የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/00 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ነሐሴ 14 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 21 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 28 የሚጀምር ሳምንት
  • መስከረም 4 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 8/00 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

ነሐሴ 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 49 (114)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በአገሪቱና በጉባኤው የግንቦት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት ላይ ሐሳብ ስጥ። ወሩ ሊያልቅ የቀሩት ሁለት ቅዳሜና እሁዶች ብቻ ናቸው። ስለዚህ ወሩ ከማለቁ በፊት ሁሉም በአገልግሎት እንዲካፈሉ አበረታታ። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ለማድረግ የታቀዱትን የመስክ ስምሪት ስብሰባዎች ጥቀስ።

15 ደቂቃ:- ‘መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ።’ አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ክፍሉን በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአገልግሎታችን መጽሐፍ ከገጽ 44-5 ላይ የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት መሪዎች በቂ የአገልግሎት ክልል መኖሩን በማረጋገጥ ለቡድኖቻቸው የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴ ማደራጀት የሚችሉበትን መንገድ በተመለከተ የተሰጡትን ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ። በተጨማሪም የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች ዘወትር በአገልግሎቱ መካፈልና ሪፖርት መመለስ ይችል ዘንድ የግል እርዳታ ለሚያስፈልገው ሰው ሁሉ ትኩረት ይሰጣሉ።

18 ደቂቃ:- ትምህርት ቤት በመሄዳችሁ የምትጠቀሙት እንዴት ነው? አንድ አባት ዓለማዊ ትምህርት ጠቃሚ የሆነበትን ምክንያት እንዲገነዘቡ ለመርዳት ከልጆቹ ጋር ውይይት ያደርጋል። (ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የሚለውን መጽሐፍ ከገጽ 133-9 ተመልከት።) ብዙ ወጣቶች በዛሬው ጊዜ ባለው ሥርዓት አልበኛ የሆነ ኅብረተሰብ ውስጥ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ በጣም ፈታኝ እንደሆነ ይሰማቸዋል። በተጨማሪም የሚማሩት ነገር ምንም ዓይነት ተግባራዊ ጥቅም እንደማይሰጣቸው ሆኖ ስለሚሰማቸው መማሩ አሰልቺ ይሆንባቸዋል። አባትየው የተሟላ ዓለማዊ ትምህርት ማግኘት ጥበብ የሆነበትን ምክንያት በግልጽ የሚያሳዩ ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶችና ጠንካራ ማስረጃዎች ይጠቅሳል። አባትየው ልጆቹ በሚገባ እንዲያጠኑና በክፍል ውስጥ ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉ ያበረታታቸዋል።

መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 60 (143)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በመስክ አገልግሎት ላይ “የፍቅር አምላክ ይህን ለሚያህል ጊዜ መከራ እንዲቀጥል የፈቀደው ለምንድን ነው?” በማለት ለሚቀርብልን ጥያቄ መልስ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ የሚያሳይ ጥሩ ልምምድ የተደረገበት ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። (ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 394-5) በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ሁሉም በአገልግሎት እንዲካፈሉ አበረታታ።

10 ደቂቃ:- ያለንበት ወቅት ልዩ ነው። በኀዳር 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22-3 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

25 ደቂቃ:- “ራሳችሁን እየጠቀማችሁ ነውን?” ጥያቄና መልስ።

መዝሙር 65 (152) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 57 (136)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የነሐሴን የመስክ አገልግሎት ሪፖርት እንዲመልሱ አስታውሳቸው። ሁሉም ሪፖርቶች ከመስከረም 6 በፊት ተሰብስበው እንዲላኩ የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት መሪዎች በቡድናቸው ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው ሪፖርት መመለሱን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።

17 ደቂቃ:- “ቅዱስ ነገሮችን ታደንቃላችሁን?” የክለሳ ጥያቄዎች ያሉት ንግግር።

20 ደቂቃ:- “ስብሰባዎች ለወጣቶች ጠቃሚ ናቸው።” በሽማግሌ የሚመራ በጥ​ያቄና መልስ የሚቀርብ ውይይት። አንቀጽ 8ን ስትወያዩ በስብሰባዎች ወቅት ይበልጥ በትኩረት ለመከታተልና በንቃት ለማዳመጥ የሚረዱ ተግባራዊ ሐሳቦች ጥቀስ። (የኅዳር 1998 ንቁ! ከገጽ 13-4 ተመልከት።) ወላጆች ልጆቻቸው በሁሉም ስብሰባዎች ላይ አዘውትረው እንዲገኙ በማድረግ በኩል ጥብቅ እንዲሆኑ አበረታታ።​—⁠በመስከረም 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 25 ላይ የወጣውን ተሞክሮ ተመልከት።

መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መስከረም 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 90 (204)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥን። አስፋፊዎች ተመላልሶ መጠየቅ በሚያደርጉበት ወቅት ያጋጠሟቸውን አዎንታዊ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ አድርግ።

17 ደቂቃ:- “ቅዱሱን ቃል በጥሞና ተከታተሉ።” ጥያቄና መልስ። አንቀጽ 3 እና 4ን አንብብ።

20 ደቂቃ:- “ጽናት እያሳያችሁ ነውን?” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ሁሉም በክርስቲያናዊ አገልግሎት ጽናት በማሳየት ረገድ በግል ባገኙት ስኬት ላይ እንዲያሰላስሉ አበረታታ። ድክመታችንን በግልጽ ካስተዋልን ራሳችንን በመንፈሳዊ ማጠንከር ያስፈልገናል። በጥቅምት 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20-1 ከአንቀጽ 17-21 ድረስ ያሉትን ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ። በታማኝነት ለብዙ ዓመታት የጸኑ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ጋብዝና በጽናት ለመቀጠል ምን እያደረጉ እንዳሉ እንዲናገሩ አድርግ።

መዝሙር 19 (43) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ