ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የጽሑፍ ክለሳ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከግንቦት 7 እስከ ነሐሴ 20, 2001 በነበሩት ሳምንታት በተሰጡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ መጽሐፍ ተዘግቶ የሚደረግ የጽሑፍ ክለሳ። በሌላ ወረቀት ተጠቅመህ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የቻልከውን ያህል ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ስጥ።
[ማሳሰቢያ:- በጽሑፍ ክለሳው ወቅት ለማንኛውም ጥያቄ መልስ ለመፈለግ ማየት የሚፈቀደው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው። በቅንፍ ውስጥ የተጠቀሱት ጽሑፎች በግልህ ምርምር እንድታደርግባቸው የቀረቡ ናቸው። የትኛው መጠበቂያ ግንብ እንደሆነ በሚጠቀስበት ጊዜ አንቀጹ የተሰጠው በሁሉም ቦታ ላይ አይደለም።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር እውነት ወይም ሐሰት እያልክ መልስ:-
1. ነህምያ 2:4 ላይ የተጠቀሰው ጸሎት ባለቀ ሰዓት ላይ የቀረበ የጭንቅ ጸሎት ነው። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 2/15 ገጽ 25 አን. 8ን ተመልከት።]
2. በግሪክኛ የክርስቲያን ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ “ጉባኤ” የሚለው ቃል ኤክሊሲአ ከተባለው የግሪክኛ ቃል የተተረጎመ ሲሆን ቃሉ መተባበርና በጋራ መደጋገፍ የሚሉ ሐሳቦችን ያስተላልፋል። [w99 5/15 ገጽ 25 አን. 4]
3. የይሖዋ አገልጋዮች ከሞት ጋር የተያያዙ ከአምላክ ቃል ጋር የሚጋጩ ልማዶችን ቢርቁም እንኳ ከሞት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ልማዶች በሙሉ አይቃወሙም። (ዮሐ. 19:40) [rs ገጽ 102 አን. 4]
4. ኢዮብ በኖረበት ዘመን ለይሖዋ ታማኝ የነበረ ሰው እሱ ብቻ ነው። (ኢዮብ 1:8) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w92 8/1 ገጽ 31 አን. 3-4ን ተመልከት።]
5. ሳውል ወይም ጳውሎስ ድንኳን በመስፋት ራሱን መደገፉ ከድሀ ቤተሰብ የመጣ መሆኑን ያሳያል። (ሥራ 18:2, 3) [w99 5/15 ገጽ 30 አን. 2–ገጽ 31 አን. 1]
6. ምንም እንኳ ዳዊት ከባድ ኃጢአቶች ቢፈጽምም ንስሐ ስለገባና ጥሩ ባሕርያት ስለነበሩት ይሖዋ ‘በፍጹም ልቡ ተከትሎኛል’ ሊል ችሏል። (1 ነገ. 14:8) [w99 6/15 ገጽ 11 አን. 5]
7. ከጊዜ በኋላ ቃላችንን መጠበቅ ቢከብደንም እንኳ ቃል የገባነው ነገር ከቅዱስ ጽሑፉ ጋር የሚጋጭ እስካልሆነ ድረስ የገባነውን ቃል ለመፈጸም የቻልነውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል። (መዝ. 15:4) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w18-110 ገጽ 23 አን. 6ን ተመልከት።]
8. መዝሙር 22:1 ዳዊት በጭንቀት ተውጦ እያለ ለጊዜው እምነት ማጣቱን ያሳያል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 8/15 ገጽ 20 አን. 19ን ተመልከት።]
9. አንድ ክርስቲያን ካደረበት የተስፋ መቁረጥ ስሜት፣ ካጋጠመው አሳዛኝ ሁኔታ እንዲሁም ከደረሰበት የፍትሕ መጓደል ወይም የኢኮኖሚ ድቀት የተነሳ “ቢወድቅም” እንኳ ከአምላክ መንፈስና አፍቃሪ ከሆኑ አምላኪዎቹ እርዳታ ስለሚያገኝ በመንፈሳዊ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ “ለድንጋፄ አይጣልም።” (መዝ. 37:23, 24) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 11/1 ገጽ 30 አን. 14ን ተመልከት።]
10. ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 አምላክ በዚች ምድር ላይ ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ የፈጠረው የ24 ሰዓት ርዝመት ባላቸው ስድስት ቀናት ውስጥ መሆኑን ይናገራል። [rs ገጽ 126 አን. 4]
ቀጥሎ ላሉት ጥያቄዎች መልስ ስጥ:-
11. ዕዝራና ረዳቶቹ ሕጉን ‘ያስታውቁ’ የነበረው እንዴት ነው? (ነህ. 8:8) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 2/15 ገጽ 26 አን. 4ን ተመልከት።]
12. ‘የይሖዋ ደስታ’ የሚገኘው እንዴት ነው? (ነህ. 8:10) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 2/15 ገጽ 26 አን. 9ን ተመልከት።]
13. ‘በፈቃዳቸው በኢየሩሳሌም ለመቀመጥ የወደዱ’ ሰዎች የተባረኩት ለምንድን ነው? (ነህ. 11:2) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 2/15 ገጽ 26 አን. 12ን ተመልከት።]
14. አስቴር የምትፈልገውን ነገር ለንጉሡ ወዲያው ያላሳወቀችው ለምን ነበር? (አስቴር 5:6-8) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 3/15 ገጽ 24 አን. 18ን ተመልከት።]
15. የኢዮብ መጽሐፍ መልስ የሚሰጥባቸው ሁለት ዓበይት ጥያቄዎች የትኞቹ ናቸው? [si ገጽ 95 አን. 1]
16. ኤልፋዝ የሰጠው ምክር ኢዮብን ተስፋ ያስቆረጠውና ሳያጽናናው የቀረው ለምንድን ነው? (ኢዮብ 21:34፤ 22:2, 3) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 2/15 ገጽ 27 አን. 5-6ን ተመልከት።]
17. መዝሙር ምንድን ነው? [si ገጽ 101 አን. 2]
18. መዝሙር 2:1 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው ብሔራት ‘የሚናገሩት’ “ከንቱ” ነገር ምንድን ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 8/15 ገጽ 20 አን. 5ን ተመልከት።]
19. ፊልጶስ ለሳምራውያንና ለኢትዮጵያዊው ባለሥልጣን ከሰጠው አገልግሎት አለማዳላትን በተመለከተ ምን ተግባራዊ ትምህርት ማግኘት እንችላለን? (ሥራ 8:6-13, 26-39) [w99 7/15 ገጽ 25 አን. 2]
20. ኢዮብ ከደረሰበት ሥቃይ ተሸሽጎ የሚቀመጥበት ቦታ እንደሆነ አድርጎ ከቆጠረው ከመቃብር አምላክ ሊያስነሣው እንደሚችል ያለውን የጸና እምነት በምሳሌ የገለጸው እንዴት ነው? (ኢዮብ 14:7, 13-15) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w00 5/15 ገጽ 27 አን. 7–ገጽ 28 አን. 1ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር የሚያሟላውን ቃል ( ቃላት) ወይም ሐረግ ስጥ:-
21. አስቴር 8:17 ብዙ ሰዎች ‘አይሁድ ነን እንዳሉ’ ይናገራል። በተመሳሳይም ዛሬ “ሌሎች በጎች” የሆኑ “ _________________________ ” ከ_________________________ ጎን ተሰልፈዋል። (ራእይ 7:9፤ ዮሐ. 10:16፤ ዘካ. 8:23) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 3/15 ገጽ 25 አን. 14ን ተመልከት።]
22. ሥራ 1:7 እንደሚያሳየው ይሖዋ _________________________ በጥንቃቄ የሚጠብቅ ቢሆንም እንኳ የፍርዱ ቀን የሚመጣው እንደ _________________________ ሰዎች ባልጠበቁት ጊዜ ነው። (2 ጴጥ. 3:10) [w99 6/1 ገጽ 5 አን. 1-2]
23. ሁለተኛ ጴጥሮስ 3:7, 10 ላይ የሚገኙት “ሰማያት” እና “ምድር” የሚሉት ቃላት _________________________ የተሠራባቸው ሲሆን “ምድር” _________________________ እንደሚያመለክት በጥቅሱ ዙሪያ ያለው ሐሳብ ያሳያል። [rs ገጽ 114 አን. 4–ገጽ 115 አን. 2]
24. መተማመንና የጋራ መግባባት ካለ ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት ማድረግ ይቻላል። እንዲህ ያሉት ባሕርያት የሚመጡት ጋብቻን _________________________ ዝምድና አድርገው ሲመለከቱትና የተሳካ እንዲሆንም ልባዊ _________________________ ሲኖር ነው። [w99 7/15 ገጽ 21 አን. 3]
25. እኩዮች የሚያሳድሩት በጎ ተጽዕኖ ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ ደንቦችን _________________________ እንድናደርግና ይሖዋን _________________________ እንድናገለግል ሊረዳን ይችላል። [w99 8/1 ገጽ 24 አን. 4]
ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ትክክለኛውን መልስ ምረጥ:-
26. መርዶክዮስ ‘በንጉሡ በር መቀመጡ’ (የንጉሡ አጃቢ፤ ከንጉሥ አሕሻዊሮስ ሹማምት መካከል አንዱ፤ ንጉሡ ዘንድ ለመግባት እየተጠባበቀ) መሆኑን ያሳያል። (አስቴር 2:19, 20) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 3/15 ገጽ 24 አን. 9ን ተመልከት።]
27. ኢዮብ 19:25-27 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው ኢዮብ ‘እግዚአብሔርን እንደሚያይ’ ያለውን እምነት መግለጹ (የማየት አጋጣሚ እንደሚሰጠው፤ ለሰማያዊ ሕይወት ትንሣኤ እንደሚያገኝ፤ ስለ ይሖዋ እውነቱ ምን እንደሆነ መረዳት እንዲችል የማስተዋል ዓይኑ እንደሚከፈት) መናገሩ ነበር። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w94 11/15 ገጽ 19 አን. 17ን ተመልከት።]
28. ኢዮብ በይበልጥ የሚታወሰው (በፍቅሩ፣ በደግነቱ፣ በጽናቱ) ነው። (ያዕ. 5:11) [si ገጽ 100 አን. 41]
29. የመዝሙር መጽሐፍ የተጻፈበት የጊዜ ርዝመት (ሦስት መቶ፤ አምስት መቶ፣ አንድ ሺህ) ዓመት ገደማ ነው። [si ገጽ. 101 አን. 4]
30. የመዝሙር መጽሐፍን ያጠናቀረው የመጨረሻው ሰው (ዳዊት፣ አሳፍ፣ ዕዝራ) እንደሆነ ከሁኔታዎቹ መረዳት ይቻላል። [si ገጽ 102 አን. 6]
ቀጥሎ ያሉትን ጥቅሶች ከታች ካሉት ሐሳቦች ጋር አዛምድ:-
ነህ. 3:5፤ መዝ. 12:2፤ 19:7፤ 2 ጢሞ. 3:16, 17፤ ያዕ. 5:14-16
31. የጉልበት ሥራ ክብራችንን ዝቅ እንደሚያደርግ በማሰብ በኩራት መንፈስ ከመራቅ ይልቅ ራሳችንን ለማቅረብ ፈቃደኞች መሆን አለብን። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ wE86 2/15 ገጽ 25 አን. 12, 19ን ተመልከት።]
32. ከባድ ስሕተት የፈጸመ አንድ ክርስቲያን ኃጢአቱን ለሽማግሌዎች መናዘዝ አለበት። [rs ገጽ 82 አን. 7]
33. አምላክ በጥንት ዘመን ለሕዝቦቹ ማስጠንቀቂያ፣ መመሪያና ትንቢት ለማስተላለፍ በሕልም የተጠቀመ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ግን መዳን እንድናገኝ ይህን የሚሰጠን በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው ቃሉ አማካኝነት ነው። [rs ገጽ 106 አን. 1]
34. የአምላክ ወዳጅ መሆን ከፈለግን ግብዝነትን አስወግደን ከልባችን ሐቀኞች መሆን አለብን። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w18-110 ገጽ 22 አን. 1ን ተመልከት።]
35. ለአምላክ ሕግ ታዛዥ መሆን አንድ ሰው ነፍሱ እንዲታደስና መንፈሳዊነቱ እንዲሻሻል ያደርጋል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w00 10/1 ገጽ 13 አን. 4ን ተመልከት።]