“እንዴት ይሰማሉ?”
1 ኢየሱስ “አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል” በማለት አጥብቆ ተናግሯል። (ማር. 13:10) ትጋት የተሞላበት ጥረት ብናደርግም በግለሰብ ደረጃ ምሥክርነቱ ያልደረሳቸው በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ። አንዳንድ መንግሥታት በሥራችን ላይ እገዳ ጥለዋል። ብዙ አገሮች በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ የሚሄድ የሕዝብ ብዛት አላቸው። ታዲያ “እንዴት ይሰማሉ?”—ሮሜ 10:14
2 በይሖዋ ላይ ትምክህት ይኑራችሁ:- ይሖዋ የሰዎችን የልብ ሁኔታ እንደሚያውቅ መዘንጋት የለብንም። ግለሰቡ ያለበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ስለ አምላክ እውነቱን ለማወቅ ልባዊ ጥረት ካደረገ ያገኘዋል።—1 ዜና 28:9
3 አብርሃም የሰዶምና የገሞራ ነዋሪዎች እጣ አሳስቦት ነበር። ነገር ግን አምላክ በሰዶም ውስጥ አሥር ጻድቃን ሰዎች እንኳ ከተገኙ ከተማይቱ እንደማትጠፋ ማረጋገጫ ሰጠው። (ዘፍ. 18:20, 23, 25, 32) የሎጥና የሴቶች ልጆቹ መዳን እንደሚያሳየው ይሖዋ ጻድቃንን ከክፉዎች ጋር በፍጹም አያጠፋም።—2 ጴጥ. 2:6-9
4 ኤልያስ በአንድ ወቅት እውነተኛውን አምላክ እያገለገለ ያለው ብቻውን እንደሆነ ተሰምቶት ነበር። ይሁን እንጂ ብቻውን እንዳልሆነና የጀመረው ሥራም ፍጻሜ እንደሚያገኝ ይሖዋ አረጋገጠለት። (1 ነገ. 19:14-18) በዘመናችን ስላለው ሁኔታስ ምን ለማለት ይቻላል?
5 በአምላክ አገልግሎት እንደተጠመዳችሁ ቀጥሉ:- የምሥክርነቱ ሥራ ገና ምን ያህል መሠራት እንደሚቀረው አናውቅም። የዚህ ሥራ ኃላፊ ይሖዋ ሲሆን ሥራውን በበላይነት እንዲቆጣጠሩ መላእክቱን እየተጠቀመ ነው። (ራእይ 14:6, 7) ለአሕዛብ ሁሉ ምስክርነቱ መሰጠት ያለበት እስከ ምን ድረስ እንደሆነ የሚወስነው እሱ ነው። ይሖዋ ከፈለገ ብዙ ሰዎች “የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ” እኛ ልንገምተው በማንችለው መንገድ ተጠቅሞ የመንግሥቱ መልእክት እንዲሰራጭ ሊያደርግ ይችላል። (ሥራ 15:7) ይሖዋ የሚያደርገው ሁሉ ከባሕርያቱ ማለትም ከፍቅሩ፣ ከጥበቡና ከፍትሑ ጋር የሚስማማ ይሆናል።
6 እያንዳንዱ ሰው ምሥራቹን እንዲሰማ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ከይሖዋ ፈቃድ ጋር ተስማምተን መሥራታችን ለእኛ መብት ነው።—1 ቆሮ. 9:16