የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/98 ገጽ 8
  • አዲሲቱ ዓለም ትርጉምን ማበርከት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዲሲቱ ዓለም ትርጉምን ማበርከት
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በዓለም ዙሪያ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ አድናቆት ያተረፈው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • የአምላክ ቃል አፍቃሪዎች ትልቅ ግምት የሚሰጡት ክንውን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • አዲስ ዓለም ትርጉም ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ነው?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • ሕያው የሆነ የአምላክ ቃል ትርጉም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 12/98 ገጽ 8

አዲሲቱ ዓለም ትርጉምን ማበርከት

1 “አዲሲቱ ዓለም [ትርጉምን] ማግኘቱ እጅግ ጠቃሚ ነው። ቀስቃሽና ሕያው ሲሆን አንባቢውንም እንዲያስብና እንዲያጠና ያደርገዋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ተቺዎች የሥራ ውጤት ሳይሆን ለአምላክና ለቃሉ አክብሮት ያላቸው ምሁራን ሥራ ነው።” እንዲህ በማለት የተናገሩት አንድ የታወቁ የዕብራይስጥና የግሪክ ቋንቋ ተንታኝ ናቸው። እኛም በዚህ ሐሳብ እንስማማለን። በታኅሣሥ ወር የአዲሲቱ ዓለም ትርጉምን ከእውቀት መጽሐፍ ጋር በአንድነት ስናበረክት ሰዎች ለትርጉሙ ተመሳሳይ የሆነ አድናቆት እንዲኖራቸው እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን?

2 አንዳንድ ሰዎች “የራሴ መጽሐፍ ቅዱስ አለኝ። ሌላ አልፈልግም” የሚል ምላሽ ይሰጡ ይሆናል። ዋናው ዓላማችን አዲሲቱ ዓለም ትርጉም እንደ ማንኛውም ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም አለመሆኑን እንዲገነዘቡ ማድረግ ነው። የበኩረ ጽሑፉን ሐሳብ በትክክል የያዘና በዘመናዊ ቋንቋ የተጻፈ ቀጥተኛ ትርጉም ነው። ትርጉሙ የላቀ እንደሆነ የሚያሳየው አንዱ ገጽታ በ1 ቆሮንቶስ 10:25 ላይ ለተገለጸው “በሥጋ ገበያ” ለሚለው ሐረግ በኪንግ ጄምስ ቨርሽን ላይ የገባውን “ሼምብልስ” የሚለውን የቆየ የእንግሊዝኛ ቃል በአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ላይ ከገባው “ሚት ማርኬት” ከሚለው ዘመናዊ ቃል ጋር በማወዳደር ለማየት ይቻላል።

3 መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡ ጥቂት ሰዎች ቢኖሩም እንኳ እነሱም ቢሆኑ ለዕለት ተለት ሕይወት ጠቃሚ የሆኑትን መመሪያዎች በትክክል አይረዱም። የአምላክ ቃል በሕይወታቸው ላይ በጎ ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችልና ስለ ሐቀኝነት፣ ስለ ሥነ ምግባር እንዲሁም ስለ ቤተሰብ ሕይወት የሚሰጠው ምክር የጊዜያችንን ችግሮች ለመወጣት ሊረዳን እንደሚችል ማወቅ ያስፈልጋቸዋል። ይህን እንዴት ማድረግ ይቻላል?

4 ለናሙና የሚሆን አቀራረብ፦ “በፍጥነት በመለዋወጥ ላይ ባሉት የጊዜያችን የሥነ ምግባር አቋሞችና ስለ ወደፊቱ ጊዜ ባለው ጥርጣሬ ምክንያት ለሕይወታችን አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት እንደሚያስፈልገን አይስማሙም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊ መጽሐፍ ቢሆንም ለዘመናዊው ኑሮና አስደሳች ለሆነ የቤተሰብ ሕይወት ተግባራዊ ምክር ይሰጣል።” ከዚያም እውቀት መጽሐፍ ምዕራፍ 2⁠ን ግለጥና አንቀጽ 10⁠ን እና የአንቀጽ 11⁠ን የመጀመሪያ ዓረፍተ ነገር እንዲሁም 2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17⁠ን አንብብ። ፍላጎት ካሳየ የእውቀት መጽሐፍን አበርክትና በነፃ ስለምናደርገው የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አብራራለት፤ ከዚያም አዲሲቱ ዓለም ትርጉም እንዲወስድ ጋብዘው። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በተሰኘው ብሮሹር ጥናት ማስጀመሩ የተሻለ ሆኖ ካገኘኸው እንደዚያ ልታደርግ ትችላለህ። በማመራመር መጽሐፍ ከገጽ 9–15 ላይ ተስማሚ የሆኑ ተጨማሪ መግቢያዎች ታገኛለህ።

5 ከሁሉ የላቀ ለሆነው ለአዲሲቱ ዓለም ትርጉም አድናቆት እንዳለን እናሳይ። በታኅሣሥ ወር በቅንዓት በማበርከት ይህን ልናደርግ እንችላለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ