ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የጽሑፍ ክለሳ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከግንቦት 1 እስከ ነሐሴ 21, 2000 በነበሩት ሳምንታት በተሰጡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ መጽሐፍ ተዘግቶ የሚደረግ የጽሑፍ ክለሳ። በሌላ ወረቀት ተጠቅመህ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የቻልከውን ያህል ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ስጥ።
[ማሳሰቢያ:- በጽሑፍ ክለሳው ወቅት ለማንኛውም ጥያቄ መልስ ለመፈለግ ማየት የሚፈቀደው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው። በቅንፍ ውስጥ የተጠቀሱት ጽሑፎች በግልህ ምርምር እንድታደርግባቸው የቀረቡ ናቸው። የትኛው መጠበቂያ ግንብ እንደሆነ በሚጠቀስበት ጊዜ አንቀጹ የተሰጠው በሁሉም ቦታ ላይ አይደለም።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር እውነት ወይም ሐሰት እያልክ መልስ:-
1. ጌዴዎን የኤፍሬም ሰዎች ለሰነዘሩበት መሠረተ ቢስ ውንጀላ የሰጣቸው መልስ ቁጡ አለመሆኑንና ትሕትናውን የሚያንጸባርቅ ከመሆኑም በላይ አግባብ ያልሆነውን ወቀሳቸውን ውድቅ ለማድረግና ሰላሙን ለመጠበቅ አስችሎታል። (መሳ. 8:1-3) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ]
2. ምንም እንኳ ማኑሄ “እግዚአብሔርን አይተናል” ቢልም እንደ እውነቱ ከሆነ እሱና ሚስቱ ያዩት ራሱን ይሖዋን ሳይሆን ሥጋ የለበሰውን የግል ቃል አቀባዩን ነው። (መሳ. 13:22) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w E88 5/15 ገጽ 23 አን. 3ን ተመልከት።]
3. መሳፍንት 5:31 ላይ የሚገኘው “ወዳጆችህ” የሚለው መግለጫ በትንቢታዊ ሁኔታ 144, 000 የመንግሥቱን ወራሾች ይወክላል። [si ገጽ 50 አን. 28]
4. ከሙት ባሕር ጥቅልሎች መካከል አንድም የሩት መጽሐፍ ቁርጥራጭ አልተገኘም። [si ገጽ 51 አን. 3]
5. መሳፍንት 21:25 ይሖዋ ለእስራኤል ብሔር ምንም ዓይነት አመራር ከመስጠት የተቆጠበበትን ጊዜ ያመለክታል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 6/15 ገጽ 22 አን. 16ን ተመልከት።]
6. በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ የተቀመጡት የኪሩቤል ምስሎች ‘በኪሩቤል ላይ [ወይም “መካከል”] እንደሚቀመጥ’ የተነገረውን የይሖዋን በንጉሣዊ ሥልጣን መገኘት ያመለክቱ ነበር። (1 ሳሙ. 4:4፣ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ።) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w E80 11/1 ገጽ 29 አን. 2ን ተመልከት።]
7. የሳኦል ወታደሮች በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ደም በልተው ሳይቀጡ መቅረታቸው አንድ ሰው ሕይወቱን ለማትረፍ ሲል ለጊዜው መለኮታዊ ሕግ እንዲጥስ የሚፈቅዱለት አጥጋቢ ምክንያቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ያሳያል። (1 ሳሙ. 14:24-35) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w94 4/15 ገጽ 31 አን. 7-9ን ተመልከት።]
8. ምንም እንኳ አንዳንዶች “ማሳመን” የሚለውን ቃል በዘዴ ከማግባባት ወይም ከብልጠት ጋር ቢያያይዙትም ትክክለኛና አሳማኝ ማስረጃ በማቅረብ የማሳመንንና አስተሳሰብን የመለወጥ ሐሳብ ለማስተላለፍ አዎንታዊ በሆነ መንገድ ሊሠራበት ይችላል። (2 ጢሞ. 3:14, 15 NW ) [w98 5/15 ገጽ 21 አን. 4]
9. “የሕይወት ከረጢት፣” ዳዊት በአምላክ ዓይን ከደም ዕዳ ከራቀ ከመለኮታዊ ጥበቃና ከለላ የሚያገኘውን ጥቅም የሚያመለክት ዝግጅት ነው። (1 ሳሙ. 25:29 NW ) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w91 6/15 ገጽ 14 አን. 3ን ተመልከት።]
10. ሁለተኛ ሳሙኤል 7:16 ላይ የተጠቀሰው የዳዊት የመንግሥት ቃል ኪዳን ወደ መሲሑ የሚያደርሰውን የዘሩን መስመር ከማጥበቡም በተጨማሪ “ለዘላለም” የሚገዛ አንድ ንጉሥ በዳዊት መስመር እንደሚመጣ የተሰጠ ሕጋዊ ዋስትና ነበር። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w3-110 ገጽ 14 አን. 21–ገጽ 15 አን. 22ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ:-
11. መዝሙር 34:18 ምን ማረጋገጫ ይሰጠናል? [w98 4/1 ገጽ 31 አን. 2]
12. ለዮሴፍ በርናባስ የሚል ቅጽል ስም መሰጠቱ ምን ያመለክታል? (ሥ.ራ 4:36) [w98 4/15 ገጽ 20 አን. 3፣ የግርጌ ማስታወሻ።]
13. የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ዔሊ ከይሖዋ ይልቅ ልጆቹን እንዳከበረ የሚናገረው ለምንድን ነው? (1 ሳሙ. 2:12, 22-24, 29) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w96 9/15 ገጽ 13 አን. 14ን ተመልከት።]
14. መጽሐፈ ሩት በመንግሥቱ ተስፋዎች ላይ ያለንን ትምክህት ሊያጠናክርልን የሚገባው ለምንድን ነው? [si ገጽ 53 አን. 10]
15. በ1 ሳሙኤል 1:1-7 መሠረት የሳሙኤል ቤተሰብ ምን የላቀ ምሳሌ ትቷል? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w98 3/1 ገጽ 16 አን. 12ን ተመልከት።]
16. ‘ባለጠግነት የማታለል ኃይል አለው’ ሊባል የሚችለው ከምን አንጻር ነው? (ማቴ. 13:22) [w98 5/15 ገጽ 5 አን. 1]
17. በዕድሜ ታላቁ የነበረው ዮናታን ይሖዋ ለቀባው ለዳዊት ዕውቅና መስጠቱን ያሳየው እንዴት ነው? ይህስ በዛሬው ጊዜ ለምን ነገር ጥላ ይሆናል? (1 ሳሙ. 18:1, 3, 4) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w1-110 ገጽ 18, 19 አን. 4, 13ን ተመልከት።]
18. ምንም እንኳ ኢዮብ “እንከን የለሽና ቅን” የነበረ ቢሆንም ፍጹም ነበር ማለት እንዳልሆነ የኢዮብ መጽሐፍ የሚያሳየው እንዴት ነው? (ኢዮብ 1:8) [w98 5/1 ገጽ 31 አን. 1]
19. “ተጋደሉ” የሚለው ቃል ምን መልዕክት ያስተላልፋል? (ሉቃስ 13:24) [w98 6/15 ገጽ 31 አን. 1, 4]
20. ከሌሎች ጋር አብረን ስንሠራ በ2 ሳሙኤል 12:26-28 ላይ በተመዘገበው መሠረት ምን ጠቃሚ ትምህርት ማግኘት እንችላለን? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w93 12/1 ገጽ 19 አን. 19ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር የሚያሟላውን ቃል ወይም ሐረግ ስጥ:-
21. ይሖዋ የበኣል አምልኮን ክፉኛ ማውገዙ በዘመናችን ካሉት ተመሳሳይ ነገሮች ማለትም ___________________________ ፣ ________________________________ እና _______________________________ እንድንርቅ ሊገፋፋን ይገባል። (መሳ. 2:11-18) [si ገጽ 50 አን. 26]
22. የ______________________________ ዘመን ወደ ማብቂያው የመጣው በሳሙኤል ጊዜ ሲሆን ከዚያም __________________________ የሚገዙበት ዘመን የጀመረውና በመጨረሻም እስራኤል የይሖዋን ሞገስ ያጣችው በዚሁ ዘመን ነበር። [si ገጽ 53 አን. 1]
23. ይሖዋ የሚለው መለኮታዊ ስም _________________________ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ይሖዋ _________________________ ለማሳካት ሲል የፈለገውን እንደሚሆን የሚያመለክት ሐሳብ አለው። [w98 5/1 ገጽ 5 አን. 3]
24. ዔሊና ሳኦል ለውድቀት የተዳረጉት ዔሊ እርምጃ ለመውሰድ _________________________ በመሆኑ ሲሆን ሳኦል ደግሞ _____________________________ በማድረጉ ነው። [si ገጽ 57 አን. 27]
25. ኢየሱስ ስለ ደጉ ሳምራዊ የሰጠው ምሳሌ እንደሚያሳየው ትክክል የሆነውን ነገር ከልቡ የሚሠራ ሰው የአምላክን _________________________ መታዘዝ ብቻ ሳይሆን _________________________ ይኮርጃል። (ሉቃስ 10:29-37) [w98 7/1 ገጽ 31 አን. 2]
ቀጥሎ ላለው ለእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ትክክለኛውን መልስ ምረጥ:-
26. ቀድሞ የ(በአል፣ ኬሞሽ፣ ዳጎን) አምላኪ የነበረችው ሞአባዊቷ (ሩት፣ ናኦሚ፣ ኦርፋ) ወደ እውነተኛው አምልኮ መጥታ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ አያት እንድትሆን መመረጧ የይሖዋ የ(ጥበብ፣ ኃይል፣ ፍቅር) ባሕርይ ምን ያህል ሰፊ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። (ማቴ. 1:3, 5, 16) [si ገጽ 51 አን. 1]
27. እስራኤል በመሳፍንት ትገዛበት የነበረው ዘመን ያበቃው (ሳሙኤል፣ ዳዊት፣ ሳኦል) ንጉሥ ሆኖ በተቀባበት ጊዜ ሲሆን ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በይሖዋ ድጋፍ (አሞናውያንን፣ ሞአባውያንን፣ ፍልስጤማውያንን) ድል አድርጓል። (1 ሳሙ. 11:6, 11) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 12/15 ገጽ 9 አን. 2–ገጽ 10 አን. 1ን ተመልከት።]
28. ጢሞቴዎስ የተዋጣለት ሚስዮናዊ እና የበላይ ተመልካች ለመሆን እስኪበቃ ድረስ “ቅዱሳን መጻሕፍትን” በማስተማር ረገድ ግንባር ቀደም የነበሩት (ሐዋርያው ጳውሎስ፣ አባቱ፣ እናቱና አያቱ) ናቸው። (2 ጢሞ. 3:14, 15፤ ፊልጵ. 2:19-22) [w98 5/15 ገጽ 8 አን. 3–ገጽ 9 አን. 5]
29. (ዳዊት፣ ሳሙኤል፣ ዮናታን) በወጣትነቱ ያከናወነው አገልግሎት ዛሬ ወጣቶች አገልግሎት እንዲጀምሩ ሊያበረታታቸው የሚገባ ሲሆን እስከ ሕይወቱ ማብቂያ ድረስ አገልግሎቱን ሳያቋርጥ መቀጠሉ ደግሞ በዕድሜ የገፉትን ሊያበረታታቸው ይገባል። [si ገጽ 58 አን. 30]
30. ሁለተኛ ሳሙኤል የሚሸፍነው የጊዜ ርዝመት ከ (1077 እስከ 1040 ገደማ፣ 1077 እስከ 1037 ገደማ፣ 1070 እስከ 1040 ገደማ) ከዘአበ ነው። [si ገጽ 59 አን. 3]
ቀጥሎ ያሉትን ጥቅሶች ከታች ካሉት ሐሳቦች ጋር አዛምድ:-
መሳ. 11:30, 31፤ 1 ሳሙ. 15:22፤ 30:24, 25፤ 2 ነገ. 6:15-17፤ ያዕ. 5:11
31. ይሖዋ ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ መንገድ ሕዝቡን ለመጠበቅ ሰማያዊ ሠራዊቱን እንደሚጠቀም ማረጋገጫ ሰጥቶናል። [w98 4/15 ገጽ 29 አን. 5]
32. ምንም እንኳ አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ሊሆንባቸውና ብዙ ወጪ ሊጠይቅባቸው ቢችልም የጉባኤ የበላይ ተመልካቾች የገቡትን የስምምነት ቃል የማክበር ኃላፊነት አለባቸው። [w99 9/15 ገጽ 10 አን. 3-4]
33. በፈተና ሥር ንጹሕ አቋም መጠበቅ ከይሖዋ አምላክ ዘንድ ታላቅ በረከት ያስገኛል። [w98 5/1 ገጽ 31 አን. 4]
34. ለአምላክ ልባዊ ፍቅር ማሳየት ለእሱ መሥዋዕት እንድናቀርብ ብቻ ሳይሆን መለኮታዊ መመሪያዎችን እንድንታዘዝም ይጠይቅብናል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w96 6/15 ገጽ 5 አን. 1ን ተመልከት።]
35. ይሖዋ በዛሬው ጊዜ በድርጅቱ ውስጥ እገዛ ለሚያደርጉት ሁሉ ጥልቅ አድናቆት ያሳያል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 9/1 ገጽ 28 አን. 4ን ተመልከት።]