ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴ፦ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊ ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? እና የምትወዱት ሰው ሲሞት። የሚቀጥሉትን ብሮሹሮች ደግሞ ተስማሚ ሆኖ ሲገኝ ማበርከት ይቻላል:- ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ እና የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? መስከረም፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች ማበርከትና ኮንትራት ማስገባት። ኅዳር፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለው ብሮሹር ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለው መጽሐፍ።
◼ በዓመት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ልጆች ከትምህርት ቤት እንዲሁም ሠራተኞች ከሥራ ነፃ የሚሆኑባቸው ዓለማዊ በዓላት አሉ። እነዚህ ጊዜያት የጉባኤውን የመስክ አገልግሎት ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ግሩም አጋጣሚዎች ናቸው። ሽማግሌዎች በእነዚህ ጊዜያት ቀደም ብለው ዕቅድ በማውጣት በበዓል ቀናቱ ሊደረግ ስለታሰበው የመስክ አገልግሎት ዝግጅት ለጉባኤው አስቀድመው ማስታወቅ ይኖርባቸዋል።
◼ በ2,000 የአገልግሎት ዓመት የምትጠቀሙባቸው በቂ መጠን ያላቸው ቅጾች ለእያንዳንዱ ጉባኤ በመላክ ላይ ናቸው። እባካችሁ እነዚህን ቅጾች በአግባቡ ተጠቀሙባቸው። ለታቀደላቸው ዓላማ ብቻ መዋል ይኖርባቸዋል።
◼ እያንዳንዱ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (s-18-AM) ይደርሱታል። የጉባኤው ጸሐፊ በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎች የሚቆጠሩበትን ቀን ለመወሰን በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ የጽሑፍ አገልጋዩን ማነጋገር ይኖርበታል። በጉባኤው ውስጥ ያሉት ጽሑፎች ሁሉ አንድ በአንድ መቆጠር አለባቸው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጹ ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ መጽሔቶችን ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ ማግኘት ይቻላል። እባካችሁ ከመስከረም 6 በፊት ዋናውን ቅጂ ለማኅበሩ ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ ፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሥሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ጸሐፊው አብሮ መቁጠር ያለበት ሲሆን ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ደግሞ ተሠርቶ ያለቀውን ቅጽ መመርመር ይኖርበታል። ጸሐፊውና ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ቅጹ ላይ ይፈርማሉ።
◼ ጉባኤዎች በመስከረም ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ2,000 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ ማዘዝ ይኖርባቸዋል። የቀን መቁጠሪያው በአረብኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛና በጣልያንኛ ቋንቋዎች ይገኛል።