የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/98 ገጽ 2
  • የመስከረም የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመስከረም የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 9/98 ገጽ 2

የመስከረም የአገልግሎት ስብሰባዎች

መስከረም 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 66 (155)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “የበለጠ ማድረግ እንችላለን።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ሁሉም ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ሊደርሱባቸው የሚችሉትን ግቦች እንዲያወጡና ግቦቻቸው ላይ ለመድረስም ጠንክረው እንዲሠሩ አበረታታ።—አገልግሎታችን ገጽ 116–18 ተመልከት።

20 ደቂቃ፦ “አቅኚዎች ሌሎችን ይረዳሉ።” አንድ ሽማግሌ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ማሠልጠኛ በተጨማሪ አቅኚዎች በግለሰብ ደረጃ ሌሎችን በአገልግሎት እንዲረዱ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ያብራራል። በርዕሰ ትምህርቱ ላይ የተመሠረቱ ጥያቄዎችን በማቅረብ አድማጮች በተለይም በዚህ ፕሮግራም በመካፈል ላይ የሚገኙ አቅኚዎችና አስፋፊዎች ሐሳብ እንዲሰጡ ይጋብዛል። ከዚህ ዝግጅት የተሻለ ውጤት እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ተወያዩ። አቅኚዎች ሌሎችን በመርዳቱ በኩል በመካፈላቸው ደስታና ጥቅም ያገኙት እንዴት እንደሆነ ሊናገሩ ይችላሉ። እርዳታ እያገኙ ያሉት አስፋፊዎችም ይህን ፍቅራዊ ዝግጅት ምን ያህል እንደሚያደንቁ ሊናገሩ እንዲሁም በአገልግሎት ይበልጥ ስኬትና ደስታ እንዲያገኙ የረዷቸውን ነገሮች ሊጠቅሱ ይችላሉ።

መዝሙር 76 (172) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መስከረም 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 69 (160)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ፦ “‘የአምላክ የሕይወት መንገድ’ የ1998 የአውራጃና ብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።

20 ደቂቃ፦ ያለፈው ዓመት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስላል? ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ያለፈው ዓመት የጉባኤው የአገልግሎት ሪፖርትና የተሰብሳቢዎች አኃዝ ምን ይመስል እንደነበር ይከልሳሉ። አበረታች የሆኑትን የሪፖርቱ ገጽታዎች ከጠቀሱ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ በሚያስፈልግባቸው ዘርፎች ላይ ያተኩራሉ። በነሐሴ ወር በአገልግሎት የተካፈሉት ሁሉም አስፋፊዎች ናቸውን? ሁሉም አዘውታሪ አስፋፊ እንዲሆኑ መርዳትን ጨምሮ በመጪዎቹ ወራት ሽማግሌዎች ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ግቦች ይዘረዝራሉ። የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ባለፈው ጉብኝቱ ካሰፈረው ሪፖርት ተስማሚ ሐሳቦችን ጥቀሱ።

መዝሙር 61 (144) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መስከረም 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 51 (127)

15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜና። አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም።

10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ፦ “ከወንድሞቻችሁ ጋር በደንብ ተዋወቁ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። መጠበቂያ ግንብ 19–109 ከገጽ 10-12 ላይ የሰፈሩትን ሐሳቦች አክለህ አቅርብ። ሁሉም ራሳቸው ቀዳሚ በመሆን ሌላውን በደንብ ለማወቅ እንዲነሳሱ አበረታታ።

መዝሙር 14 (34) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መስከረም 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 25 (53)

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስከረም የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። የመጽሔት ስርጭቱን ከፍ ለማድረግ እንዲቻል በጥቅምት ወር ሁሉም ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት ይበልጥ ለመካፈል የሚያስችላቸውን እቅድ ከወዲሁ እንዲያወጡ አበረታታ። አቀራረቦችን እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል ሐሳብ ለማግኘት የጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 10⁠ን እንዲመለከቱ ሐሳብ ስጥ። በቅርቡ የደረሱንን መጽሔቶች እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ቅዳሜና እሁድ በአገልግሎት የምትጠቀሙባቸውን መጽሔቶች ውሰዱ።

20 ደቂቃ፦ “ግንባር ቀደም ሆነው የሚያገለግሉ የበላይ ተመልካቾች—የአገልግሎት የበላይ ተመልካች።” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግር የሚቀርብ። የሥራ ኃላፊነቶቹን ከገለጸ በኋላ ጉባኤው የአገልግሎት አድማሱንና ውጤታማነቱን ለማስፋት ይችል ዘንድ ትብብሩን ሊያሳይ የሚችልባቸውን መንገዶች ለይቶ ይጠቅሳል።

13 ደቂቃ፦ ትጉህ የጉባኤ አስፋፊ ለመሆን የሚያስፈልገው ምንድን ነው? አድማጮች መጠነኛ ተሳትፎ የሚያደርጉበት ንግግር። ትጉህ አስፋፊ ለመሆን ልዩ ችሎታ ወይም የተለየ ተሰጥዎ አይጠይቅም። ከዚያ ይልቅ ዋናው ነገር ሁላችንም ፍቅርን፣ ትሕትናን፣ ቅንዓትንና አድናቆትን የሚያንጸባርቅ የፈቃደኝነት ዝንባሌ መያዛችን ነው። ከዚህ ቀጥሎ የሰፈሩት ባሕርያት አስፈላጊ የሆኑት ለምን እንደሆነ አድማጮች እንዲናገሩ ጋብዝ:- (1) የደስተኝነት መንፈስ፣ (2) በስብሰባዎች ላይ አዘውትሮ መገኘትና ተሳትፎ ማድረግ፣ (3) የሥራ ኃላፊነቶችን ለመቀበልና ለመፈጸም የፈቃደኝነት መንፈስ ማሳየት፣ (4) ከሽማግሌዎችና ለጉባኤው ከሚደረጉት ዝግጅቶች ጋር ተባብሮ መሥራት፣ (5) ሌሎችን ለማገዝ ልባዊ ፍላጎት ማሳየት እንዲሁም (6) በመስክ አገልግሎት አዘውትሮ መካፈልና በየወሩ ሳይዘገዩ ሪፖርት መመለስ።

መዝሙር 27 (57) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ