የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/97 ገጽ 2-7
  • የሚያዝያ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሚያዝያ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሚያዝያ 7 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 14 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 21 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 28 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 4/97 ገጽ 2-7

የሚያዝያ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ሚያዝያ 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 13 (33)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በቅርቡ ከወጡ መጽሔቶች መካከል ውይይት ለመክፈት የሚረዱ አንዳንድ ሐሳቦችን ጥቀስ። በየዓመቱ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያሉት ወራት ያልተሠራባቸው የአገልግሎት ክልሎችን ለመሸፈን ጥረት የሚደረግባቸው ጊዜያት እንደሆኑ እባክህ ግለጽ። በመጋቢት ምን እንደተከናወነና ገና የሚከናወን ምን ነገር እንደቀረ የሚገልጽ ወቅታዊ መረጃዎችን አቅርብ።

15 ደቂቃ:- “ብዙ ሰዎች እየጎረፉ ነው።” ጥያቄና መልስ። በነሐሴ 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 12-17 ላይ ከቀረቡት ሐሳቦች መካከል ቁልፍ ነጥቦችን ከልስ።

18 ደቂቃ:- “ተሞክሮ የሌላቸውን እንዲያስተውሉ እርዷቸው።” ጥያቄና መልስ። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘው ብሮሹር ቀለል ያለ የማስጠኛ ዘዴ፣ ተስማሚ ጥያቄዎች፣ ማራኪ ሥዕሎችና በዛ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንዳሉት በመግለጽ የብሮሹሩን ይዘት ከልስ። ውሎ አድሮ እውቀት ወደ ተባለው መጽሐፍ ለማሸጋገር በዚህ ብሮሹር ጥናት የማስጀመር ግብ እንዲያወጡ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። አንቀጽ 4 ላይ የተዘረዘሩትን አቀራረቦች ተጠቅመው ጥሩ ችሎታ ያላቸው አስፋፊዎች ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። በጉባኤ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ብሮሹሩን እንዲያጠኑ አበረታታ።

መዝሙር 53 (130) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 46 (107)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር በማበርከት ወይም ይህን ብሮሹር ተጠቅሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በማስጀመር የተገኙ የጉባኤ የመስክ ተሞክሮዎችን በአጭሩ ተናገር።

15 ደቂቃ:- “ተማሪዎችን ከስማችን በስተጀርባ ወዳለው ድርጅት መምራት።” (ከአንቀጽ 1-6) ጥያቄና መልስ። ከአንቀጽ 5-6 እና በአንቀጾቹ ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች አንብብ። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የይሖዋ ምሥክሮች​—ከስሙ በስተጀርባ ያለው ድርጅት የተሰኘውን ቪዲዮ በማየታቸው የተሰማቸውን ስሜት የሚገልጽ ከጉባኤ የተገኙ ተሞክሮዎችን ተናገር።

20 ደቂቃ:- “አምላክ ምን እንደሚፈልግባቸው አስተምሯቸው።” ከአንቀጽ 1-4 ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በአንቀጽ 5 ላይ ተመሥርተህ በመንገድ ላይ፣ በቤት ውስጥ፣ በገበያና በመናፈሻ ቦታ ላይ የሚደረገውን ምሥክርነት የሚያሳዩ አራት የተለያዩ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በዚህ ምሽት ወደ ቤት ከመሄዳቸው በፊት ለመስክ አገልግሎት የሚሆኑ ብሮሹሮችንና መጽሔቶችን እንዲወስዱ አሳስባቸው።

መዝሙር 96 (215) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 48 (113)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በግንቦት ረዳት አቅኚ ለመሆን ማመልከቻ ለማስገባት ጊዜው አሁንም እንዳላለፈ ግለጽ። የጥያቄ ሣጥኑን ከልስና በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ የሚገኘውን ቤተ መጻሕፍት የተሟላ ለማድረግ አንዳንድ መጻሕፍት ያስፈልጉ እንደሆነ ለጉባኤው አሳውቅ።

15 ደቂቃ:- “ተማሪዎችን ከስማችን በስተጀርባ ወዳለው ድርጅት መምራት።” (ከአንቀጽ 7-14) ጥያቄና መልስ። በስብሰባዎች ላይ የመገኘትን አስፈላጊነት ከአንድ ተማሪ ጋር በደግነትና ግልጽ በሆነ መንገድ እንዴት ውይይት ማድረግ እንደሚቻል አንድ ጥሩ ችሎታ ያለው አስተማሪ በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።

18 ደቂቃ:- በጽሑፎቻችን ሙሉ በሙሉ መጠቀም። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ራእይ 9:​16-19ን አንብብና በዚህ ጥቅስ ፍጻሜ ውስጥ እኛ ያለንን ድርሻ (ራእይ መደምደሚያ ገጽ 151-153) እንዲሁም ጽሑፎቻችን የሚያበረክቱልንን እርዳታ ግለጽ። ክፉ ሰዎችን ለማስጠንቀቅና የሰላም መልእክተኞች እንደመሆናችን መጠን በሰይጣንና በአጋንንቱ ሥራዎች የሚተክዙና የሚያዝኑ ሰዎችን ለመርዳት የአገልግሎት ክልላችንን መሸፈን ያለብን እንዴት እንደሆነ ግለጽ። ብዙ ቅን ልቦና ያላቸው ሰዎች ከሃይማኖታዊ አስተማሪዎቻቸው የማያገኙትን የተሟላ መንፈሳዊ ምግብ ለማግኘትና የራሳቸው የሃይማኖት ተከታዮች እርስ በእርሳቸው በሚዋጉበት ጊዜ የክርስቶስ ተከታዮች ያላቸው ፍቅር የሚንጸባረቅበት ማኅበር ለማግኘት ይጓጓሉ። ከዚያም “መጽሔቶቻችንን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙባቸው” (የመንግሥት አገልግሎታችን 9/95 ከገጽ 3-5) ከሚለውና በጥቅምት 23, 1996 ለጉባኤዎች በሙሉ ከተጻፈው ደብዳቤ አንቀጽ 5 ላይ ያሉትን ሐሳቦች ተጠቀም። በጉባኤያችሁ ምን ያህል የመጽሔት ክምችት እንዳለና የቆዩ እትሞችን ለማበርከት ምን ጥረት እንደሚደረግ ለጉባኤው ግለጽ። የቆዩ እትሞች ጥቅም እንደሌሏቸው አድርጋችሁ አትመልከቷቸው። መጽሔት ለማበርከት በሚደረገው አገልግሎት አዘውትራችሁ ተካፈሉ። ያልተሠራባቸው የአገልግሎት ክልሎችን ለመሸፈን ቅድሚያ ስጡ። ለሦስት ወር በሚደረገው ዘመቻ ለዘላለም መኖር የተሰኘውን መጽሐፍ በቅናሽ ዋጋ እንደምናበረክት ለመግለጽ የመደምደሚያ ደቂቃ ተጠቀም። በየወሩ ቢያንስ አንድ መጽሐፍ ለማበርከት ለራሳቸው ግብ እንዲያወጡ ሁሉንም አበረታታ። ይህ መጽሐፍ በጉባኤ ውስጥ ምን ያህል እንዳለ አስታውቅና በሐምሌ መጨረሻ ላይ ሁሉም ቢያንስ ሦስት መጽሐፍ ማበርከት እንዲችሉ ምን ያህል መጽሐፍ መታዘዝ እንዳለበት አስላ። ይህን መጽሐፍ ለማበርከት በታኅሣሥ 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 10 ላይ የወጣውን ሐሳብ በአጭሩ ጥቀስ። ከጊዜ በኋላ እውቀት ወደ ተሰኘው መጽሐፍ ለማሸጋገር አሁንም ቢሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በዚህ መጽሐፍ ማስጀመር እንደሚቻል አስታውስ።

መዝሙር 12 (32) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 85 (191)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የሚያዝያ የአገልግሎት ሪፖርት እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በግንቦት ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉትን ስም ዝርዝር አንብብ። ጉባኤው የመስክ አገልግሎት ስብሰባን በተመለከተ ያደረጋቸውን ተጨማሪ ዝግጅቶች ግለጽ። በግንቦት ጥናት የማስጀመርን ግብ በመያዝ ብሮሹር ለተበረከተላቸው ሰዎች ክትትል ለማድረግ ልዩ ጥረት ይደረጋል። መደበኛ ባልሆነ መንገድ የመሰከርንላቸውን ሰዎች ስምና አድራሻ በዘዴ መጠየቅ የምንችልባቸውን የተለያዩ መንገዶች በአጭሩ ግለጽ። በመጀመሪያ የእናንተን ስምና አድራሻ ልትነግሯቸው ትችላላችሁ፤ ከዚያም ልትገናኙ የምትችሉበትን ስልክ ቁጥር እንዲሰጣችሁ ጠይቁ። አድማጮች ውጤታማ ሆኖ ያገኙት ሌላ ሐሳብ ካላቸው እንዲናገሩ ጋብዛቸው።

15 ደቂቃ:- “አቅኚ የሆኑት ለምንድን ነው?” አንድ ሽማግሌ ከሁለት ወይም ከሦስት የዘወትር አቅኚዎች ጋር ውይይት በማድረግ ያቀርበዋል። (የዘወትር አቅኚ ከሌለ ብዙ ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆኖ ከሚያገለግል አስፋፊ ጋር አቅርብ።) በጥር 15, 1994 መጠበቂያ ግንብ ላይ “አቅኚዎች በረከትን ይሰጣሉ፤ መልሰውም በረከት ያገኛሉ” ከሚለው ርዕስ ጎላ ያሉ ነጥቦችን ጨምረህ አቅርብ። እርሷ ወይም እርሱ የአቅኚነትን አገልግሎት የጀመሩት ለምን እንደሆነ ሁለቱም እንዲናገሩ አድርግ። አቅኚ በመሆናቸው የተባረኩት እንዴት እንደሆነ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጠይቅ።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። ሽማግሌዎች ጉባኤው በሚያስፈልጉት ነገሮች ላይ በማተኮር ሐሳብ ወይም “እድገትህ በግልጽ እንዲታይ አድርግ” የሚለውን ክፍል ሊያቀርቡ ይችላሉ። (የመንግሥት አገልግሎታችን 12/95 ገጽ 2)

መዝሙር 52 (129) እና የመደምደሚያ ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ