ለጸሐፊውና ለአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የተሰጠ ማሳሰቢያ
በየዓመቱ የየካቲት የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ “የዘወትር አቅኚዎችን እንቅስቃሴ እንዲገመግሙ የሚያዝ ማስታወቂያ ያወጣል። የዚህ ግምገማ ዓላማ ምንድን ነው? የአገልግሎት ዓመቱ ሳያልቅ የሰዓት ግቡን በማሟላት ረገድ እርዳታ የሚያስፈልገው ማን እንደሆነ ለማወቅ እንዲችሉ ነው።
የዘወትር አቅኚዎች በየዓመቱ 1,000 ሰዓት እንዲያገለግሉ ይፈለግባቸዋል። በየካቲት መጨረሻ ላይ አንዳንድ አቅኚዎች ሰዓታቸው ዝቅተኛ እንደሆነ ይገነዘባሉ፤ ይህም ተስፋ እንዲቆርጡ ሊያደርጋቸው ይችላል። ብዙውን ጊዜ ሽማግሌዎች ማበረታቻና ተግባራዊ ሐሳቦችን በመለገስ ሊረዷቸው ይችላሉ። ይህ እርዳታ አቅኚዎች የሚፈለግባቸውን ሰዓት እንዲያሟሉ ወይም ከአቅኚነት እንዲወርዱ እስከማድረግ ድረስ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።
አቅኚዎች በዚህ ረገድ ሽማግሌዎች የሚያሳዩአቸውን ልባዊ አሳቢነት እንደሚያደንቁ የተረጋገጠ ነው። ጉባኤውም በአገልግሎታቸው በሚደሰቱና የተሰጣቸውን ሥራ በታማኝነት ከሚያከናውኑ አቅኚዎች ይጠቀማል።