ማቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
◼ ጥቅምት 7, 1998 በቡልጋሪያ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች ሕጋዊ እውቅና አግኝተው ተመዝግበዋል። ለዚህ ለውጥ በዚያ ከሚገኙት 946 አስፋፊዎች ጋር ሆነን ይሖዋን እናመሰግናለን።
◼ በጥቅምት 12, 1998 የላቲቪያ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ 21 ጉባኤዎች ውስጥ ለሁለቱ የምዝገባ ፈቃድ ሰጥቷል።
◼ በፈረንሳይ የሚኖሩ ወንድሞች ተቃውሞ ቢኖርባቸውም በመንግሥቱ የስብከት ሥራ ጸንተዋል። በኅዳርና በታኅሣሥ የአገሪቱ ነዋሪዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ትኩረት እንዲሰጡ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ብሮሹር ለማበርከት ልዩ ዘመቻ ተደርጎ ነበር። ወደ 50 የሚጠጉ ቤቴላውያን በቅርንጫፍ ቢሮው በሚካሄደው የኅትመትና ጽሑፍ የመላክ ሥራ ለማገዝ ከፈረንሳይ ወደ ብሪታንያ ተዛውረዋል። የተቀሩት 250 የፈረንሳይ ቤቴል ቤተሰብ አባላት እንዲሁም በመስክ የሚያገለግሉ ወንድሞች እንደወትሮው በደስታ ማገልገላቸውን ቀጥለዋል።
◼ የሚከተሉት የመንግሥት አዳራሾች በቅርቡ ለአምላክ አገልግሎት ተወስነዋል:- አለታ ወንዶ፣ አዋሳ፣ ደሴ፣ ጊንጪ፣ ሻሸመኔ፣ ሲባጫሮ፣ ወሊሶ፣ ይርጋለም።