የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/00 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ኘሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ኘሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ግንቦት 8 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 15 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 22 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 29 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 5 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 5/00 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባዎች ኘሮግራም

ግንቦት 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 34 (77)

12 ደቂቃ:- የጉባኤና የመንግሥት አገልግሎታችን ማስታወቂያዎች። እስካሁን ባደረግነው ልዩ የአገልግሎት ክልል ዘመቻ ወቅት ምን እንደተከናወነና ምን ደግሞ መሠራት እንደሚቀረው የክልል አገልጋዩ ሪፖርት እንዲያቀርብ አድርግ። ከዚያም ሁሉም የአገልግሎት ክልሎችን በመሸፈኑ ሥራ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ። የቆዩ መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርገናል? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚያስችሉንን አጋጣሚዎች ለማግኘት በምናደርገው ጥረት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር እንጠቀማለንን?

15 ደቂቃ:- “ከምታቀርቡት ቅዱስ አገልግሎት ደስታ ማግኘት።” በንግግር የሚቀርብ። በአገልግሎታችን ለመደሰት የሚያበቁንን ምክንያቶች ተወያዩ።​—⁠ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ጥራዝ 2 ገጽ 120ን ተመልከት።

18 ደቂቃ:- “ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው የቅዱስ አገልግሎት መብቶች።” ለጉባኤው ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ነጥቦችን ከነሐሴ 1, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 25-29 ላይ መርጠህ አቅርብ። ከቤተሰባቸው አባላት አንዱ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለመካፈል የሚያስችለውን መንገድ እንዲፈልጉ ቤተሰቦችን አበረታታ። በተጨማሪም በጉባኤው ውስጥ ያሉት የተጠመቁ ወንድሞች መብት ለማግኘት መጣጣራቸው ያለውን አስፈላጊነት ጥቀስ።

መዝሙር 89 (201) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 65 (152)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ:- “አንድ ክርስቲያን ከቀብር ሥነ ሥርዓት ጋር ለተያያዙ ልማዶች የሚኖረው አመለካከት።” በሐምሌ 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20 እና 22-24 ላይ የተመሰረተ። ቀለል ያለ የቀብር ሥነ ሥርዓት ማድረጉም ሆነ ሐዘን የደረሰበት ቤተሰብ በስብሰባዎችና በመስክ አገልግሎት የመካፈል ቲኦክራሲያዊ ልማዱን ሳይዘገይ ለመቀጠል ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ ሁልጊዜም አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ለጉባኤው እንደሚስማማ አድርገህ አቅርብ። በገጽ 23 ላይ የሚገኘውን የመጨረሻ አንቀጽና በገጽ 24 ላይ የሚገኙትን ሁለት የመጨረሻ አንቀጾች አጉላ። ሌሊቱን ሙሉ ቁጭ ብሎ የማደር ልማድ ባለባቸው ቦታዎች በገጽ 21 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ጨምረህ መሸፈን ትችላለህ።

20 ደቂቃ:- “አምላክን በአንድነት የሚያገለግሉ ብዙ ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች” በሚል ርዕስ በየካቲት 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 9-12 ላይ የተመሰረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ቤተሰቦች ቋሚ የቤተሰብ ጥናት ሊኖራቸው የሚችለውና መላው ቤተሰብ መንፈሳዊ ግቦችን ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተል ማድረግ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ግለጽ። የመደምደሚያ ክለሳ ለማድረግ ሦስት ደቂቃዎች ያህል መድብ።

መዝሙር 21 (46) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 29 (62)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥኑን ከልስ።

20 ደቂቃ:- “ነቅታችሁ ኑሩ።” በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት። ቀንና ሰዓቱን ባናውቀውም በመንፈሳዊ ንቁዎች ሆነን መቆየታችን አጣዳፊ የሆነው ለምን እንደሆነ አብራራ።​—⁠የኀዳር 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20ን ተመልከት።

13 ደቂቃ:- “ ‘ብቁ መሆናቸው ይፈተን’​—⁠እንዴት?” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በጉባኤው ውስጥ የጉባኤ አገልጋዮችን ለማግኘት የተደረገውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ዝግጅት ከልስ። (ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ጥራዝ 2 ገጽ 409ን ተመልከት።) ለዚህ ኃላፊነት ለመብቃት እንዲያሟሉ የሚጠበቅባቸው ነገር ምን እንደሆነ ግለጽ። (አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 55-7 ተመልከት።) የጉባኤ አገልጋዮች ሊያገለግሉ የሚችሉባቸውን መስኮች ከጠቀስክ በኋላ ተጨማሪ ወንድሞች እዚህ መብት ላይ ለመድረስ እንዲጣጣሩ አበረታታ።

መዝሙር 83 (187) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 56 (135)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የግንቦት የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በሰኔ የሚበረከተውን ጽሑፍ በመጠቀም አንድ አጭር ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ከተባለው ብሮሹር ላይ ትምህርት 13ን በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደምንችል ግለጽ።

15 ደቂቃ:- “ራስህን ከልክ በላይ አታስጨንቅ” በሚል ርዕስ በወጣው የመጋቢት 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21-23 ላይ የተመሠረተ ንግግር። ነጥቦቹ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች ጠቁም። በመጨረሻም ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ከልስ።

18 ደቂቃ:- ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ። በትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 34-5 አንቀጽ 6-7 ላይ ተመስርቶ በንግግርና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። ጎላ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ነጥቦች የሚቀርቡበት መደበኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ኘሮግራም የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ሥርዓተ ትምህርት አካል ነው። አንድ ቤተሰብ ለዚህ ሳምንት የተመደበውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ኘሮግራም እንዴት መሸፈን ይችል እንደነበር ለማሳየት በተወሰኑት ምዕራፎች ላይ በቤተሰብ መልክ ውይይት ሲደረግ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። አንድ ወይም ሁለት ትኩረት የሚስቡ ነጥቦች ይመርጡና የመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎች ማውጫ ን ወይም ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል የተባለውን መጽሐፍ በመጠቀም ተጨማሪ ምርምር ያደርጋሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ‘የእውነትን ቃል በትክክል በመጠቀም’ ረገድ የተሻለ ብቃት እንዲኖረን በማድረግ የበለጠ ትርጉም አዘል ሊሆንልን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ግለጽ።​—⁠2 ጢ⁠ሞ. 2:​15 NW 

መዝሙር 71 (163) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 5 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 16 (37)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

12 ደቂቃ:- “ለይሖዋ የምናቀርበውን ውዳሴ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል አስደሳች መንገድ።” በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት።

15 ደቂቃ:- “ለልጆች ክፍት የሆነ የአገልግሎት መብት።” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በታኅሣሥ 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 13 አንቀጽ 15 ላይ የሚገኙትን ተሞክሮዎች ተናገር። ትንንሽ ልጆች መጽሔቶች በማሰራጨት እንዴት ደስታ እንዳገኙ እንዲናገሩ ጋብዝ። አንድ ወይም ሁለት ልጆች ከቤት ወደ ቤት ሄደው መጽሔት ሲያበረክቱ የሚያሳይ ቀለል ያለ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። በየሳምንቱ በሚደረገው የመጽሔት ቀን ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘዋቸው እንዲሄዱ አበረታታ።

13 ደቂቃ:- ትምህርት ቤት ሲዘጋ የዕረፍት ጊዜያችሁን እንዴት ልትጠቀሙበት አስባችኋል? አንድ ቤተሰብ በእነዚህ ወራት ምን እንደሚያደርግ ይወያያል። በመንፈሳዊ ጽሑፎች ላይ ተጨማሪ የግል ጥናት ለማድረግ እንዲሁም ለአንድ ወይም ከአንድ ለሚበልጡ ወራት በረዳት አቅኚነት ለማገልገል በሚያስችል ኘሮግራም ላይ ይነጋገራሉ። ውብና ማራኪ የሆነ መናፈሻ ቦታ የመጎብኘት ወይም ጤናማ በሆነ መዝናኛ የመካፈል አጋጣሚም ሊኖር ይችላል። ሁሉም ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴያቸውን ችላ ላለማለት ይስማማሉ።

መዝሙር 37 (82) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ