የኅዳር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ኅዳር 6 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “አዲሱ መጽሐፍ አምላክ የሚሰጠውን እውቀት ጎላ አድርጎ ይገልጻል።” በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት። ሁሉም መጽሐፉን በመስክ አገልግሎት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም እንዲችሉ ከመጽሐፉ ይዘት ጋር ሙሉ በሙሉ እንዲተዋወቁ አበረታታቸው።
20 ደቂቃ፦ “አዳዲስ አስፋፊዎችን መርዳት።” በሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 97–102 ላይ የተመሠረተ ውይይት።
መዝሙር 10 እና የመደምደሚያ ጸሎት
ኅዳር 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 33
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ “በስብሰባ ላይ አዘውትሮ መገኘት ጸንቶ ለመኖር የግድ አስፈላጊ ነው።” ንግግርና ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት።
20 ደቂቃ፦ “ለምሥራቹ የሚገባ ጠባይ አሳዩ።” ጥያቄና መልስ። ከ12–110 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16–18 አንቀጽ 5–9 የተወሰዱ ተጨማሪ ነጥቦች አቅርብ።
መዝሙር 53 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 180
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። (ወይም በሰኔ 15, 1994 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8–11 ላይ የተመሠረተ “በግል ጥናት ትደሰታለህን?” የሚል ንግግር አቅርብ።)
20 ደቂቃ፦ “ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ዋጋማነት እንዲገነዘቡ እርዷቸው።” አንድ ሽማግሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመርን ግብ በማድረግ ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ ያለብን ለምን እንደሆነ ከሁለት ወይም ከሦስት አስፋፊዎች ጋር ወይይት ያደርጋል። ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ የተሰጡትን አቀራረቦች ከልስና ሲለማመዱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 222
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 94–97 ላይ ያሉትን (“ለውጤታማ ምሥክርነት . . .” እና “በቡድን ሆኖ መመሥከር” የሚሉትን ንዑስ ርዕሶች) ፍሬ ነገሮች ባጭሩ አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ “በላይ ያለውን አስቡ።” ጥያቄና መልስ።
15 ደቂቃ፦ “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ ለማስተማር ይጠቅማል።” ጥሩ ችሎታ ያለው አስፋፊ አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ አቀራረቦች በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ። በታኅሣሥ ወር ሁሉም ለዘላለም መኖር በተባለው መጽሐፍ ጥሩ አድርገው እንዲጠቀሙ አበረታታ።
መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።