የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/95 ገጽ 4
  • ዓላማ ያላቸው ተመላልሶ መጠየቆች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዓላማ ያላቸው ተመላልሶ መጠየቆች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ተመላልሶ መጠየቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ያስችላል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ትርጉም ያላቸው ተመላልሶ መጠይቆችን በማድረግ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች እድገት እንዲያደርጉ ማነቃቃት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • መጽሔቶቻችንን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙባቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ደፋሮች ሁኑ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 10/95 ገጽ 4

ዓላማ ያላቸው ተመላልሶ መጠየቆች

1 ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግ የምታነጋግረው ሰው ባለፈው ጊዜ ስለተወያያችሁበት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ርዕስ ያለውን እውቀት የሚያዳብርለት ጥቅስ ለመጠቀም ጥረት ማድረግ አለብህ።

2 መጽሔት ላበረከትንላቸው ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግ አንዱ ግባችን የመጽሔት ደንበኛ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። እንደሚከተለው ያለ ቀላል አቀራረብ ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ ሊሆን ይችላል:-

◼ “ወደ ነፃነት ስለሚወስደው መንገድ የሚያብራራውን ባለፈው ጊዜ የተውኩልዎትን መጠበቂያ ግንብ አንብበው እንደተደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ። ዛሬ ደግሞ ‘ቅናት ሁሉ ስሕተት ነውን?’ የሚል ጥያቄ የያዘ ሌላ መጠበቂያ ግንብ ይዤልዎት መጥቻለሁ። ይህ ጥሩ ጥያቄ አይደለም እንዴ? እባክዎን ይህንን መጽሔት ይውሰዱና በአምላክ ቃል ውስጥ የቀረበውን ጥሩ ማብራሪያ ይመርምሩ።” የሚቀጥሉትን እትሞች ለማምጣትና አምላክ ታዛዥ ለሆኑ የሰው ልጆች ምን አደርግላቸዋለሁ ብሎ ቃል እንደገባ ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ ተመልሰህ እንደምትመጣ ንገረው። መጽሔቶች ይዘህለት በሄድክ ቁጥር አንድ ተመላልሶ መጠየቅ መመዝገብ እንደምትችል አትርሳ።

3 “ጦርነት የማይኖርበት ዓለም የሚመጣው መቼ ነው?” የሚለውን እትም አበርክተህ ከነበረ እንዲህ ማለት ትችላለህ:-

◼ “ጦርነት ባይኖር ኖሮ በዚህ ምድር ላይ ያለው ሕይወት ምን ይመስል ነበር? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አምላክ ምን ለማድረግ ቃል እንደገባ ላሳይዎ።” መዝሙር 37:10, 11⁠ን አንብብና የአምላክ ፈቃድ በምድር ሲሆን ነገሮች ምን መልክ እንደሚኖራቸው ግለጽለት። ኢየሱስ በማቴዎስ 6:9, 10 ላይ እንደተመዘገበው ደቀ መዛሙርቱን ምን ብለው እንዲጸልዩ እንዳስተማራቸው አስታውሰው። ኢየሱስ የተናገራቸው ቃላት ባላቸው ትርጉም ላይ ጠለቅ ብሎ እንዲያስብ እርዳው። ልባዊ ፍላጎት ካሳየ መጠበቂያ ግንብ ኮንትራት እንዲገባ ሐሳብ ማቅረብና ሌላ ጊዜ ተመልሰህ ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ መያዝ ትችላለህ።

4 “ኤድስ በአፍሪካ” በሚል ርዕስ የወጣው ንቁ! ተበርክቶ ከነበረና በዚያው መስመር ውይይቱን ለመቀጠል ከተፈለገ እንደሚከተለው በማለት መጀመር ይቻላል:-

◼ “ባለፈው የመጣሁ ጊዜ በአፍሪካ ስለሚታየው የኤድስ መስፋፋት ተነጋግረን ነበር። መጽሔቱን በማንበብ እንደተገነዘቡት ኤድስ እጅግ አስደንጋጭ በሆነ መንገድ በመስፋፋት ላይ ይገኛል። በዚሁ ከቀጠለ አንዳንድ አካባቢዎች ሰው አልባ እንዳይሆኑ ያስፈራል መባሉን ሳያስተውሉት አልቀሩም። ታዲያ ስለ ኤድስ ማቆሚያ መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ የሚሰጥ ይመስልዎታልን? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አምላክ ለሰው ልጆች ወደፊት ጥሩ ነገር ለማምጣት ያሰበ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጽልናል።” ቀጥለህ ዮሐንስ 17:3⁠ን አንብብና ከአምላክ የሚገኝ እውቀት እንዴት ወደ ዘላለም ሕይወት እንደሚመራ አብራራ። ከዚያም ቋሚ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስለመጀመር ልታነሳለት ወይም ለሌላ ውይይት ቀጠሮ መያዝ ትችላለህ።

5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር በአገልግሎታችን ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ግቦች አንዱ ነው። ምናልባት መጽሔት ለሚወስድ ሰው ብዙ ተመላልሶ መጠየቅ አድርገህ ሊሆን ይችላል። በሚቀጥለው ጊዜ ስትሄድ የሚከተለውን አቀራረብ ለምን አትሞክርም?:-

◼ “ሰዎች ስለ ሃይማኖትና ሃይማኖት በአሁኑ ዘመናዊ ሕይወት ውስጥ ስላለው ዋጋ ብዛት ያላቸው የተለያዩ አስተሳሰቦች አሏቸው። አምላክ ክፋትን ስለ ፈቀደበት ምክንያት ወይም ስለምናረጅበትና ስለምንሞትበት ምክንያት እርስ በርሳቸው የሚጋጩ እምነቶች አሉ። አንዳንድ ሰዎች እንዴት መጸለይ እንዳለባቸውና አምላክ ጸሎታቸውን እንዲሰማ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለማወቅ ይፈልጋሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ ለማስጠናት ከምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በአንዱ ውስጥ የሚገኝ፣ የምታነጋግረውን ሰው ትኩረት ይስባል ብለህ የምታስበውን ርዕስ አውጣና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት እንደሚካሄድ በአጭሩ አሳየው።

6 ይሖዋ ዓላማ ያለው አምላክ ነው። በጥቅምት ወር ዓላማ ያላቸው ተመላልሶ መጠየቆች በማድረግ እርሱን እንምሰለው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ