የመስከረም የአገልግሎት ስብሰባዎች
መስከረም 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 105
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ “ፍላጎት ያሳዩትን ሁሉ ተከታትሎ በመርዳት እንዲጠቀሙ ማድረግ።” ስለ ተመላልሶ መጠየቆች የተሰጡትን አቀራረቦች ከልስ። ይህን ክፍል እንዲያቀርብ የተመደበው ወንድም ከሁለት ወይም ከሦስት አስፋፊዎች ጋር ተመላልሶ ሲጠይቁ ምን ብለው እንደሚናገሩ ከተወያየ በኋላ አቀራረባቸውን እንዲያሳዩ ይጠይቃቸዋል።
15 ደቂቃ፦ “ሌሎች ራሳቸውን እንዲጠቅሙ እርዷቸው።” የተሰጡትን አቀራረቦች ከልስና ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
መዝሙር 204 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 11 ወይም 18 የሚጀምር ሳምንት (“ደስተኛ አወዳሾች” የአውራጃ ስብሰባ የሚደረግባቸው ሳምንታት)
መዝሙር 155
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
7 ደቂቃ፦ የነሐሴ ወር የጉባኤው የመስክ አገልግሎት ሪፖርት። በአገልግሎት የበላይ ተመልካች የሚቀርብ። አቅኚዎችን ጨምሮ ምን ያህሉ ሪፖርት አድርገዋል? ሁሉም አስፋፊዎች ሪፖርታቸውን መልሰዋል? ሁሉም አዘውታሪ አስፋፊዎች እንዲሆኑ አበረታታቸው።
15 ደቂቃ፦ “መጽሔቶቻችንን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙባቸው።” በአባሪ ገጽ ከአንቀጽ 1 እስከ 13 ላይ የተመሠረተ በአገልግሎት የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ሞቅ ያለ ንግግር።
18 ደቂቃ፦ “ለልጆቻችሁ ምን ዓይነት ግቦች አውጥታችሁላቸዋል?” ጥያቄና መልስ። አንድ ወይም ሁለት ምሳሌ የሚሆኑ ወጣቶች ወይም ከልጅነታቸው ጀምሮ ይሖዋን ያገለገሉ አዋቂዎች በመንግሥቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጠቃሚ ግቦችን በመምረጥ በኩል ወላጆቻቸው እንዴት እንደረዷቸው አጠር አድርገው እንዲናገሩ አድርግ።
መዝሙር 187 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 177
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ሁሉንም ነገር ለአምላክ ክብር አድርጉት።” በሽማግሌ የሚቀርብ አድማጮች የሚካፈሉበት ንግግር። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በነሐሴ 15, 1992 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 15–20 ላይ የተመሠረተ ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።
10 ደቂቃ፦ “በይሖዋ መመርመሩ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?” በሽማግሌ የሚቀርብ አበረታች ንግግር።
15 ደቂቃ፦ “መጽሔቶቻችንን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙባቸው።” በአባሪው ገጽ ከ14 እስከ 16 ባሉት አንቀጾች ላይ ከአድማጮች ጋር ተወያይ። በጥቅምት ወር መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ለማሰራጨት ልዩ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። መጽሔቶቹ በተለያየ ቋንቋ ስለሚታተሙ የውጪ ቋንቋ ተናጋሪዎች ሲያጋጥሙን መጽሔቱ በራሳቸው ቋንቋ አንደሚገኝ መንገር አለብን። (ለዚያ የአገልግሎት ክልል ለተመደበው የውጪ ቋንቋ ተናጋሪ ጉባኤ ሁኔታውን ማሳወቅ አለብን።) መጽሔቶች በየሳምንቱ አዳዲስ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተደጋግሞ በተሠራበት የአገልግሎት ክልል ውስጥ መጽሔቶቻችንን ማበርከት የሰዎችን ፍላጎት የሚያሳድግ ከሁሉ የተሻለ ውጤታማ መንገድ ሊሆን ይችላል። በተመላልሶ መጠየቁ ወቅት ፍላጎት ካሳዩ ኮንትራት እንዲገቡ ሐሳብ አቅርቡላቸው። የአንድ ቤተሰብ አባላት በአንቀጽ 14 ላይ በተገለጸው መሠረት ልምምድ ሲያደርጉ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። በተጨማሪም የምናበረክታቸውን መጽሔቶች ቁጥር ለመጨመር የሚረዱ አንዳንድ ሊሠሩ የሚችሉ ሐሳቦችን ግለጽ።
መዝሙር 143 እና የመደምደሚያ ጸሎት።