የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች
ጥቅምት 6 የሚጀምር ሳምንት
ሙር 1 (3)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ሰዎች ሁሉ እርስ በእርሳቸው የሚዋደዱበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?” ጥያቄና መልስ። የመንግሥት ዜና ቁ. 35 የያዘውን ጎላ ያሉ ነጥቦች ከልስ። በክልላችን ውስጥ ያሉ ሰዎች ከዚህ ትራክት ጥቅም ሊያገኙ የሚችሉበትን ምክንያት አመልክት። ትራክቱን በማሰራጨት ሙሉ ተሳትፎ ለማድረግ ከአሁኑ እቅድ የማውጣትንና ፍላጎት ያሳዩትን ሁሉ ተከታትሎ በመርዳት ረገድ ትጉ የመሆንን አስፈላጊነት እባክህ ግለጽ።
20 ደቂቃ፦ “የመንግሥት ዜና ቁ. 35ን በስፋት አሰራጩ።” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ የመክፈቻ ንግግር። ከአንቀጽ 5-8 ያለውን በጥያቄና መልስ ሸፍን። ሰፊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ጉባኤው ያደረገውን ዝግጅት ግለጽ። ክልሎች ሙሉ በሙሉ መሸፈን የሚችሉባቸውን መንገዶች ተናገር። አስፋፊዎች በአውቶቡስ ማቆሚያ፣ በአነስተኛ የንግድ ቦታዎች፣ በመኪና ማቆሚያዎችና በሌሎችም ቦታዎች ለሚያገኟቸው ሰዎች በሚመሰክሩበት ጊዜ የመንግሥት ዜና ቁ. 35ን መጠቀም ይችላሉ። በስብከቱ ሥራ መካፈል ለመጀመር የሚፈልጉትን አዳዲሶች እንዴት መርዳት እንደሚቻል ሐሳብ አቅርብ። ሚያዝያ 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ አንቀጽ 11 ላይ ያለውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ። በአንዳንድ ክልሎች ውስጥ የመንግሥት ዜና በምናሰራጭበት ጊዜ ለብቻ ሆኖ ማገልገልና የአገልግሎት ቦርሳ አለመያዝ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ሁለት ወይም ሦስት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
መዝሙር 8 (21) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 35 (79)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በቅርብ ከወጡት የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! እትሞች የመነጋገሪያ ነጥቦች ጥቀስ። ቅዳሜና እሑድ በሚከናወነው የስብከት ሥራ ከመንግሥት ዜና ቁ. 35 ጋር በተጓዳኝነት መጽሔቶችም እንደሚበረከቱ አስታውሳቸው። ፍላጎት ያሳዩትን ሁሉ ተከታትለን መርዳት አለብን።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
18 ደቂቃ፦ “የሰዎች ግዴለሽነት በእናንተ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?” ሁለት ሽማግሌዎች በውይይት ያቀርቡታል። “የሰዎችን ግዴለሽነት ልትወጣ የምትችልበት ዘዴ” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር በሐምሌ 15, 1974 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 445-6 ከወጣው ትምህርት ተጨማሪ ሐሳቦችን አቅርብ።
መዝሙር 53 (130) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 18 (42)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “ዓለም አቀፍ የመንግሥት ዜና ስርጭት” በሚል ርዕስ በ1996 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 6-8 ላይ የወጡ አንዳንድ ተሞክሮዎችን አቅርብ። ባለፈው የመንግሥት ዜና ስርጭት ላይ አስፋፊዎች በግለሰብ ደረጃ ያደረጉትን ጥረት ጎላ አድርገህ ግለጽ። የመንግሥት ዜና ቁ. 35ን በማሰራጨቱ ሥራ ሁሉም ሙሉ በሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “መዋሸት በጣም ቀላል የሆነው ለምንድን ነው?” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። (መጠበቂያ ግንብ 92 12/15 21-23)
15 ደቂቃ፦ “የሙሉ ጊዜ ምሥክር ነህን?” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
መዝሙር 55 (133) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 19 (43)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የመንግሥት ዜና ቁ. 35 ስርጭት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ግለጽ። አድማጮች የሚያበረታቱ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ። እስካሁን ድረስ ምን ያህል ክልል እንደተሸፈነ ሪፖርት ካደረግህ በኋላ እስከ ኅዳር 16 ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ሪፖርት አቅርብ። የጉባኤውን ክልል አጣርተን ከሸፈንን በኋላ በቀሪው የወሩ ክፍል እውቀት የተባለውን መጽሐፍ እናበረክታለን። የመንግሥት ዜና ሲበረከትላቸው ጥሩ ምላሽ ያሳዩትን ተመልሰን በምንጠይቅበት ጊዜ ጥናት የማስጀመርን ግብ አጥብቀህ አሳስብ።
15 ደቂቃ፦ “ተስፋ አስቆራጭ በሆኑ ሁኔታዎች ሥር በተስፋ መኖር።” በግንቦት 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22-5 ላይ ተመስርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
18 ደቂቃ፦ ብርሃናችሁ ይብራ። ከአገልግሎታችን መጽሐፍ ገጽ 84-8 በንግግርና በውይይት የሚቀርብ። ቀጥሎ በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ የተወሰኑ ሐሳቦች እንዲሰጡ አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ:- (1) የይሖዋ ምሥክሮች ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ የሚሰብኩት ለምንድን ነው? (2) በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይህ ዘዴ ምን ያህል ተሠርቶበት ነበር? (3) በዛሬው ጊዜ ከቤት ወደ ቤት እየሄድን መስበክ መቀጠላችን አጣዳፊ ጉዳይ የሆነው ለምንድን ነው? (4) ከቤት ወደ ቤት አዘውትረን እንዳንሳተፍ ችግር የሚፈጥሩብን ሁኔታዎች ምንድን ናቸው? (5) ጸንተን ለመቀጠል እንድንችል እርዳታ እንዴት ማግኘት እንችላለን? (6) ብርሃናችን እንዲበራ በማድረጋችን ምን በረከት አግኝተናል? (7) ሰዎችን ቀርበን በማነጋገር ይበልጥ ስኬታማ እንድንሆን ምን ማድረግ እንችላለን? ከሱቅ ወደ ሱቅና በመንገድ ላይ ምስክርነት ሲሰጡ ያገኟቸውን አስደሳች ተሞክሮዎች ሦስት ወይም አራት አስፋፊዎች እንዲናገሩ በማድረግ ጉዳዩን አብራራ።
መዝሙር 57 (136) እና የመደምደሚያ ጸሎት።