ምንድን ነው የምለው?
ለምሥራቹ መልእክት ጥሩ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ስናገኝ ተጨማሪ ምስክርነት ለመስጠት ተመልሰን ለመሄድ እንጓጓለን። ሆኖም ተመልሰን በምንሄድበት ጊዜ ምን ብለን ውይይቱን መጀመር እንደምንችል ግራ ይገባን ይሆናል። ቀጥሎ ያለውን ዘዴ መጠቀም ትችላለህ:- ፍላጎት የሚቀሰቅስ አንድ ጥያቄ ካነሳህ በኋላ ቅዱስ ጽሑፋዊ መልሱን ለመስጠት በማመራመር መጽሐፍ ተጠቀም። ወደ አንድ ቤት ተመልሰህ በምትሄድበት ጊዜ ፍላጎት ሊቀሰቅስ ይችላል ብለህ ያሰብከውን አንድ ጥያቄ መጠየቅ እንድትችል የተለያዩ ጥያቄዎችን በዝርዝር ጽፈህ ብትይዝ ጠቃሚ ነው። ከዚህ በታች የሰፈረው ከማመራመር መጽሐፍ የተውጣጣው የጥያቄዎች ዝርዝር መልሶቹ የሚገኙበትን ገጽ ይዟል:-
◼ የምናረጀውና የምንሞተው ለምንድን ነው? (98)
◼ በአምላክ መኖር ለማመን የሚያበቁ ጥሩ ምክንያቶች አሉን? (146)
◼ አምላክ በሰው ልጆች ላይ ስለሚደርሰው ነገር ግድ አለውን? (147)
◼ አንድ ሰው እውነተኛ ደስታ ያለበት ሕይወት እንዲያገኝ ወደ ሰማይ መሄድ ይኖርበታልን? (163)
◼ የአምላክን የግል ስም ማወቅና መጠቀም ያስፈለገው ለምንድን ነው? (197)
◼ የአምላክ መንግሥት ወደፊት ምን ያከናውናል? (228)
◼ የሰብዓዊ ሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? (243)
◼ ይህን ያህል ብዙ ሃይማኖቶች የኖሩት ለምንድን ነው? (321)
◼ አንድ ሰው ትክክለኛው ሃይማኖት የትኛው እንደሆነ እንዴት ሊያውቅ ይችላል? (327)
◼ ሰይጣን በአሁኑ ዓለም ውስጥ ምን ያህል ኃያል ነው? (363)
◼ አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? (392)
◼ ክፋት ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው? (427)
አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ወዲያውኑ ልታየው እንድትችል እንዲህ ዓይነት የጥያቄዎች ዝርዝር የያዘ ወረቀት መጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ ወይም ማመራመር መጽሐፍህ ውስጥ ማስቀመጥ ትችላለህ። ተመላልሶ መጠየቅ በምታደርግበት ጊዜ አንድ የምትናገረው ተጨባጭ ነገር በአእምሮህ መያዝህ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ሁሉ ተከታትሎ በመርዳት በኩል ታማኝ እንድትሆን ይረዳሃል።