ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ነጠላ ቅጂዎች። በተመላልሶ መጠየቅ ጊዜ ፍላጎት ላሳየ ሰው ኮንትራት እንዲገባ ሐሳብ ማቅረብ ይቻላል። ከጥቅምት 12 ጀምሮ የመንግሥት ዜና ቁ. 35 እናሰራጫለን። ኅዳር፦ የመንግሥት ዜና ቁ. 35ን ማሰራጨታችንን እንቀጥላለን። በእያንዳንዱ ቤት ወይም መኖሪያ ላሉ ሰዎች የመንግሥት ዜና ቁ. 35ን ቅጂ በማዳረስ ክልላቸውን የሸፈኑ ጉባኤዎች እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። ታኅሣሥ፦ ታላቁ ሰው (የእንግሊዝኛ) ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ መጽሐፌ። ጥር፦ በጉባኤ ያለ ማንኛውም ከ1985 በፊት የታተመ ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ። እነዚህ መጽሐፎች የሌሏቸው ጉባኤዎች በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለውን መጽሐፍ ሊያበረክቱ ይችላሉ።
◼ ይህ የመንግሥት አገልግሎታችን ካሉት አባሪዎች መካከል አንዱ “የ1998 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ሲሆን ዓመቱን ሙሉ ልንጠቀምበት እንድንችል በጥሩ ሁኔታ ልንይዘው ይገባል።
◼ አምስት ቅዳሜና እሑድ ያሉት የኅዳር ወር ለብዙዎች ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል አመቺ ጊዜ ሊሆንላቸው ይችላል።
◼ ለብዙ ጉባኤዎች የስብሰባ ሰዓታቸው ከጥር 1 ጀምሮ ይቀየራል። በዚህም ምክንያት የተደረገውን የመሰብሰቢያ ሰዓት ለውጥ ለማመልከት አዲስ የስብሰባ ጥሪ ወረቀቶች እንዲላክላችሁ ማዘዝ ያስፈልጋችሁ ይሆናል።
◼ ጉባኤዎች በጥቅምት ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ላይ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር-1998 ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። ቡክሌቶቹ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛና በትግርኛ ይገኛሉ። እነዚህ ቡክሌቶች በልዩ ትእዛዝ የሚገኙ ጽሑፎች ናቸው። እስኪላክላችሁ ድረስ በጉባኤያችሁ የጽሑፍ መላኪያ ዝርዝር ላይ “በቅርብ የሚደርስ” ተብሎ ይወጣል።
◼ ከጥር 1998 ጀምሮ የአማርኛው ንቁ! መጽሔት ወርኃዊ እትም ይሆናል። ስለዚህ ኮንትራት መግባትም ሆነ ማስገባት ይቻላል። በአንድ ዓመት ውስጥ የሚታተሙት ቅጂዎች ብዛት 12 ስለሆነ የኮንትራቱ ዋጋ በዚሁ መጠን ይሆናል።