግኘት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እናነባለን። [አንብብ።] ለምሳሌ ያህል እስቲ በታላቅ አስተማሪነቱ ያስተማራቸውን እነዚህን ርዕሶች ይመልከቱ።” መጽሐፉን ገልጠህ ገጽ 3 እና 4ን አሳይና አበርክተው።
4 ይህንኑ መጽሐፍ ለማበርከት የሚያስችል ሌላው አቀራረብ የሚከተለው ሊሆን ይች ላል:-
◼ “[ጤና ይስጥልኝ።] እኔ [ስምህን ተናገር] እና ጓደኛዬ [ስሙን ተናገር] ጥቂት ጊዜ ወስደን በቤተሰብ ሕይወት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን እንዴት መቋቋም እንደሚችሉ ከወላጆችና ከወጣቶች ጋር እየተነጋገርን ነው። ዛሬ ልጆችን ማሳደግ ቀላል እንዳልሆነ የሚገነዘቡ ይመስለኛል። [ትንሽ ቆም በል።] ብዙ ወጣቶች እንደ ሞዴል የሚመለከቷቸውን ሰዎች ይፈልጋሉ፤ ከሁሉ የላቀው ምሳሌ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ አይደለም እንዴ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ፍቀድለት።] 1 ጴጥሮስ 2:21 ላይ እንዲህ እናነባለን:- [አንብብ።] ብዙ ሰዎች እሱን ለመምሰል ቢጥሩ ዓለም ምን ይመስል ነበር ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ቤተሰቦች ከእሱ ለመማርና እሱን ለመምሰል እንዲችሉ የሚረዳ ግሩም መጽሐፍ ይኸውልዎ።”
5 “አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?” በተባለው ብሮሹር ለመጠቀም ትመርጥ ይሆናል። ከሆነ እንዲህ ለማለት ትችላለህ:-
◼ “ብዙ ሰዎች በዚህ ዓለም ላይ ይህን ያህል መከራ እንዲኖር አምላክ ለምን እንደፈቀደ ይጠይቃሉ። ሁሉን ቻይ ስለሆነ መከራን ለማስወገድ ለምን አንድ ነገር አያደርግም? እርስዎ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ እንዳልተወን ያረጋግጥልናል።” ገጽ 27 አንቀጽ 22ን ግለጥና መዝሙር 37:11, 29ን አንብብ። ወደፊት ልንጠባበቀው የምንችለውን ሁኔታ የሚጠቁመውን ማራኪ ሥዕላዊ መግለጫ አሳየው። ብሮሹሩን ከተቀበለ ብሮሹሩን መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት እንዴት ሊጠቀምበት እንደሚችል ለማሳየት ተመልሰህ ብትመጣ ደስ የሚልህ መሆኑን ንገረው።
6 ጽሑፋችን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በይበልጥ እንዲመረምሩ ገፋፍቷቸዋል። የተማሩት ነገር ደስታ የተሞላበት የወደፊት ተስፋ አስገኝቶላቸዋል። (መዝ. 146:5) እነሱን መርዳት መብታችን ነው።