የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/99 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 1/99 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥርና የካቲት፦ በጉባኤው የሚገኝ ከ1985 በፊት የታተመ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ወይም መንግሥትህ ትምጣ፣ የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው፣ በሕይወት ተርፎ ወደ አዲስ ምድር መግባት፣ የአምልኮ አንድነት ወይም ወጣትነትህ የተባሉትን መጻሕፍት እያንዳንዳቸውን በሦስት ብር ማበርከት ይችላሉ። መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት መጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል።

◼ ጥር 4 በሚጀምር ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚገኙት የተጠመቁ አስፋፊዎች በሙሉ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገው ሰነድ ይሰጣቸዋል። ለልጆቻቸው ደግሞ መታወቂያ ካርዱ ይሰጣል።

◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የሚውለውን የመታሰቢያ በዓል ለማክበር ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ምንም እንኳን ንግግሩን ቀደም ብሎ መጀመር ቢቻልም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ የምትጠልቅበትን ሰዓት ጠይቃችሁ ተረዱ። ምንም እንኳ እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን ቢያከብር የሚመረጥ ቢሆንም ሁልጊዜ እንዲህ ማድረግ አይቻል ይሆናል። የሚቻል ከሆነ ከእንግዶች ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ፣ አዳዲሶችን ለማበረታታት እንዲሁም ከአጋጣሚው ሙሉ ጥቅም ማግኘት እንዲቻል ሁለቱ ጉባኤዎች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች መካከል ቢያንስ 20 ደቂቃ እንድትመድቡ ሐሳብ እናቀርብላችኋለን። የሽማግሌዎች አካል ካሁን ቀደም የተላከላቸውን የሚያዝያ 27, 1998 ደብዳቤ ግምት ውስጥ በማስገባት ለጉባኤያቸው ምን ዝግጅት ቢያደርጉ የተሻለ እንደሚሆን መወሰን አለባቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ