የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/95 ገጽ 1
  • ይሖዋን ዘወትር አወድሱት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋን ዘወትር አወድሱት
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 9/95 ገጽ 1

ይሖዋን ዘወትር አወድሱት

1 በጣም አስፈላጊ ከመሆናቸው የተነሳ ዘወትር ትኩረታችንን የሚሹ ጥቂት እንቅስቃሴዎች አሉ። ከእነዚህ መካከል መብላት፣ መተንፈስና መተኛት ይገኙበታል። በሕይወት እንድንቀጥል ከተፈለገ እነዚህ ነገሮች የግድ አስፈላጊ ናቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ “ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት . . . እናቅርብለት” ብሎ ባሳሰበ ጊዜ ምሥራቹን ለመስበኩ ሥራ ተመሳሳይ ቦታ ሰጥቶታል። (ዕብ. 13:15) ስለዚህ ይሖዋን የማወደሱ ተግባርም የዘወትር ትኩረታችንን የሚሻ ነው። ሰማያዊ አባታችንን በየዕለቱ ለማወደስ መጣጣር ይገ ባናል።

2 ኢየሱስ ሰዎች ትኩረቱን ሊከፋፍሉት በሞከሩ ጊዜ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እሰብክ ዘንድ ይገባኛል” በማለት መልሶላቸዋል። (ሉቃስ 4:43) በሦስት ዓመት ተኩል አገልግሎቱ ወቅት በየዕለቱ ያከናውን የነበረው እያንዳንዱ ነገር በሆነ መንገድ አምላክን ከማክበር ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነበር። ጳውሎስ በ1 ቆሮንቶስ 9:16 ላይ “ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ” በማለት የገለጸውን ሐሳብ ስንመለከት እርሱም እንደ ኢየሱስ ተሰምቶት እንደነበር እንገነዘባለን። ሌሎች ታማኝ ክርስቲያኖችም ስለ ተስፋቸው ለሚጠይቋቸው ሰዎች መልስ ለመስጠት ዘወትር ዝግጁ እንዲሆኑ ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል። (1 ጴጥ. 3:15) በዛሬው ጊዜ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ቀናተኛ አቅኚዎችና በሚልዮን የሚቆጠሩ የጉባኤ አስፋፊዎች እንዲህ ያሉትን ግሩም ምሳሌዎች ለመኮረጅ ጥረት ያደርጋሉ።

3 ምሳሌያችን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ባሳየው ከሙሉ ልብ የመነጨ ቅንዓት ላይ ስናሰላስል ፈለጉን በቅርብ ለመከታተል እንገፋፋለን። (1 ጴጥ. 2:21) የዕለት ተዕለት የኑሮ ችግሮች ሲያጋጥሙን አንዳንድ ጊዜ ተስፋ እንቆርጥ ይሆናል። የሙሉ ጊዜ ሰብዓዊ ሥራ የምንሠራ ከሆነ የምናገኛቸውን አጋጣሚዎች በየዕለቱ ይሖዋን ለማወደስ ልንጠቀምባቸው የምንችለው እንዴት ነው? በርከት ያለ ጊዜ የሚጠይቁብንን የቤተሰብ ኃላፊነቶችንም ቢሆን ችላ ማለት አንችልም። አብዛኞቹ ወጣቶች ጊዜያቸው አስፈላጊ በሆነው ዕለታዊ ትምህርት ተይዟል። አንዳንዶች ይሖዋን በየዕለቱ በሕዝብ ፊት ማወደስ የማይቻል ይመስላቸዋል። ሌሎች ደግሞ ምሥራቹን በመስበኩ ሥራ ሳይካፈሉ አንድ ወር ሙሉ ያሳልፉ ይሆናል።

4 ኤርምያስ የይሖዋን ቃል ሳይናገር ዝም ብሎ መቀመጥ አላስቻለውም ነበር። ለጥቂት ጊዜ በይሖዋ ስም መናገሩን ሲያቆም በውስጡ እንደሚነድ የሚያንገበግብ እሳት ሆኖ ተሰምቶት ነበር። (ኤር. 20:9) ኤርምያስ ከአቅም በላይ መስሎ የሚታይ ችግር በሚያጋጥመው ጊዜ እንኳ የይሖዋን መልእክት ዘወትር ለሌሎች ይናገር ነበር። የእርሱን የድፍረት ምሳሌ በመኮረጅ ፈጣሪያችንን በየዕለቱ ማወደስ የምንችልባቸውን አጋጣሚዎች ያለመታከት መፈለግ እንችላለንን?

5 ስለ ይሖዋ የምንናገርበት ጊዜ አስቀድመን አመቻችተን ከሌሎች አስፋፊዎች ጋር በመሆን በጉባኤያችን ክልል ውስጥ በምናደርገው መደበኛ ምሥክርነት ብቻ መወሰን የለበትም። ዋናው የምንፈልገው ነገር ሰሚ ጆሮ ነው። በየዕለቱ ከሰዎች ጋር እንገናኛለን። ሰዎች ወደ ቤታችን ይመጣሉ፣ የምንሠራው ከሰዎች ጋር ነው፣ በገበያ ቦታዎች ብንሰለፍ ከሰዎቸ ጋር ነው፣ በአውቶቡስ ስንጓዝም ሰዎች አብረውን ይኖራሉ። ውይይት ለመጀመር የሚፈለገው ነገር ወዳጃዊ ሰላምታና ስሜትን የሚኮረኩር ጥያቄ ወይም ሐሳብ ማቅረብ ብቻ ነው። ብዙዎች እንዲህ ዓይነቱ ምሥክርነት ከሁሉ የተሻለ ፍሬያማ ሆኖ አግኝተውታል። ምሥራቹን ለሰዎች ለመናገር የሚያስችሉ ብዙ አጋጣሚዎች እያሉን ስለ መንግሥቱ ምሥክርነት ሳንሰጥ አንድ ወር ሙሉ ማሳለፋችን ተገቢ አይ ሆንም።

6 ይሖዋን የማወደሱ መብት ፍጻሜ የለውም። መዝሙራዊው እንደተናገረው እስትንፋስ ያለው ሁሉ ይሖዋን ማወደስ አለበት። እኛም ከእነዚህ መካከል ለመሆን እንደምንፈልግ አያጠራጥርም። (መዝ. 150:6) ልባችን ዘወትር እንዲህ ለማድረግ የሚገፋፋን ከሆነ ስለ ይሖዋና ስለ ቃሉ ለመናገር የሚያስችሉንን አጋጣሚዎች በየዕለቱ እንጠቀምባቸዋለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ