የታኅሣሥ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ታኅሣሥ 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 27 (57)
13 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። “ወንጌል በኢንተርኔት” የሚለውን አጠር አድርገህ ሸፍን።
15 ደቂቃ፦ “በየዕለቱ ስለ ይሖዋ ተናገሩ።” ጥያቄና መልስ። አንቀጽ 4 ላይ በምትደርስበት ጊዜ ከትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ጥናት 16 ከአንቀጽ 14-16 ያሉትን ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ።
17 ደቂቃ፦ በወሩ ውስጥ የሚበረከተውን ጽሑፍ በግለት አስተዋውቅ። ክፍሉ የሚቀርበው በታኅሣሥ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 16 በአንቀጽ 7, 8 ላይ ተመሥርቶ ይሆናል። ተግባራዊ የሚሆኑ መግቢያዎችንና ተመላልሶ መጠየቆችን ከአንድ ሠርቶ ማሳያ ጋር አቅርብ።
መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 28 (58)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
20 ደቂቃ፦ “ኃጢአትን መግለጥ ለምን አስፈለገ?” በነሐሴ 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 26-30 ላይ የተመሰረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
15 ደቂቃ፦ “መቅረትህ ያጎድላል!” አንድ ሽማግሌ ከአድማጮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። የጉባኤውን አማካይ የተሰብሳቢዎች ቁጥር ጥቀስ። አንድ ላይ በስብሰባ ስንገናኝ አንዳንዶች መንፈሳቸው የሚታደሰው በምን ምክንያት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 76 (172) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 30 (63)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ዓለማዊ በዓሎችን አስመልክቶ የመልካም ምኞት መግለጫዎች በሚቀርቡልን ጊዜ በዘዴ መልስ መስጠት እንዴት እንደምንችል አንዳንድ ሐሳቦች አቅርብ።
12 ደቂቃ፦ በጥር 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣው የጥያቄ ሣጥን። ሁሉም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን፣ ለተወሰነ ጊዜ ርቀው በሚሄዱበት ጊዜ ጭምር በታማኝነት በመመለስ ከጉባኤው ጋር እንዲተባበሩ አበረታታ።
25 ደቂቃ፦ “ሰባኪዎች ብቻ ሳይሆን አስተማሪዎችም መሆን አለብን።” ጥያቄና መልስ። አንቀጽ 11ን በምታቀርብበት ጊዜ ከትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ጥናት 15 አንቀጽ 11ን አንብብ።
መዝሙር 77 (174) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 58 (138)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በተጨማሪም “አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም” የሚለውን ሸፍን።
10 ደቂቃ፦ “የ1998 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት።” በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። በሚቀጥለው ዓመት ውስጥ ሁሉም ከትምህርት ቤቱ ሙሉ ጥቅም ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ጥቀስ። በየሳምንቱ አዲሱን “ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም” እንዲከታተሉ አበረታታቸው።
20 ደቂቃ፦ ምሥራቹን በሁሉም ቦታ ስበኩ። ቀጥሎ በተዘረዘሩት ጥያቄዎች በመጠቀም ከአገልግሎታችን መጽሐፍ ገጽ 92-7 ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። (1) ምሥራቹን በማስፋፋት ረገድ ጽሑፎችን መጠቀም ውጤታማ የሆነው ለምንድን ነው? ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ጽሑፍ ማበርከት ያለብን ለምንድን ነው? (2) መደበኛ ባልሆነ ምሥክርነት ለመሳተፍ ንቁ መሆን ያለብን ለምንድን ነው? መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመስከር የሚያስችሉን አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው? (አንዳንዶች መደበኛ ባልሆነ መንገድ መስክረው ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።) (3) ጉባኤዎች የተመደበላቸውን ክልል አጣርተው ለመሸፈን ጥረት ማድረግ ያለባቸው ለምንድን ነው? ጉባኤው በቂ ክልል ካለው የራሳችንን ክልል መውሰዱ ምን ጥቅም አለው? (4) በቡድን ለመመስከር ከሚደረጉ ዝግጅቶች ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? ጊዜያችንን በአግባቡ መጠቀም እንድንችል ለስብከት ሥራችን እንዴት እቅድ ማውጣት እንችላለን?
መዝሙር 100 (222) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 81 (181)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም” የሚለውን ከልስ። ሁሉም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አበረታታ። ጉባኤያችሁ በአዲሱ ዓመት የመሰብሰቢያ ሰዓቱን የሚቀይር ከሆነ በአዲሱ ፕሮግራም መሠረት ሁሉም ዘወትር ጉባኤ መምጣት እንዲቀጥሉ በደግነት አበረታታቸው።
12 ደቂቃ፦ በጥር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። መግቢያ ለማዘጋጀት የሚረዱ ትኩረት የሚስቡ የመነጋገሪያ ነጥቦችን በመንግሥት አገልግሎታችን ጥር 1996 ገጽ 4 እና ሰኔ 1995 ገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ተጠቀም። አንድ ሠርቶ ማሳያም አቅርብ። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በተባለው ብሮሹር ወይም በእውቀት መጽሐፍ አማካኝነት ጥናት ለማስጀመር የምናደርገውን ጥረት መቀጠል ይኖርብናል።
23 ደቂቃ፦ “በአምላክ ቃል ማመን” የተባለውን የአውራጃ ስብሰባ ከልሱ። የእያንዳንዱን የስብሰባ ቀን እንዲከልሱ ሦስት ሽማግሌዎች ሊመደቡ ይችላሉ።
መዝሙር 96 (215) እና የመደምደሚያ ጸሎት።