የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/95 ገጽ 2
  • የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ግንቦት 1 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 8 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 15 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 22 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 29 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 5/95 ገጽ 2

የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች

ግንቦት 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 215

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “ለቅን ሰዎች የሚሆን ምሥራች።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን ተጠቅመህ ትዕይንት አዘጋጅ።

20 ደቂቃ፦ “ለሁሉም ሰው የሚሆን ልዩ የመንግሥት ዜና።” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በመወያየት የሚቀርብ። የመንግሥት ዜና እስከ አሁን ድረስ ምን ያህል እንደተሰራጨ ባጭሩ ግለጽ። በተለይ ለተደረጉት የአገልግሎት ዝግጅቶች የተሰጠውን ጥሩ ድጋፍና አዳዲስ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በመስክ አገልግሎት ያደረጉትን ተሳትፎ ጥቀስ። ምን ያህል ክልሎች እንደተሸፈኑ ግለጽ። ሌላ ጉባኤ እርዳታ ቢጠይቅ ምን ሊደረግ እንደሚገባ ግለጽ። የወሰዱትን የመንግሥት ዜና ለማሰራጨት ተጨማሪ ጥረት እንዲያደርጉ ሁሉንም አበረታታ። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ስም በማስታወሻ ላይ የመመዝገብንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ግብ በማድረግ ተመላልሶ መጠየቅ የማድረግን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። በተሰጡት አቀራረቦች ትዕይንት አዘጋጅ።

መዝሙር 155 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 143

15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “አንተም ጥሩ ጥሩ ተሞክሮዎችን ልታገኝ ትችላለህ!” ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች የመንግሥት ዜና ሲያበረክቱ ያገኟቸውን የሚያበረታቱ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።

15 ደቂቃ፦ “ገንዘብን በተገቢው መንገድ መያዝ።” በአንድ ሽማግሌና በአንድ ዲያቆን መካከል የሚደረግ ውይይት። የመጨረሻው አንቀጽ መነበብ ይኖርበታል።

15 ደቂቃ፦ “ቤታቸው ያላገኘናቸውን ሰዎች በማስታወሻ መያዝ የሚኖርብን ለምንድን ነው?” ጥያቄና መልስ።

መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 105

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ፦ “ብርሃን አብሪዎች በመሆን ምሳሌያችንን መከተል።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።

20 ደቂቃ፦ አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት ከተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 7 ከገጽ 60–4 በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።

መዝሙር 6 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 47

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በሚመጡት ወራት ረዳት አቅኚ ሆኖ ስለማገልገል ማበረታቻ ስጥ። አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 113–14 ላይ የተዘረዘሩትን ብቃቶች በአጭሩ ጥቀስ።

35 ደቂቃ፦ “ለጉባኤ ስብሰባዎች አድናቆት ማሳየት።” አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 64–9 በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት። ለመጠበቂያ ግንብ ጥናት ሁሉም የየራሳቸውን የጥናት ቅጂ ይዘው መምጣት እንዳለባቸው ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።

መዝሙር 114 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 136

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ሰዎችን በሚያነጋግሩበት ጊዜ የመግቢያቸው ክፍል አድርገው ከቅዱስ ጽሑፍ አንድ ጥቅስ እንዲያነቡ የሚያበረታታ ሐሳብ አቅርብ። ብዙ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት ስላላቸው መጽሐፍ ቅዱስ በሚነበብበት ጊዜ ለማዳመጥ ፈቃደኞች ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ክብደት ያለው ስለሆነ አንድን ቅን የሆነ ሰው እርምጃ እንዲወስድ ሊያንቀሳቅሰው ይችላል። ወደ በሩ በምንቀርብበት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱሳችንን አውጥተን በእጃችን መያዝ ጥሩ ሊሆን ይችላል። ጥቅሶች ሞቅ ባለ ስሜትና በትክክል መነበብ ይኖርባቸዋል።— ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 32–3፣ አንቀጽ 12–15⁠ን ተመልከት።

12 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አስቀድመን ስንዘጋጅና የተጠቀሱትን ጽሑፎች ስንይዝ ከስብሰባዎች ለምን የበለጠ ጥቅም እንደምናገኝ አብራራ።

23 ደቂቃ፦ “በሳምንቱ መካከል ከሚደረጉ ስብሰባዎች ጥቅም ማግኘት።” አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 69–76 በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። እንያንዳንዱ ሰው በመጽሐፍ ጥናት ወቅት የሚጠናው የራሱ መጽሐፍ እንዲኖረው ጎላ አድርገህ ግለጽ።

መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ