የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/99 ገጽ 2
  • የጥር የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥር የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥር 4 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 11 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 18 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 1/99 ገጽ 2

የጥር የአገልግሎት ስብሰባዎች

ጥር 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 65 (152)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “የቆዩ መጻሕፍትን በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙባቸው።” ጥያቄና መልስ። በጉባኤያችሁ የሚገኙትን የቆዩ መጻሕፍት ዘርዝር። አንዳንድ ማራኪ የሆኑ ገጽታቸውን ጥቀስና ማበርከት የሚቻልበትን መንገድ ግለጽ። በጥርና በየካቲት በመስክ አገልግሎትና መደበኛ ባልሆነ ምሥክርነት ሲካፈሉ እነዚህን መጻሕፍት እንዲያበረክቱ ሁሉንም አበረታታ። አጭርና ቀላል የሆነ አቀራረብ የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

20 ደቂቃ፦ ደም አልባ የሆነ ሕክምና ለማግኘት ሕጋዊ ምርጫ ማድረግ። (ሥራ 15:28, 29) በ11–09 እና በመስከረም 1992 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ተመሥርቶ ጥሩ ችሎታ ባለው ሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርግ ካርድ:- ከዚህ ስብሰባ በኋላ የተጠመቁ ምሥክሮች አዲስ ካርድ የሚሰጣቸው ሲሆን ያልተጠመቁ ትንንሽ ልጆች ካሏቸው ለእያንዳንዱ ልጅ የመታወቂያ ካርድ ይሰጣቸዋል። እነዚህ ካርዶች ዛሬውኑ መሞላት የለባቸውም። እቤት በጥንቃቄ ሊሞሉ ይገባል ሆኖም አይፈረምባቸውም። ሁሉም ካርዶች የሚፈረምባቸው፣ የምሥክሮቹ ስምና ቀን የሚጻፍባቸው ከፊታችን የሚደረገው የመጽሐፍ ጥናት ስብሰባ ካለቀ በኋላ በመጽሐፍ ጥናቱ መሪ ተቆጣጣሪነት ነው። ከመፈረማችሁ በፊት ካርዶቹ ሙሉ በሙሉ መሞላታቸውን አረጋግጡ። ምሥክር ሆነው የሚፈርሙት የካርዱ ባለቤት ሰነዱን ሲፈርም ማየት ይኖርባቸዋል። ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ከሁኔታቸውና ከአቋማቸው ጋር በሚስማማ መንገድ ሐሳቡን ከዚህ ካርድ ላይ በመውሰድ ለራሳቸውና ለልጆቻቸው የራሳቸውን መመሪያ ሊያዘጋጁ ይችላሉ። የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች በቡድናቸው ውስጥ ያሉት በሙሉ በቅድሚያ የተሰጠውን የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሞያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገውን ካርድ መሙላት እንዲችሉ አስፈላጊውን ትብብር ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ ምልክት የሚያደርጉበት ማስታዎሻ ማዘጋጀት አለባቸው።

መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 11 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 20 (45)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

20 ደቂቃ፦ “የይሖዋን የሕይወት መንገድ ለመከተል ያደረግነው ቁርጥ ውሳኔ።” ንግግር። ሁሉም በአምስቱ የጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ዘወትር እንዲገኙ ማበረታቻ ስጥ።

15 ደቂቃ፦ “ታገሡ።” በአንድ የቤተሰብ አባላት መካከል የሚደረግ ውይይት። በአገልግሎታቸው በተሻለ ሁኔታ ትዕግሥት ማሳየት በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ ይወያያሉ። ከሰኔ 15, 1995 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 12 ላይ ተስማሚ የሆኑ ሐሳቦችን ጨምራችሁ አቅርቡ።

መዝሙር 56 (135) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 18 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 75 (169)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “ግንባር ቀደም የሆኑ የበላይ ተመልካቾች—የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት መሪዎች።” ኃላፊነቶቹን በመከለስ ምሳሌ የሚሆን የመጽሐፍ ጥናት መሪ በንግግር ያቀርበዋል። እንዲህ የመሰለው ሥራ ለጉባኤው እድገትና መንፈሳዊ ደኅንነት ምን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይገልጻል። አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 43–5, 75–6 ላይ ቁልፍ የሆኑ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

20 ደቂቃ፦ “አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? በተባለው ብሮሹር ጥናት ማስጀመር።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።

መዝሙር 94 (212) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 25 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 89 (201)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “አቅኚዎች እንዲያሟሉ በሚጠበቅባቸው ሰዓት ላይ የተደረገ ማሻሻያ።” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በጉባኤያችሁ ያሉትን አቅኚዎች አመስግናቸው። በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ተጨማሪ ጥረት እንደምናደርግ ግምት ውስጥ በማስገባት ተጨማሪ አስፋፊዎች የረዳትና የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት እንዲጀምሩ አበረታታ። ከየካቲት 1997 እና ከሐምሌ 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪዎች አንዳንድ ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።

20 ደቂቃ፦ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ ትመረምራላችሁ? በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በየዓመቱ ማኅበሩ ቅዱሳን ጽሑፎችን መመርመር የተባለውን ቡክሌት ያዘጋጃል። በግል ወይም በቤተሰብ መልክ ይህን ጽሑፍ ጥሩ አድርጋችሁ ትጠቀሙበታላችሁ? ለእያንዳንዱ ቀን የተመደበውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ መመርመራችን ጠቃሚ የሆነበትን ምክንያት አብራራ። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—1999 ላይ በገጽ 3–4 በሚገኘው መቅድም ላይ የተሰጡትን ሐሳቦች ጥቀስ። አስፋፊዎች በግልም ሆነ በቤተሰብ መልክ ያለማቋረጥ የዕለቱን ጥቅስና ሐሳቡን ለመመርመር የሚያደርጉትን ልዩ ጥረት እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 97 (217) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ