ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች በጥቅምት:- ንቁ! እና መጠበቂያ ግንብ። የመጽሔቶቹን ቅጂዎች ለማበርከት ልዩ ጥረት አድርጉ። ልባዊ ፍላጎት ካሳዩ በተመላልሶ መጠየቅ ጊዜ ኮንትራት እንዲገቡ ሐሳብ ማቅረብ ይቻላል። ኅዳር፦ የቤተሰብ ኑሮ እና/ወይም ወጣትነትህ የተባሉት መጽሐፎች እያንዳንዳቸው በ3 ብር ይበረከታሉ። ታኅሣሥ፦ ለዘላለም መኖር የተባለው መጽሐፍ ይበረከታል፤ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ማስጀመርን ግብ በማድረግ የተበረከተላቸውን ሰዎች ሁሉ ተከታትሎ ለመርዳት ልዩ ጥረት ይደረጋል። ጥር፦ ከ1982 በፊት የታተመ በጉባኤው እጅ የሚገኝ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ይበረከታል። እነዚህ መጽሐፎች የሌሏቸው ጉባኤዎች ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተዘረዘሩትን የዘመቻ ጽሑፎች እስካሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14–AM) መጠየቅ ይችላሉ። በጥር የሚበረከቱት ከ1982 በፊት የታተሙ ጽሑፎች ብሩክሊን አይገኙም።
◼ የዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን እትም አባሪ “የ1996 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ሲሆን በ1996 ዓመቱን ሙሉ ልንጠቀምበት ይገባል።
◼ ጉባኤዎች ከጥቅምት የጽሑፍ ትእዛዛቸው ጋር ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር— 1996 የተባለውን ቡክሌት ማዘዝ መጀመር አለባቸው። ቡክሌቱ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛና በትግርኛ ይኖራል። ቡክሌቱ መጥቶ እስከሚላክ ድረስ በጉባኤው የተላኩ ጽሑፎች ዝርዝር (ፓኪንግ ሊስት) ላይ “በቅርቡ የሚደርስ” ተብሎ ይሰፍራል። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር የተባለው ቡክሌት በልዩ ትእዛዝ የሚገኝ ጽሑፍ ነው።