የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች
ጥቅምት 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 175
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂ ያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ይሖዋን ዘወትር አወድሱት” በጥያቄና መልስ። የተጠቀሱትን ጥቅሶች፣ ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሰውን ጭምር ለምን እንደተጠቀሱ አብራራ። (ከመስከረም የመአ ላይ የሚወሰድ።)
20 ደቂቃ፦ “መጽሔቶችን በማንኛውም አጋጣሚ አበርክቱ።” ዋና ዋና ነጥቦቹን አብራራና በቅርብ የወጡ እትሞችን ለማበርከት የሚያገለግሉ ርዕሶችን ግለጽ። ሁለት ወይም ሦስት አቀራረቦችን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
መዝሙር 13 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 174
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። ወይም በሐምሌ 15, 1995 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 25–7 ላይ በሚገኘው “ውገዳ ፍቅራዊ ዝግጅት ነውን?” በሚለው ርዕስ ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ፦ “ማዘናጊያዎችን በማስወገድ ነቅተን እየኖርን ነውን?” ጥያቄና መልስ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ከግንቦት 1, 1992 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20–2 ላይ ተጨማሪ ሐሳቦችን አቅርብ።
መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 33
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ “የአውራጃ ስብሰባው ቀስቃሽ ጥሪ አቅርቧል!— ዕለት ዕለት ይሖዋን በደስታ አወድሱ!” ጥያቄና መልስ።
20 ደቂቃ፦ “ዓላማ ያላቸው ተመላልሶ መጠየቆች።” ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግ የሚኖሩንን ግቦች አብራራ። ብቃት ያላቸው አስፋፊዎች ሁለት የተለያዩ አቀራረቦችን በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አመቻች። ይህ ሥራ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው እንዴት እንደሆነ አንድ አስፋፊ እንዲናገር አድርግ።
መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 155
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች። “አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም።”
15 ደቂቃ፦ “ጉባኤ ያስፈልገናል።” በጥያቄና መልስ።
20 ደቂቃ፦ ሰዎች ለድርጅቱ አድናቆት እንዲያድርባቸው አድርጉ። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች በተባለው ብሮሹር አማካኝነት ከሁለት ወይም ከሦስት አስፋፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋል። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ድርጅቱ የሚሠራው እንዴት እንደሆነ፣ የተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ ሥርዓት ባለው ሁኔታ የተደራጁት እንዴት እንደሆነና እነርሱ በዚህ እንቅስቃሴ እንዴት መካፈል እንደሚችሉ እንዲያውቁ ማድረጉ ጠቃሚ የሆነው ለምን እንደሆነ ግለጽ። ገጽ 14 እና 15 ላይ በሚገኘው “ለፍቅርና ለመልካም ሥራ የሚያነቃቁ ስብሰባዎች” በሚለው ርዕስ ሥር ያሉትን ነጥቦች ከልስ። አስፋፊዎቹ አንድ ፍላጎት ያሳየ ሰው በስብሰባ ላይ የመገኘትን አስፈላጊነት እንዲገነዘብ ለመርዳት በተመላልሶ መጠየቅ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወቅት ከሚደረገው ውይይት ጎን ይህንን ትምህርት አብሮ ማቅረብ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ ያቅርቡ። ለሚቀጥለው ሳምንት ፕሮግራም ሁሉም የየካቲት 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ ይዘው እንዲመጡ አሳስባቸው።
መዝሙር 79 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 204
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በኅዳር ወር “የቤተሰብ ኑሮ” እና/ወይም “ወጣትነትህ” የተባሉትን መጽሐፎች በማበርከቱ ሥራ እንዲካፈሉ አበረታታ። ጉባኤው በሰኔ ወር ያበረከታቸውን መጽሐፎች ብዛት መግለጽ ትችላለህ። በመስከረም 95 መአ ገጽ 7 ላይ የሰኔ የአገልግሎት ሪፖርት በሚለው ሥር የተሰጠውን ሐሳብ ጥቀስ።
15 ደቂቃ፦ በጥናቶች አማካኝነት ጥናት ለማግኘት ሞክረሃልን? ንግግር። አንዳንድ አስፋፊዎች በሚከተለው መንገድ አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አስጀምረዋል:- አንድን ፍላጎት ያሳየ ሰው ለጥቂት ጊዜ ካስጠኑ በኋላ ከጓደኞቹ፣ ከዘመዶቹ ወይም ከሚያውቃቸው ሰዎች መካከል መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት የሚፈልግ ሰው እንዳለ ይጠይቁታል። አብዛኛውን ጊዜ ሰውዬው በርከት ያሉ ስሞችን ይጠቅሳል። እነዚህን ሰዎች ስታነጋግር የእርሱን ስም መጥቀስ ትችል እንደሆነ ጠይቀው። ሰዎቹን ስታነጋግር እንዲህ ማለት ትችላለህ:- “እከሌ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ በጣም አስደስቶታል፤ እርስዎም ሰዎችን ያለክፍያ በምናስጠናበት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራም መጠቀም እንደሚፈልጉ ተሰምቶታል።” ይህ ፍሬያማ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች የሚሆኑ ብዙ ተመላልሶ መጠይቆች ሊያስገኝ ይችላል። በዚህ መንገድ ፍላጎት ያላቸው ሰዎችን ያገኙ ወይም አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ያስጀመሩ የሁለት ወይም የሦስት አስፋፊዎችን ተሞክሮ ጨምረህ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “ጥፋቱ የማን ነው?” በመግ 2/1 95 ላይ የተመሠረተ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት።
መዝሙር 6 እና የመደምደሚያ ጸሎት።