የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/95 ገጽ 3
  • ጉባኤ ያስፈልገናል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጉባኤ ያስፈልገናል
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጉባኤው ይሖዋን ያወድሰው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ጉባኤው እየተጠናከረ ይሂድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • በይሖዋ ጉባኤ ውስጥ ቦታ አለህ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • በጉባኤ ውስጥ ያላችሁን ድርሻ ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 10/95 ገጽ 3

ጉባኤ ያስፈልገናል

1 አንድ ጊዜ የቆሬ ልጆች ለይሖዋ ጉባኤ ያላቸውን አድናቆት እንዲህ በማለት ገልጸዋል:- “በሌላ ስፍራ አንድ ሺ ቀን ከመቆየት፣ በመቅደስህ አንድ ቀን መዋል የተሻለ ነው።” (መዝ. 84:10 የ1980 ትርጉም) ዓለም ከይሖዋ ጉባኤ ጋር የሚወዳደር ምንም ነገር ሊያቀርብላቸው አይችልም። እንደዚህ እንዲሰማህ ከፈለግህ ጉባኤ የሕይወትህ ዋንኛ ክፍል እንዲሆን ማድረግ አለብህ።

2 የክርስቲያን ጉባኤ ገና ከጅምሩ ይሖዋ እንደባረከው ታይቷል። (ሥራ 16:4, 5) ማናችንም ብንሆን ለጉባኤ የአመስጋኝነት መንፈስ ማጣት ወይም በአካል የሚያገናኘን ብቻ እንደሆነ አድርገን መውሰድ የለብንም። ጉባኤ በማንኛውም ማኅበረሰብ ውስጥ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች ማበረታቻ የሚያገኙበት ቦታ ነው። ከይሖዋ የተማርንና ለመንግሥቱ ሥራዎች የተደራጀን ለመሆን የሚያስችለንን አንድነት ያስገኝልናል።— ኢሳ. 2:2

3 የክርስቲያን ጉባኤ እውነትን የምንማርበት ዋና መንገድ ነው። (1 ጢሞ. 3:15) የኢየሱስ ተከታዮች ከአምላክ፣ ከክርስቶስ ጋርና እርስ በርሳቸው በመተሳሰር “አንድ” መሆን አለባቸው። (ዮሐ. 17:20, 21፤ ከኢሳይያስ 54:13 ጋር አወዳድር።) ወደ የትኛውም የዓለም ክፍል ብንሄድ ወንድሞቻችን በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችና መሠረታዊ ሥርዓቶች ከማመናቸውም በላይ ከእነርሱ ጋር ተስማምተው ይኖራሉ።

4 ደቀ መዛሙርት የማድረግ ሥራችንን ለማከናወን የሚያስችል ሥልጠናና ትጥቅ አግኝተናል። መጠበቂያ ግንብ፣ ንቁ! እና የመንግሥት አገልግሎታችን ቅዱስ ጽሑፋዊ ውይይት ለመጀመር የሚረዱ ጠቃሚ ሐሳቦች በየወሩ ያቀርቡልናል። ስብሰባዎቹ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች እንዴት ማግኘትና ፍላጎታቸውን ማዳበር እንደምንችል ሊያሳዩን ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። በዓለም ዙሪያ የምንመለከተው እድገት በዚህ ሥራ ሰማያዊ ድጋፍ እንዳለን ያሳያል።— ማቴ. 28:18–20

5 በጉባኤዎች አማካኝነት ‘ለፍቅርና ለመልካም ሥራ የሚያነቃቁን’ ዕለታዊ ማበረታቻዎች እናገኛለን። (ዕብ. 10:24, 25) የሚደርሱብንን ፈተናዎች በታማኝነት እንድንወጣ የሚያስችሉ ማበረታቻዎች ይሰጡናል። አፍቃሪ የበላይ ተመልካቾች የሚደርሱብንን ተጽዕኖዎችና ጭንቀቶች እንድንወጣ ይረዱናል። (መክ. 4:9–12) መንገዳችንን የመሳት አደጋ ሲያጋጥመን አስፈላጊ ምክር ይሰጠናል። እንዲህ ያለ ፍቅር የተሞላበት እንክብክቤ የሚያደርግ ሌላ ድርጅት ይገኛልን?— 1 ተሰ. 5:14

6 ይሖዋ ከድርጅቱ ጋር በመቀራረብ አንድነታችንን ጠብቀን እንድንኖር ይፈልጋል። (ዮሐ. 10:16) ማኅበሩ ከታማኝና ልባም ባሪያ ክፍል ጋር ያለንን ግንኙነት ጠብቀን እንድንቀጥል የሚረዳበት አንዱ መንገድ ማበረታቻ እንድናገኝ ተጓዥ የበላይ ተመልካቾችን በመላክ ነው። ፍቅር ለተሞላበት መመሪያ የምንሰጠው ቀና ምላሽ በመንፈሳዊ ጠንካራ ሆነን ለመቀጠል የሚረዳን የቅርብ ትስስር ያስገኝልናል።

7 በመንፈሳዊ ሕያው ሆነን ለመቀጠል ጉባኤ በጣም አስፈላጊ ነው። ከጉባኤ ተለይተን ተቀባይነት ባለው መንገድ ይሖዋን ማገልገል ዘበት ነው። ስለዚህ ይሖዋ ካዘጋጀልን ዝግጅት ጋር ተቀራርበን እንቀጥል። ጉባኤው ካሉት ግቦች ጋር ተስማምተን የምንሠራና በጉባኤ የሚሰጠንን ምክር ከልባችን በተግባር የምናውል እንሁን። ጉባኤን ምን ያህል ከፍ አድርገን እንደምንመለከት ማሳየት የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።— መዝ. 27:4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ