የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች
ግንቦት 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር ቁጥር 53 (130)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሁሉም ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ እንዲወስዱና አመቺ በሆነ አጋጣሚ ሁሉ እንዲያበረክቱ አበረታታ።
12 ደቂቃ:- “ያለማቋረጥ ኢየሱስን ተከተሉ።” ጥያቄና መልስ። ሰኔ 1, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 12 ላይ ያሉትን ተሞክሮዎች ጨምረህ አቅርብ።
25 ደቂቃ:- “ፍላጎት ላላቸው ሁሉ ልባዊ አሳቢነት አሳዩ።” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ፍላጎት ያሳዩትን ሁሉ ተከታትሎ የመርዳትን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ተጨማሪ ምሥክርነት እንድንሰጣቸው በአደባባይ ላይ ያገኘናቸውን ሰዎች ስምና የሚኖሩበትን አድራሻ ለመጠየቅ የሚያስችሉ አንዳንድ ዘዴ የታከለባቸውን መንገዶች ጠቁም። ችሎታ ያላቸው ሁለት አስፋፊዎች ከአንቀጽ 6-9 ላይ ካሉት የመግቢያ ሐሳቦች መካከል በሁለቱ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። በመጋቢት 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ገጽ 3 ላይ “ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ረገድ ስኬታማ መሆን የሚቻልበት መንገድ” የሚለውን ሣጥን ከልስ። ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ በየሳምንቱ የተወሰነ ሰዓት እንዲመድቡ ሁሉንም አበረታታ።
መዝሙር 64 (151) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 55 (133)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ሁሉም ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ እንዲወስዱና አመቺ በሆነ አጋጣሚ ሁሉ እንዲያበረክቱ አበረታታ።
15 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን (የመጀመሪያውን ጥያቄ)። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ:- “እድገት የሚያደርጉ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን መምራት።” ጥናት በመምራት በኩል ከተሳካላቸው ሁለት አስፋፊዎች ጋር ብቃት ያለው ወንድም በውይይት ያቀርበዋል። እውቀት ከተባለው መጽሐፍ አንዳንድ ክፍሎችን እንደ ምሳሌ አድርገው በመውሰድ የማስተማር ዘዴዎችን ያብራራሉ።— የሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ አንቀጽ 5, 8, 12 እና 21ን ተመልከቱ።
መዝሙር 70 (162) እና የመደምደሚያ ጸሎት
ግንቦት 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 59 (139)
7 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ እንዲወስዱና አመቺ በሆነ አጋጣሚ ሁሉ እንዲያበረክቱ አበረታታ።
20 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። ጉባኤው በመንፈሳዊ የሚያስፈልጉትን ነገሮች አንድ ሽማግሌ በንግግር መልክ ያቅርብ ወይም ሁለት ሽማግሌዎች በውይይት መልክ ያቅርቡ። መሻሻል ለማድረግ የሚጠቅሙ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክሮችን ወይም ተግባራዊ ሐሳቦችን አቅርቡ።
18 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን (ሁለተኛውን ጥያቄ)። ሁሉንም ጥቅሶች አንብብ።
መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ንቦት 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 63 (148)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በሰኔ የሚበረከተውን ጽሑፍ ግለጽ። ሁሉም ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ እንዲወስዱና አመቺ በሆነ አጋጣሚ ሁሉ እንዲያበረክቱ አበረታታ። ተመላልሶ መጠየቅንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን አስመልክቶ በትክክል ሪፖርት ስለማድረግ ማሳሰቢያ ስጥ። ጥናት የማስጀመር ጥረት በማድረግ ላይ እንዲያተኩሩ ሁሉንም አበረታታ። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ፈጣን እድገት እንዲያደርጉ የመርዳትን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።— የጥር 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 13-14ን ተመልከት።
15 ደቂቃ:- “ያለማቋረጥ ተመልሰን የምንሄደው ለምንድን ነው?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አዋጅ ነጋሪዎች ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 570 ላይ ካለው ሣጥን ነጥቦችን ጨምረህ አቅርብ።
18 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን (የሰኔ 1997 የመንግሥት አገልግሎታችንን ተመልከት።)
ነመዝሙር 77 (174) እና የመደምደሚያ ጸሎት።