የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/97 ገጽ 2-9
  • አቅኚ የሆኑት ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አቅኚ የሆኑት ለምንድን ነው?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአቅኚነት አገልግሎት የሚያስገኛቸው በረከቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • አቅኚዎች በረከትን ይሰጣሉ፤ መልሰውም በረከት ያገኛሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ለመስበክ ጊዜው አሁን ነው!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • “ጥሩ አቅኚ ሊወጣህ ይችላል!”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 4/97 ገጽ 2-9

አቅኚ የሆኑት ለምንድን ነው?

1 ክርስቶስ ‘የአምላክ ቤት ቅንዓት እንደሚበላው’ አስቀድሞ በትንቢት ተነግሮ ነበር። (መዝ. 69:​9) ኢየሱስ ለይሖዋ እውነተኛ አምልኮ የነበረው ቅንዓት አገልግሎቱን በአንደኛ ቦታ እንዲያስቀምጥ ገፋፍቶታል። (ሉቃስ 4:​43፤ ዮሐ. 18:​37) እንዲህ ያለው ለእውነት በቅንዓት የመመስከር ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች በሚያከናውኑት አገልግሎት ላይ ግልጽ ሆኖ ይታያል። ባለፈው የአገልግሎት ዓመት በዓለም ዙሪያ በአማካይ 645, 509 የሚሆኑ ሰዎች በእያንዳንዱ ወር በአንዱ ዓይነት የአቅኚነት አገልግሎት ተካፍለዋል። ራሳችንን ለአምላክ ስንወስን እያንዳንዳችን ረዳት ወይም የዘወትር አቅኚ ሆነን ለማገልገል ሁኔታዎቻችንን ማስተካከል እንችል እንደሆነ በጸሎት ማሰብ ይኖርብናል።​— መዝ. 110:​3 NW፤ መክ. 12:​1፤ ሮሜ 12:​1

2 የምንኖረው ራስ ወዳድ በሆነና ፍቅረ ነዋይ በተጠናወተው ሥርዓት ውስጥ ነው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ብዙ ሰዎች አንድ ሰው ምንም ዓይነት የገንዘብ ጥቅም ወይም ክብር በማያስገኘው አገልግሎት በትጋት የሚሠራው ለምን እንደሆነ ለመረዳት አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል። አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉት ለምንድን ነው? አቅኚዎች ሕይወት አድን በሆነ ሥራ ላይ እንደተሰማሩ ያውቃሉ። ለይሖዋና ለሰው ባላቸው የጠለቀ ፍቅር ተገፋፍተው ሕይወት አድን በሆነው ሥራ የመካፈል ከፍተኛ የሞራል ግዴታ እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። (ሮሜ 1:​14-16፤ 1 ጢ⁠ሞ. 2:​4፤ 4:​16) አንድ አቅኚ ባልና ሚስት “አቅኚ ሆነን የምናገለግለው ለምንድን ነው? አቅኚ ባንሆን ኖሮ አቅኚ ያልሆንበትን ምክንያት ለይሖዋ ማቅረብ እንችላለን?” በማለት ሁኔታውን ጠቅለል ባለ መንገድ አስቀምጠውታል።

3 ሌላ እህት አቅኚነት ለመጀመር የወሰነችበትን ምክንያት ስትገልጽ እንዲህ ብላ ጽፋለች:- “ባለቤቴና እኔ የግድ አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮችን ለመተውና በአንድ ገቢ ብቻ ለመተዳደር እቅድ አወጣን። ይሖዋ አብዝቶ ስለባረከን እንድንደኸይ ወይም እንድንቸገር ፈጽሞ አልተወንም። . . . የምኖረው ለምን እንደሆነ ትክክለኛውን ምክንያት አግኝቻለሁ። ይህም በመንፈሳዊ የተቸገሩ ሰዎች እውነተኛ አምላክ የሆነው ይሖዋ ከሚፈልጉት ሰዎች ሩቅ እንዳልሆነ እንዲያውቁ መርዳት ነው።” የጊዜውን አጣዳፊነት በመመልከት አቅኚዎች ለዘላለም የሚኖረውን መንፈሳዊ ውድ ሃብት ለማግኘት አጥብቀው በሚፈልጉበት ጊዜ ለሕይወት አስፈላጊ በሆኑ መሠረታዊ ነገሮች ብቻ ረክተው ይኖራሉ።​— 1 ጢ⁠ሞ. 6:​8, 18, 19

4 የግል ሁኔታዎችህ የሚፈቅዱልህ ከሆነ በዓለም ዙሪያ አቅኚ ሆነው በማገልገል ላይ ከሚገኙት በመቶ ሺህ ከሚቆጠሩ ወንድሞችና እህቶች ጋር አቅኚ ሆነህ ለምን አታገለግልም? በዚህ መንገድ እነርሱ ያገኙት ዓይነት ደስታ አንተም ልታገኝ ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ