ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
◼ አልባኒያ፦ በጥር ወር 1,556 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ሪፖርት አድርጋለች። ይህም ካለፈው ዓመት አማካይ ቁጥር 20 በመቶ ጭማሪ አለው።
◼ ካናዳ፦ በጥር 1, 1999 አራት መቶ ስልሳ አዳዲስ የዘወትር አቅኚዎች ተሹመዋል።
◼ የማርሻል ደሴቶች፦ በየካቲት በአጠቃላይ 203 አስፋፊዎች የነበሩ ሲሆን ይህም ባለፈው ዓመት በዚሁ ወር ከነበሩት አስፋፊዎች 4 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል!
◼ ኖርዌይ፦ በየካቲት 1999 የነበሩት የረዳት አቅኚዎች ቁጥር በየካቲት 1998 ከነበረው 72 በመቶ፣ የዘወትር አቅኚዎች ቁጥር 9 በመቶ፣ ተመላልሶ መጠየቅ 4 በመቶ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ቁጥር 6 በመቶ ከፍ ብሏል። የተበረከቱ መጻሕፍትና ብሮሹሮች ቁጥርም ጨምሯል።
◼ ሩማንያ፦ በአቅኚነቱ እንቅስቃሴና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ረገድ ጥሩ ጭማሪ የታየ ሲሆን በየካቲት ወር 37,502 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር በመስኩ ተገኝቷል።
◼ ኢትዮጵያ፦ በአሶሳ አዲስ የመንግሥት አዳራሽ ለአምላክ አገልግሎት ተወስኗል። የተሟላው የመታሰቢያው በዓል ተሰብሳቢ ቁጥራችን 15,987 ሲሆን ይህም አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ነው።