የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/98 ገጽ 2
  • የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ግንቦት 4 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 11 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 18 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 25 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 5/98 ገጽ 2

የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች

ግንቦት 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 5 (10)

8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች። ለበዓል ቀናት የተደረጉ ልዩ የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶችን ግለጽ።

15 ደቂቃ፦ “የይሖዋ መንፈስ ይደግፈናል።” ጥያቄና መልስ። አንቀጽ 3⁠ን ስትሸፍን ከዓመት መጽሐፍ ላይ የተመረጡ ነጥቦችን ጨምረህ አቅርብ።

22 ደቂቃ፦ “የሰዎችን ትኩረት የሚስቡ የተወሰኑ ርዕሶችን ምረጡ።” ከርዕሱ ውስጥ ዋና ዋና ነጥቦችን ከልስ። በጥሩ ሁኔታ የሚገኙ የቆዩ እትሞችንም በዚህ መንገድ ማበርከት እንደሚቻል አብራራ። ጥሩ ውጤት ያስገኘላቸው ርዕስ የትኛው እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። አንቀጽ 7 ላይ ባለው አቀራረብ አንድ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

መዝሙር 94 (212) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 11 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 22 (47)

8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

12 ደቂቃ፦ “ለመጪዎቹ ወራት ምን ዕቅድ አውጥታችኋል?” አንድ ሽማግሌ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎችን ለመጪዎቹ ወራት ምን እቅድ እንዳላቸው ይጠይቃቸዋል። የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴያቸውንና ሌሎች ቲኦክራሲያዊ ግቦቻቸውን ከፍ ማድረግ የሚችሉባቸውን ዝግጅቶች ይከልሳሉ።

25 ደቂቃ፦ “የዓለም መንፈስ እየመረዛችሁ ነውን?” በጥቅምት 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ ላይ የተመሠረተ ንግግር። መጨረሻ ላይ ዋና ዋና ነጥቦችን በጥያቄና መልስ ከልስ።

መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 18 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 80 (180)

8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “‘የሥጋ መውጊያ አለብህን?’” ጥያቄና መልስ። ኅዳር 15, 1987 መጠበቂያ ግንብ (እንግሊዝኛ) ገጽ 29 “የአንባብያን ጥያቄዎች” ከሚለው ላይ ሐሳብ አክል።

22 ደቂቃ፦ “በመንፈሳዊ በደንብ ትመገባለህ?” በሚያዝያ 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ላይ የተመሠረተ ንግግር ከቀረበ በኋላ በጥያቄና መልስ ይከለሳል።

መዝሙር 59 (139) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 25 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 36 (81)

7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

18 ደቂቃ፦ “በጥሩ ምግባር መመሥከር።” ጥያቄና መልስ። ምሳሌ ለሚሆኑ የተወሰኑ ወጣቶች ቃለ መጠይቅ አድርግ። በክርስቲያናዊ ምግባራቸው የተነሳ ሌሎች እንዴት እንደተነኩ ይናገራሉ። ከጥር 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 24-5 ላይ አንድ ወይም ሁለት ተሞክሮዎችን ተናገር።

20 ደቂቃ፦ የጉባኤ ስብሰባዎችን ከፍ አድርገን የምንመለከተው ለምንድን ነው? አንድ ሽማግሌ የተለያየ ሁኔታ ያላቸውን የጉባኤ አባላት የሚወክሉ አዘውታሪ ተሰብሳቢ ወንድሞችንና እህቶችን ካቀፈ አንድ ቡድን ጋር ወይይት ያደርጋል። በስብሰባዎች ላይ ዘወትር የሚገኙት ለምን እንደሆነ ይገልጻሉ። ከሚጠቅሷቸው ምክንያቶች መካከል በጉባኤ የሚያገኙት ጥሩ ባልንጀርነት፣ መለኮታዊ ትምህርት እንዲሁም በየዕለቱ የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለመወጣትና በመንፈሳዊ ጠንካራ ሆነው ለመቆም የሚያስችሉ ጠቃሚ ምክሮች ይገኙባቸዋል። የሚሰጡት ሐሳብ ሁላችንም አዘውትረን በስብሰባዎች ላይ በመገኘታችን የተባረክነው እንዴት እንደሆነ ጠበቅ አድርጎ የሚገልጽ ይሁን።

መዝሙር 100 (222) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ