መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። መዝሙር። ማህሌት።
66 ምድር ሁሉ፣ በድል አድራጊነት ለአምላክ እልል ትበል።+
2 ለክብራማ ስሙ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።
ውዳሴውን አድምቁ።+
3 አምላክን እንዲህ በሉት፦ “ሥራዎችህ አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ ናቸው።+
ከኃይልህ ታላቅነት የተነሳ
ጠላቶችህ በፊትህ ይሽቆጠቆጣሉ።+
5 ኑና የአምላክን ሥራዎች ተመልከቱ።
ለሰው ልጆች ያከናወናቸው ተግባሮች አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ ናቸው።+
በዚያ በእሱ እጅግ ደስ አለን።+
7 በኃይሉ ለዘላለም ይገዛል።+
ዓይኖቹ ብሔራትን አተኩረው ያያሉ።+
ግትር የሆኑ ሰዎች ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያድርጉ።+ (ሴላ)
8 እናንተ ሕዝቦች ሆይ፣ አምላካችንን አወድሱ፤+
ለእሱ የሚቀርበውም የውዳሴ ድምፅ ይሰማ።
10 አምላክ ሆይ፣ አንተ መርምረኸናልና፤+
ብር በእሳት እንደሚጠራ ሁሉ አንተም እኛን አጥርተኸናል።
11 ማጥመጃ መረብ ውስጥ አስገባኸን፤
በላያችንም* ከባድ ሸክም ጫንክብን።
13 ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ይዤ ወደ ቤትህ እመጣለሁ፤+
ስእለቴንም ለአንተ እፈጽማለሁ፤+
14 ይህም በጭንቅ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ ከንፈሮቼ ቃል የገቡት፣
አፌም የተናገረው ነው።+
15 የሰቡ እንስሳትን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጌ
ከሚጨስ የአውራ በጎች መሥዋዕት ጋር አቀርብልሃለሁ።
ከአውራ ፍየሎችም ጋር ኮርማዎችን አቀርባለሁ። (ሴላ)
17 በአፌ ወደ እሱ ተጣራሁ፤
በአንደበቴም ከፍ ከፍ አደረግኩት።
18 በልቤ አንዳች መጥፎ ነገር ይዤ ቢሆን ኖሮ፣
ይሖዋ ባልሰማኝ ነበር።+
20 ጸሎቴን ከመስማት ጆሮውን ያልመለሰ፣
ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን ያልነፈገኝ አምላክ ውዳሴ ይድረሰው።