የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/95 ገጽ 4
  • ገንዘብን በተገቢው መንገድ መያዝ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ገንዘብን በተገቢው መንገድ መያዝ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ተመላልሶ መጠየቅ አድርጉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ፍላጎት ያሳዩትን ሁሉ ተከታትሎ በመርዳት እንዲጠቀሙ ማድረግ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ለመስክ አገልግሎት የሚሆኑ መግቢያዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ ለማስተማር ይጠቅማል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 5/95 ገጽ 4

ገንዘብን በተገቢው መንገድ መያዝ

1 ለግላችንና ለመስክ አገልግሎት የምንጠቀምባቸው ብዛት ያላቸው የተለያዩ ጽሑፎች ማግኘት ከሚያመጣው ደስታ በተጨማሪ ሁሉም ጉባኤዎችና ቡድኖች የመጽሔትና የጽሑፍ ገንዘብ ሥርዓት ባለው መንገድ የመያዝ ኃላፊነት ተቀብለዋል። ገንዘብ የሚይዙ ወንድሞች “በአገባብና በሥርዓት” ለመያዝ እንዲችሉና ጥርጣሬ የሚያሳድር ምንም ነገር እንዳይኖር በተለያዩ መንገዶች ማሰልጠኛ ተሰጥቷቸዋል።—1 ቆሮ. 14:40፤ 2 ቆሮ. 8:19–21

2 የገንዘብ አያያዝን በተመለከተ አንዳንድ መሠረታዊ ነጥቦችን ብናውቅ ለሁላችንም ጠቃሚ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ጉባኤው ያለውን ገንዘብ መዝግበን እንይዛለን። አንድ ሰው ኮንትራት ሲገባ በሁለት ቅጂ የተፈረመበት ደረሰኝ (S–24–AM) ይዘጋጅና አንዱ ኮንትራት ላስገባው አስፋፊ ሁለተኛው ደግሞ ለሒሳብ ያዥው ይሰጣቸዋል። የመዋጮ ሣጥኖች ሁለት ብቃት ባላቸው ወንድሞች ይከፈትና ገንዘቡ ይወጣል። እነርሱም በሁለት ቅጂ በተዘጋጀ ደረሰኝ ላይ ይፈርሙና (አንድ ቅጂ ከገንዘቡ ጋር ለሒሳብ ያዥው ሌላኛው ቅጂ ደግሞ ለሒሳብ ምርመራ እንዲያገለግል ለጸሐፊው ይሰጣል።) የጽሑፍ አገልጋይ የሆነው ወንድም የተሸጡ ጽሑፎችን በሙሉ በጽሑፍ መቆጣጠሪያ ቅጽ (S–61a and b–AM) ላይ ይመዘግብና በየሳምንቱ ገንዘቡን ለሒሳብ ያዥው በሚያስረክብበት ጊዜ የደረሰኙን አንድ ቅጂ ይቀበላል። እንዲሁም የመጽሔት አገልጋይ የሆነው ወንድም በአቅኚዎችና በአስፋፊዎች የተወሰዱትን መጽሔቶች ይመዘግብና በሳምንት አንድ ጊዜ አንድ የደረሰኝ ቀሪ በመቀበል ለሒሳብ ያዥው ገንዘቡን ያስረክባል።

3 ሥርዓት ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ ይህን ማከናወን ያለባቸው ጽሑፍ ላይ ወይም መጽሔት ላይ የተመደቡ ወንድሞች ብቻ ናቸው። ማንም የቤተሰብ አባል ወይም ሌላ የጉባኤ አባል እነዚህን ወንድሞች ሳይጠይቅ ራሱ ጽሑፎችን መውሰድ አይችልም። እንዲያውም ጽሑፎችን ቆልፎ ማስቀመጥ የተሻለ ነው። ይህንን ሥራ እንዲያከናውኑ የተመደቡት ወንድሞች ጽሑፎች ሲመጡ ከኢንቮይስ ወይም ከሒሳብ መግለጫው ጋር በማመሳከር (በጽሑፍ እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ [S–28–AM] ላይ) ይመዘግባሉ። ምንም ዓይነት ጽሑፍ በዱቤ መሰጠት የለበትም። እኛ በዱቤ የመስጠት መብት የለንም። ሁሉም ጽሑፎች የሚወሰዱት እጅ በእጅ በመክፈል መሆን ይኖርበታል።—ሉቃስ 16:10

4 የሒሳብ አገልጋዩ (S–27–AM ላይ የሰፈሩትን መመሪያዎች በመከተል) ሁሉንም ገቢዎችና ለልዩ ልዩ ነገር የዋሉ ወጪዎችን በትክክልና ሳይውል ሳያድር መሙላት ይኖርበታል። ገንዘብ ባንክ ለማስገባትና የወርሃዊ ገንዘብ መላኪያና ቅናሽ መጠየቂያ ቅጽ (S–20–AM) ሞልቶ ለቅርንጫፍ ቢሮ ለመላክ ፈጣን መሆን ይኖርበታል። በእያንዳንዱ ወር መግቢያ ላይ ወርሃዊ ማወራረጃና የሒሳብ ሪፖርት (S–30– AM ቅጽ) ይሞላና በመንግሥት አገልግሎታችን በሚወጣው ፕሮግራም መሠረት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ እንዲነበብ ያደርጋል። ይህ ጉዳይ ቸል ተብሎ ቢታለፍ በጉባኤ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ለመሪ የበላይ ተመልካቹ ወይም ለወረዳ የበላይ ተመልካቹ ለማስታወስ ነፃነት ሊሰማው ይችላል።—1 ቆሮ. 4:2

5 መሪ የበላይ ተመልካቹ በየሦስት ወሩ ሒሳብ እንዲመረመር ዝግጅት ያደርጋል። እያንዳንዱ የተመዘገበው ሒሳብ ትክክል መሆኑና አለመሆኑ ሁለት ጊዜ በማመሳከር ስህተት ካለ ይስተካከላል። ሂሳቡ ተመርምሮ ካለቀ በኋላ በጽሑፍ ይገለጻል። ማንም ሰው ከጉባኤው ገንዘብ “ሊበደር” አይችልም። (የሚያዝያ 15, 1994 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19–20 ተመልከት።) ይህን አሠራር መከተል ጉድለት እንዳይከሰት ይረዳል። እንዲሁም ለጉባኤ የዋሉ ገንዘቦች በተገቢው መንገድ እንደሚቀመጡ ያረጋግጣሉ። የጽሑፎቻችንና የመጽሔቶቻችን ሒሳቦች በጥሩ መንገድ ይያዛሉ። በዚህም ምክንያት ጉባኤው ጽሑፎችን ያለ ቅድሚያ ክፍያ ማግኘቱን ሊቀጥል ይችላል። በመሆኑም የጉባኤው ሒሳብ በትክክል እንዲያዝና የጽሑፍም ሆነ የመጽሔት ሒሳብ በጥሩ ሁኔታ በመያዙ ጉባኤው የቅድሚያ ክፍያ ሳይጠየቅ ጽሑፎችን ማግኘቱን ሊቀጥል ይችላል። በተጨማሪም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወንድሞች በሙሉ ጥሩ ሕሊና እንዲኖራቸውና ከማንኛውም ክስ ነፃ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል።—1 ጴጥ. 3:16፤ ዕብ. 13:18

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ