የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/96 ገጽ 4
  • እንዲያስተውሉ እርዷቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እንዲያስተውሉ እርዷቸው
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጥድፊያ ስሜት ምስራቹን ማቅረብ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • እንዴት ብለህ ትመልሳለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • የራእይ መጽሐፍ የእውነተኛ ደስታ ቁልፍ ነው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ከአምላክ የሚገኘው እውቀት ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 2/96 ገጽ 4

እንዲያስተውሉ እርዷቸው

1 ሐዋርያው ጴጥሮስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ነገሮች ‘ለማስተዋል እንደሚያስቸግሩ’ ተናግሯል። (2 ጴጥ. 3:16) ብዙ ሰዎች በራእይ መጽሐፍ ውስጥ እንዳሉት የመሳሰሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ምን ትርጉም እንዳላቸው አያውቁም ወይም በጣም አንገብጋቢ ለሆኑ ጥያቄዎች መልስ አላገኙም። መጽሐፍ ቅዱስንና ጽሑፎቻችንን ጥሩ አድርገን ከተጠቀምንባቸው እነዚህን ሰዎች በሚገባ መርዳት እንችላለን።

2 እንደሚከተለው በማለት ጥናት ማስጀመር ትችላለህ:-

◼ “ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችዎ መልስ ማግኘት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ላሳይዎ ፈልጌ ስለነበር ዛሬ እንደገና በመገናኘታችን ደስ ብሎኛል። ብዙ ሰዎች በዚህ መጽሐፍ በመታገዝ ለጥያቄዎቻቸው መልስ አግኝተዋል።” ዘላለም መኖር ወይም እውቀት የተባለውን መጽሐፍ የርዕስ ማውጫ አውጣና “ከዚህ ውስጥ ይበልጥ ማወቅ የሚፈልጉት ስለ የትኛው ርዕሰ ጉዳይ ነው?” ብለህ ጠይቀው። መልስ እንዲሰጥ ከፈቀድክለት በኋላ የመረጠውን ምዕራፍ አውጥተህ የመጀመሪያውን አንቀጽ አንብብ። በገጹ መጨረሻ ላይ ያሉት ጥያቄዎች በዋና ዋናዎቹ ነጥቦች ላይ ለማተኮር የሚያገለግሉት እንዴት እንደሆነ ንገረውና በአንድ ወይም በሁለት ተጨማሪ አንቀጾች ላይ በማወያየት አሳየው። ከዚያም ሌላ ጊዜ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዝ።

3 በአንድ ሥዕል ተጠቅመህ የአምላክ መንግሥት መከራን የሚያስወግደው እንዴት እንደሆነ አሳይተኸው ከነበረ ያንኑ ሥዕል አውጥተህ እንዲህ ማለት ትችላለህ:-

◼ “የአምላክ መንግሥት የምታመጣቸውን በዚህ ሥዕል ላይ የተገለጹትን በረከቶች በተመለከተ ያደረግነውን ውይይት እንደሚያስታውሱት ተስፋ እናደርጋለን። በዚህ መንግሥት ውስጥ ለመኖር ከፈለግን ምን ማድረግ ያለብን ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ልንከተለው የሚገባ ግሩም ምሳሌ ትተውልናል።” ‘ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ የመመርመርን’ አስፈላጊነት ጠበቅ በማድረግ ሥራ 17:11⁠ን አንብብ። ልበ ቅን ሰዎች የአምላክን ቃል እንዲያጠኑና በተሻለ ሁኔታ እንዲያስተውሉ የይሖዋ ምሥክሮች በመርዳት ላይ እንደሆኑ ንገረው።

4 በመጀመሪያው ቀን ስትገናኙ በራእይ 1:3 ላይ ተወያይታችሁ ከነበረ የሚከተለው ሐሳብ ፍላጎታቸውን እንደገና ሊቀሰቅስ ይችላል:-

◼ “የራእይን መጽሐፍ ማስተዋል ደስታ የሚያስገኘው እንዴት እንደሆነ ባለፈው ጊዜ ተወያይተን ነበር። ቢሆንም ይህ ደስታ እንዲሁ አይመጣም። ይህንን ደስታ ለማግኘት ቢያንስ ሁለት ነገሮች ይፈለጉብናል:- መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትና ያወቅነውን በሥራ ላይ ማዋል አለብን።” ያዕቆብ 1:25⁠ን አንብብና ሐሳብ ስጥበት። ገጽ 8 አንቀጽ 9⁠ን አውጣና በራእይ መጽሐፍ ላይ ያለውን ማስተዋላችን ገነት በምትሆነው በአዲሲቱ ዓለም ውስጥ ደስታ ማግኘት የምንችልበትን መንገድ እንድናውቅ የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ተናገር።

5 “በደስታ ኑር!” በተባለው ብሮሹር ጥናት ለማስጀመር የሚከተለውን አቀራረብ መጠቀም ትችላለህ:-

◼ “ባለፈው ጊዜ እየጨመሩ ስለመጡት በሕይወት ውስጥ ስለሚያጋጥሙ ችግሮች አስደሳች ውይይት ካደረግን በኋላ እንደገና በመገናኘታችን ደስ ብሎኛል። ዛሬ ደግሞ ከተነጋገርንበት ነገር ጋር የሚስማማ አንድ ሥዕል ላሳይዎ እፈልጋለሁ።” መጀመሪያ ሥዕል 19⁠ን አሳየው፤ ከዚያም ሥዕል 20 እና 21⁠ን አሳየው። የቤቱ ባለቤት አስቀድሞ በሚያውቀው ነገር ላይ መሠረት በማድረግ አምላክ ክፉ ሰዎችን የሚያጠፋው ለምን እንደሆነ ንገረው። ከዚያም ሥዕል ቁጥር 22-24⁠ን እና 28⁠ን በመጠቀም ባለንበት ዓለም ውስጥ ያለውን ሁኔታ ግለጽ። የምታነጋግረው ሰው ያለው ጊዜ አጭር ከሆነ የተጠቀሱትን ጥቅሶች አብራችሁ እንድታነቧቸው ሌላ ቀጠሮ ያዝ። በሚቀጥለው ጊዜ ከተገናኛችሁ በኋላ ብሮሹሩን ከመጀመሪያ ጀምሮ እንዲያጠና ሐሳብ ማቅረብ ትችላለህ።

6 ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ካገኘህ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት ወይም ለዘላለም መኖር በተባሉት መጻሕፍት ወይም በደስታ ኑር! አለዚያም አምላክ ስለ እኛ ያስባልን? በተባሉት ብሮሹሮች ላይ እንዲያተኩሩ በማድረግ እነዚህን ጽሑፎች ጥናት ለማስጀመር ተጠቀምባቸው። “ሕፃናትን [“ተሞክሮ የሌላቸውን፣” አዓት] አስተዋይ” እንዲሆኑ በመርዳት ከፍተኛ ደስታ ታገኛለህ።— መዝ. 119:130

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ