የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/99 ገጽ 8
  • “ፍሬ ነገሩን” እንናገር!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ፍሬ ነገሩን” እንናገር!
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሕይወት አድን በሆነው አገልግሎታችን ስኬታማ በሆነ መንገድ መካፈል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ሌሎች ሰዎች ስለ አምላክ ልጅ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲማሩ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • መጽሔቶችን ለማበርከት የሚያስችሉ መግቢያዎችን መዘጋጀት የሚቻለው እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • በአገልግሎታችሁ ወርቃማውን ሕግ ተግባራዊ አድርጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 7/99 ገጽ 8

“ፍሬ ነገሩን” እንናገር!

1 በሚገባ የተዘጋጃችሁበትን አቀራረብ ተጠቅማችሁ አንድ ሰው ስታነጋግሩ “ምን ለማለት ነው የፈለግኸው? ፍሬ ነገሩን ተናገር!” ብሎ አቋርጧችሁ ያውቃል? ከሆነ ከዚህ ምን ልንማር እንችላለን?

2 ዛሬ ብዙ ሰዎች ትዕግሥት የላቸውም። የእኛን ማንነትና የመጣንበትን ዓላማ ቶሎ ማወቅ ይፈልጋሉ። የጉብኝታችን ዓላማ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ለመወያየት እንደሆነ ሲያውቁ ለማዳመጥ ፈቃደኞች ላይሆኑ ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብና መንፈሳዊ ውይይት ማድረግ በብዙ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ቦታ የሚሰጣቸው ነገሮች አይደሉም። እንደዚህ ያሉ ሰዎች ጥቂት ደቂቃዎች ወስደው ከእኛ ጋር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲወያዩ ልናሳምናቸው የምንችለው እንዴት ነው?

3 ከሁሉ የተሻለው ዘዴ፦ ቁልፉ እርሱን ለሚያስጨንቁት ችግሮች መጽሐፍ ቅዱስ ተግባራዊ መፍትሄ እንደሚሰጥ በተቻለ መጠን በጥቂት ቃላት ማስረዳት ነው። በጣም ውጤታማ የሚባሉት አቀራረቦች የምናነጋግረውን ሰው እንዲያስብ የሚያደርጉ ቀጥተኛ ጥያቄዎችን የያዙና ለዚያም በጥቅስ የተደገፈ መልስ የሚሰጡ ናቸው። ከዚህ ቀጥሎ ከቀረቡት ሐሳቦች መካከል አንዳንዶቹን ልትሞክሯቸው ትችላላችሁ። የምናነጋግረውን ሰው ፍላጎት ቀስቅሰን ቶሎ ወደ ‘ፍሬ ነገሩም’ መሄድ እንድንችል ለመርዳት ታስበው የተዘጋጁ ናቸው።

v4 የምታነጋግራቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ፍላጎት የለኝም በሚሉበት የአገልግሎት ክልል ውስጥ እነርሱን በቀጥታ የሚነካ ጥያቄ አንሳ:-

◼ “ወደ አዲሱ ሺህ ዓመት እየተቃረብን ባለንበት በአሁኑ ወቅት ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ ይታይዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ አሁን ስለምናያቸው የሚያሸብሩ ነገሮችና ስለሚያስከትሉት ውጤት አስቀድሞ ተናግሯል።”—2 ጢሞቴዎስ 3:1, 2, 5 እና ምሳሌ 2:21, 22⁠ን አንብብ።

◼ “ጥሩ የጤና አጠባበቅ በአካባቢያችን በሰፊው የሚያወያይ ጉዳይ ሆኗል። አምላክ ሁሉንም የጤና ችግሮች ለዘለቄታው ለማስወገድ ቃል እንደገባ ያውቃሉ?”—ራእይ 21:3, 4⁠ን አንብብ።

◼ “እያንዳንዱ ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር ተስማምቶ ቢኖር ያለንበት ማኅበረሰብ ምን ጥቅም ያገኛል ብለው ያስባሉ?”—ማቴዎስ 22:37-39⁠ን አንብብ።

5 ተልዕኮአችን የመንግሥቱን ምሥራች መስበክ ስለሆነ ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ሰዎች ይህ መንግሥት በሚያከናውነው ነገር ላይ እንዲያተኩሩ ማድረግ አለብን። እንዲህ ልትሉ ትችሉ ይሆናል:-

◼ “የዓለማችን እጅግ ጥንታዊ መጽሐፍ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ መላውን ዓለም የሚያስተዳድር አንድ መንግሥት እንደሚመጣ አስቀድሞ እንደተናገረ ያውቃሉ?”—ዳንኤል 2:44⁠ን አንብብ።

◼ “ኢየሱስ ክርስቶስ ምድርን ቢያስተዳድር ኖሮ ሁኔታዎች ምን መልክ ይኖራቸዋል ብለው ያስባሉ?”—መዝሙር 72:7, 8⁠ን አንብብ።

6 ሃይማኖታዊ የሆኑ ሰዎች በበዙበት የአገልግሎት ክልል ውስጥ ከእነዚህ መግቢያዎች አንዱን ልትጠቀሙ ትችላላችሁ:-

◼ “ብዙ ሰዎች በጾታ፣ በሃይማኖት ወይም በቆዳ ቀለማቸው የተነሳ አድልዎ ይደረግባቸዋል። አምላክ ስለ እንደዚህ ዓይነቱ መሠረተ ቢስ ጥላቻ እንዴት የሚሰማው ይመስልዎታል?”—ሥራ 10:34, 35⁠ን አንብብ።

◼ “ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት ብዙ ተዓምራትን እንዳደረገ እናውቃለን። አንድ ሌላ ተጨማሪ ተዓምር እንዲያደርግ የመጠየቅ አጋጣሚ ቢያገኙ ምን ተዓምር እንዲያከናውን ይጠይቁት ነበር?”—መዝሙር 72:12-14, 16⁠ን አንብብ።

7 የምታነጋግሩት ሰው በሩን ለመክፈት የሚያመነታ ከሆነ እንዲህ በማለት ውይይት ልትጀምሩ ትችሉ ይሆናል:-

◼ “ዛሬ ብዙ ሰዎች ስለ ችግር መስማት ሰልችቷቸዋል። ከዚህ ይልቅ መስማት የሚፈልጉት ስለ መፍትሔው ነው። እርስዎም ይህን እንደሚፈልጉ ምንም ጥርጥር የለውም። ይሁን እንጂ ለችግሮቻችን እውነተኛ መፍትሔ ከየት ማግኘት እንችላለን?” መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።—2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17⁠ን አንብብ።

8 ለምን አትሞክሯቸውም? አብዛኛውን ጊዜ የምናነጋግረውን ሰው ፍላጎት ለማነሳሳት የሚያስፈልገው ቀላልና እጥር ምጥን ያለ ጥያቄ ነው። አንዲት እህት አስቀድሞ ተቃዋሚ የነበረችን ሴት “በጌታ ጸሎት ውስጥ ያለው መንግሥትህ ትምጣ ብለው የሚጸልዩለት መንግሥት የቱ እንደሆነ ያውቃሉ?” ብላ በጠየቀቻት ጊዜ ወደ ቤቷ እንዲገቡ ጋበዘቻቸው። ጥያቄው ትኩረቷን ስቦት ነበር። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ እንድታጠና የቀረበላትን ግብዣ ተቀበለች። አሁን ራሷን የወሰነች የይሖዋ አገልጋይ ነች!

9 አንድን ሰው ስታነጋግሩ ስሜታችሁ እውነተኛ ይሁን። ከልባችሁ ተናገሩ። ሰዎች ለእነሱ ከልብ እንደምናስብላቸው ሲገነዘቡ አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጡበት አጋጣሚ ሰፊ ይሆናል።—ሥራ 2:46, 47

10 ዛሬ ምሥራቹን የመስበኩ ሥራ ተፈታታኝ ነው። አንዳንድ የምናነጋግራቸው ሰዎች የማያውቁትን ሰው ይጠራጠራሉ። ሌሎች ደግሞ ሩጫ የተሞላበት ሕይወት ስለሚመሩ ምንም ትርፍ ጊዜ የላቸውም። ሆኖም የሚገባቸው ገና ብዙ ሰዎች እንዳሉ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። (ማቴ. 10:11) አቀራረባችንን አጠር ካደረግንና “ፍሬ ነገሩን” የምንናገር ከሆነ እነሱን ለማግኘት የምናደርገው ጥረት የበለጠ ስኬታማ ይሆናል!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ