የመጋቢት የአገልግሎት ስብሰባዎች
መጋቢት 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 1 (3)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ይህን ዘወትር ለመታሰቢያዬ አድርጉት።” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በመታሰቢያው በዓል ላይ መገኘት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ከአገልግሎታችን መጽሐፍ ገጽ 80-1 ላይ ያለውን ሐሳብ አጠር አድርገህ ግለጽ።
22 ደቂቃ፦ “በሰዎች አእምሮ ውስጥ የዘላለም ሕይወት ተስፋ እንዲቀረጽ አድርጉ።” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ውይይቶችን ለማስጀመር ጥያቄዎችን እንዴት ውጤታማ በሆነ መንገድ ልንጠቀምባቸው እንደምንችል አጠር አድርገህ ግለጽ። መሪ ጥያቄዎችንም ሆነ የአመለካከት ጥያቄዎቸን በመግቢያችን ላይ እንዴት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል አንዳንድ ምሳሌዎች ስጥ። (የትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 51-2 አንቀጽ 10-12 ተመልከት።) ብቃት ያለው አንድ አስፋፊ ከቀረቡት አቀራረቦች አንዱን በመጠቀም ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ጥናት ሲያስጀምር የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ ያቅርብ።
መዝሙር 20 (45) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 59 (139)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፓርት።
15 ደቂቃ፦ ከዓመት መጽሐፍ ሙሉ በሙሉ ተጠቀሙ። ባለፈው ዓመት የነበረውን ዓለም ዓቀፍ ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴ አስመልክቶ አንድ አባት ከቤተሰቡ ጋር በመሆን ከገጽ 3-6, 31ን ይከልሳል። ዘወትር በምግብ ሰዓት በዕለቱ ጥቅስ ላይ ቢወያዩና ከዓመት መጽሐፍ የተወሰነ ክፍል ቢያነቡ ቤተሰቡ ሊያገኘው የሚችለውን ጥቅም ይነጋገራሉ። ዓመቱን ሙሉ ይህንን ፕሮግራም ለመጠበቅ ይስማማሉ።
22 ደቂቃ፦ “ዘንድሮም ጥሪውን ትቀበላላችሁን?” (ከአንቀጽ 1-11) በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። ባለፈው ዓመት ከነበረው የረዳት አቅኚነት ዘመቻ የተገኙ አንዳንድ ጎላ ያሉ ነገሮች ከጠቀስክ በኋላ በዚያ ወቅት በጉባኤው ምን ያህል አስፋፊዎች ረዳት አቅኚ እንደሆኑ ግለጽ። አቅኚ መሆን ለእኛ ለራሳችን የሚያመጣውን ጥቅም ካወያየሃቸው በኋላ ይህ ተጨማሪ ጥረት ለጉባኤው እድገት ምን ያህል አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተናገር። ብዙዎች አቅኚ እንዲሆኑ ለመርዳት ጉባኤው በሚያዝያና በግንቦት ምን የአገልግሎት ዝግጅት ለማድረግ እቅድ እንዳለው ግለጽ። ስብሰባው ካለቀ በኋላ አስፋፊዎች የረዳት አቅኚነት ማመልከቻውን ሊወስዱ ይችላሉ።
መዝሙር 87 (195) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 83 (187)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። መጋቢት 29 ለሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ጋብዙ። የሕዝብ ንግግሩ ጭብጥ “በመጽሐፍ ቅዱስ ልትተማመኑ የምትችሉበት ምክንያት” የሚል ነው።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
22 ደቂቃ፦ “ዘንድሮም ጥሪውን ትቀበላላችሁን?” (ከአንቀጽ 12-19) ጥያቄና መልስ። በአገልግሎታችን መጽሐፍ ከገጽ 113-114 ላይ የሰፈረውን አንድ ሰው አቅኚ ለመሆን የሚጠበቁበትን ብቃቶች ከልስ። አንድ ሰው ረዳት አቅኚ መሆኑ ለዘወትር አቅኚነት እንዴት ሊያዘጋጀው እንደሚችል አብራራ። የሚጠበቅባቸውን 60 ሰዓት ለማምጣት ፕሮግራማቸውን እንዴት እንዳስተካከሉ እንዲናገሩ ባለፈው ዓመት ረዳት አቅኚ ከነበሩት መካከል አንዳንዶቹን ጋብዝ። በአባሪው መጨረሻ ገጽ ላይ ቀርቦ ከነበረው የናሙና ፕሮግራም ውስጥ ከእነሱ ሁኔታ ጋር ተስማሚ ሆኖ ያገኙት የትኛው ነበር? ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በ1987 የዓመት መጽሐፍ ከገጽ 48-9, 245-246 ያለውን ተሞክሮ ተናገር። አስፋፊዎች ስብሰባው ካለቀ በኋላ የረዳት አቅኚነት ማመልከቻ እንዲወስዱ አበረታታቸው።
መዝሙር 44 (105) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47 (112)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ልዩ የሕዝብ ንግግር ማሳሰቢያዎች። ሚያዝያ 11 ለሚውለው የመታሰቢያው በዓል ፍላጎት ያላቸውን መጋበዝ እንዲጀምሩ ሁሉንም አበረታታ። የመጋበዣ ወረቀቱን አንድ ቅጂ ካሳየሃቸው በኋላ ሁሉም በርከት አድርገው እንዲወስዱና በዚህ ሳምንት ለሚጋብዟቸው ሰዎች መስጠት እንዲጀምሩ አሳስባቸው። በሚያዝያ ወር ረዳት አቅኚ የሆኑትን ስም ዝርዝር አንብብ። አሁንም ቢሆን ለረዳት አቅኚነት ማመልከት የሚቻል መሆኑን ግለጽ። በሚያዝያ ወር ጉባኤው ለአገልግሎት ያወጣውን ፕሮግራም በሙሉ ጥቀስ።
20 ደቂቃ፦ አዳዲሶችን ለመስክ አገልግሎት አዘጋጅ። በንግግርና በውይይት የሚቀርብ። በእውቀት መጽሐፍ ጥናት የሚያስጠኑ ጥናቶቻቸው በአገልግሎት ከእነሱ ጋር እንዲሳተፉ ማዘጋጀትን ሊያስቡበት ይገባል። እውቀት መጽሐፍ ገጽ 105-6 አንቀጽ 14 እንዲሁም ገጽ 179 አንቀጽ 20 ላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ አጉላ። መጠበቂያ ግንብ 22-109 ገጽ 16-17 ከአንቀጽ 7-10 ላይ አዲሶች ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለመሆን ማሟላት ያለባቸውን ብቃት ከልስ። በሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን አንቀጽ 19 ላይ ያለውን ያልተጠመቁ አዳዲስ አስፋፊዎች አገልግሎት ሲጀምሩ እንዴት እንደምንረዳቸው እንዲሁም ልጆችን አስመልክቶ በሰኔ 1986 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 (የእንግሊዝኛ) ላይ ያለውን ሐሳብ ተመልከት።
15 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሳጥን። ጥያቄና መልስ። ክፍሉን የሚያቀርበው ሽማግሌ ከአገልግሎታችን መጽሐፍ ገጽ 131 አንቀጽ 1 እና 2 ላይ ያለውን ሐሳብ ይከልሳል።
መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 11 (29)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የመጋቢት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፓርታቸውን እንዲመልሱ አሳስብ። ሚያዝያ 1987 የመንግሥት አገልግሎታችን (የእንግሊዝኛ) ላይ “የአገልግሎት ሪፓርትህን በትክክል መልስ” ከሚለው ጭብጥ ስር ከቀረበው ሐሳብ ዋና ዋና ነጥቦች ጥቀስ። በቅርብ ጊዜ የወጡ መጽሔቶችን ካሳየህ በኋላ መጽሔቶቹን ለማበርከት የትኛውን ነጥብ ልናጎላ እንደምንችል አንዳንድ ተግባራዊ የመነጋገሪያ ነጥቦችን ጥቀስ። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ከልስ፤ የመታሰቢያውን በዓል በተመለከተ ጉባኤው ያደረገውን ዝግጅት ግለጽ። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችንና ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ ሁሉም ለመጨረሻ ጊዜ የተቻላቸውን ያህል ጥረት ማድረግ አለባቸው። ቅዱሳን ጽሑፎችን በዕየለቱ መመርመር በተባለው ቡክሌት ላይ በቀረበው መሠረት ከሚያዝያ 6-11 ያለውን የመታሰቢያ በዓል ሰሞን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ተከታትለው እንዲያነቡ አስታውሳቸው።
13 ደቂቃ፦ “ልጆች ሆይ፣ በእናንተ ደስ ይለናል!” ጥያቄና መልስ። ነሐሴ 1, 1987 (የእግሊዝኛ) መጠበቂያ ግንብ ገጽ 25 ላይ ያለውን ተሞክሮ ተናገር።
20 ደቂቃ፦ መንፈሳዊ ድካምን ለመዋጋት የሚረዱን ዘዴዎች። በጥር 15, 1986 (የእንግሊዝኛ) መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19 ላይ ያለውን ሳጥን ሁለት ሽማግሌዎች በውይይት ያቀርቡታል። “የመንፈሳዊ ድካም ምልክቶች” በሚል ርዕስ ስር የቀረበውን እያንዳንዱን ነጥብ ካነሳህ በኋላ “ለመጽናት የሚረዱ ነገሮች” በሚል ከጎኑ በቀረቡት ነጥቦች አንድ ሰው እንዴት ሊጠቀም እንደሚችል በጥቅሶቹ አስደግፈህ አብራራ። እንደነዚህ የመሰሉትን ነጥቦች ተግባራዊ ማድረጋቸው መንፈሳዊ ጥንካሬያቸውን ለመጠበቅ እንዴት እንደረዱአቸው ሐሳብ እንዲሰጡ ለሁለት አስፋፊዎች ቃለ መጠይቅ አድርግ።
መዝሙር 94 (212) እና የመደምደሚያ ጸሎት።