የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/97 ገጽ 2
  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ነሐሴ 4 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 11 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 18 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 25 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 8/97 ገጽ 2

የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ነሐሴ 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 83 (187)

7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የአገሪቱንና የጉባኤውን የግንቦት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት በሚመለከት ሐሳብ ስጥ። ብሮሹሮችን እንዲያበረክቱ አበረታታ።

13 ደቂቃ፦ “ስብሰባዎች ለመልካም ሥራ ያነቃቃሉ።” ጥያቄና መልስ። ከስብሰባዎች በፊትና በኋላ ገንቢ ጭውውቶችን ማድረግ ያለውን ጠቀሜታ ግለጽ።—የትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 82 አንቀጽ 17-18⁠ን ተመልከት።

25 ደቂቃ፦ “ይሖዋ እንደሚያሳድግ እምነት ይኑራችሁ።” ንግግርና ሠርቶ ማሳያዎች። ብሮሹር ለተበረከተላቸው ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ የማድረጉን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ብሮሹር ሲበረከት የሚያሳዩ ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በመጋቢት 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ አንቀጽ 7-11 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች አክለህ አቅርብ።

መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 11 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 22 (47)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ፦ “አረጋውያን መስበካቸውን አያቋርጡም።” ጥያቄና መልስ። በሐምሌ 1, 1988 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ገጽ 13 ላይ የሚገኘውን ረዳት አቅኚ ሆና ስላገለገለች አንዲት አረጋዊት የሚገልጸውን ተሞክሮ ጨምረህ አቅርብ።

20 ደቂቃ፦ “‘በአምላክ ቃል ማመን’ የ1997 የአውራጃ ስብሰባ” (ከሐምሌ የመንግሥት አገልግሎታችን)። ከአንቀጽ 10-17 ያለውን እንዲሁም “የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ተወያዩበት።

መዝሙር 19 (43) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 18 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53 (130)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

25 ደቂቃ፦ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር በመጠቀም ተመላልሶ መጠይቆችን አድርጉ። ጥያቄ አንስቶ መልሱን ለማግኘት ወደ ብሮሹሩ እንዴት ትኩረታቸውን ማዞር እንደሚቻል አሳይ። ለምሳሌ ያህል ብሮሹሩ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል:- ሙታን ተስፋ አላቸውን? (ገጽ 5-6) ማዘን ስህተት ነውን? (ገጽ 8-9) አንድ ሰው ሐዘኑን መቋቋም የሚችለው እንዴት ነው? (ገጽ 18) ሌሎች እንዴት መርዳት ይችላሉ? (ገጽ 20-3) ለልጆች ስለ ሞት እንዴት ማስረዳት ይቻላል? (ገጽ 25) መጽሐፍ ቅዱስ ምን ማጽናኛ ይሰጣል? (ገጽ 27)—ከዚያም ችሎታ ካላቸው ሁለት አስፋፊዎች ጋር በመሆን ብዙውን ጊዜ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ለመመለስ የአምላክ መንግሥት በተባለው ብሮሹር እንዴት እንደሚጠቀሙ ተወያዩ። ገጽ 22 ስለ “መጨረሻዎቹ ቀናት” ሥዕላዊ መግለጫ ይዟል፣ ገጽ 30 ስለ አምላክ መስፈርቶች ይገልጸል፣ እንዲሁም ገጽ 3 አንቀጽ 1፣ ገጽ 29 እና 31 ስለ መንግሥቱ በረከቶች ይናገራሉ። በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት በብሮሹሩ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 25 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 21 (46)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስብ።

15 ደቂቃ፦ “የትምህርት ቤት ሕይወታችሁን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት።” አንድ አባት ከልጆቹ ጋር በመሆን ከጥቅምት-ታኅሣሥ 1996 ንቁ! መጽሔት ገጽ 7-11 ላይ የሚገኙትን ሊረዱ የሚችሉ ነጥቦች ጨምሮ ክፍሉን በውይይት ያቀርበዋል።

20 ደቂቃ፦ በዓላማ ስበኩ። አንድ ሽማግሌና አንድ ወይም ሁለት የጉባኤ አገልጋዮች አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 8-12 ላይ ያለውን ነጥብ ይከልሳሉ። አገልግሎታችንን አስመልክቶ አዎንታዊ አመለካከት እንድንይዝና መሻሻል እያደረግን እንድንቀጥል እንዲሁም ከድርጅቱ ጋር ሁልጊዜ በቅርብ ተባብረን እንድንሠራ በሚያስገድዱን ምክንያቶች ላይ ትኩረት አድርግ።

መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ