ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የጽሑፍ ክለሳ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከጥር 7 እስከ ሚያዝያ 22, 2002 በነበሩት ሳምንታት በተሰጡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ መጽሐፍ ተዘግቶ የሚደረግ የጽሑፍ ክለሳ። በሌላ ወረቀት ተጠቅመህ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የቻልከውን ያህል ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ስጥ።
[ማሳሰቢያ:- በጽሑፍ ክለሳው ወቅት ለማንኛውም ጥያቄ መልስ ለመፈለግ ማየት የሚፈቀደው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው። በቅንፍ ውስጥ የተጠቀሱት ጽሑፎች በግልህ ምርምር እንድታደርግባቸው የቀረቡ ናቸው። የትኛው መጠበቂያ ግንብ እንደሆነ በሚጠቀስበት ጊዜ አንቀጹ የተሰጠው በሁሉም ቦታ ላይ አይደለም።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር እውነት ወይም ሐሰት እያልክ መልስ:-
1. በመክብብ 2:2 ላይ ሰሎሞን ሳቅና ደስታ መቅረት እንዳለበት ማመልከቱ ነበር። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w87 9/15 ገጽ 24 አን. 5ን ተመልከት።]
2. መክብብ አሉታዊ አመለካከት የሰፈረበት መጽሐፍ ሳይሆን መለኮታዊ ጥበብ በያዙ ውድ እውነቶች የተሞላ በመሆኑ አምላክን ችላ የሚሉ ሰዎች የጥፋት አካሄድ እንደያዙ ያሳያል። [si ገጽ 114 አን. 15]
3. ኢሳይያስ 1:7 ላይ ነቢዩ በአካዝ የንግሥና ዘመን በይሁዳ ላይ የደረሰውን ጥፋት ተናግሯል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ ip-1 ገጽ 17 አን. 16ን ተመልከት።]
4. ራእይ 7:9 ላይ ተጠቅሶ የሚገኘው ‘በዙፋኑና በበጉ ፊት መቆም’ ሰማያዊ ቦታን የሚያመለክት ነው። [rs ገጽ 168 አን. 1]
5. በሃብታችን ማለትም በጊዜያችን፣ በተሰጥኦዋችን፣ በጉልበታችንና በቁሳዊ ንብረቶቻችን በልግስና ‘ይሖዋን ማክበራችን’ ከይሖዋ ዘንድ የተትረፈረፈ መንፈሳዊ በረከት ያስገኝልናል። (ምሳሌ 3:9, 10) [w00 1/15 ገጽ 25 አን. 1]
6. ኢሳይያስ 28:21 ላይ በትንቢት የተነገረው በዘመናችን የሚፈጸመው ‘እንግዳ ሥራና ያልታወቀ አድራጎት’ ብሔራት በአርማጌዶን የሚደርስባቸውን ጥፋት ያመለክታል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ ip-1 ገጽ 295 አን. 16ን፤ ገጽ 301 አን. 28ን ተመልከት።]
7. ማቴዎስ 24:38, 39 እንደሚያሳየው በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከሌሎች የዕለት ተዕለት የኑሮ ጉዳዮች በተጨማሪ ከልክ በላይ በመብልና መጠጥ መጠመዳቸው ለጥፋት ውኃ ዳርጓቸዋል። [w00 2/15 ገጽ 6 አን. 6]
8. ይሖዋ ራስ ወዳድነት በሌለበት መንገድ በትሕትና የሚያገለግሉት አገልጋዮቹ የሚያቀርቡትን ልመና ሁሉ ይፈጽምላቸዋል። [w00 3/1 ገጽ 4 አን. 3]
9. ኢሳይያስ 60:3 ላይ የተጠቀሱት “አሕዛብ” አምላክ ወደሚፈነጥቀው ብርሃን ተስበው የመጡ በተናጠል ያሉ ፖለቲካዊ ብሔራት ናቸው። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w00 1/1 ገጽ 12 አን. 4ን ተመልከት።]
10. ይሖዋ ኤርምያስን ከመወለዱ በፊት ‘የቀደሰው’ የኤርምያስን ዘላለማዊ ዕጣ አስቀድሞ በመወሰን ነው። (ኤር. 1:5) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 4/1 ገጽ 10 አን. 2ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ላሉት ጥያቄዎች መልስ ስጥ:-
11. መክብብ 11:1 ላይ የሚገኘው ‘እንጀራን መጣል’ የሚለው አባባል ትርጉም ምንድን ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w87 9/15 ገጽ 25 አን. 11ን ተመልከት።]
12. ኢሳይያስ 6:8 ላይ ይሖዋ ‘እኛ’ ብሎ ሲናገር ከእሱ ጋር ያለው ማን ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ ip-1 ገጽ 94-5 አን. 13ን ተመልከት።]
13. በኢሳይያስ 9:2 ፍጻሜ መሠረት በገሊላ “ታላቅ [NW ] ብርሃን” የታየው እንዴት ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ ip-1 ገጽ 126 አን. 17ን ተመልከት።]
14. ባቢሎን በ539 ከዘአበ ከመውደቋና በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ ባድማ ከመሆኗ ጋር በተያያዘ በዘመናችን ምን ዓይነት ተመሳሳይ ሁኔታ መጥቀስ ይቻላል? (ኢሳ. 13:19, 20፤ 14:22, 23) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ ip-1 ገጽ 188 አን. 30-1ን ተመልከት።]
15. “ታማኝና ልባም ባሪያ” ኢሳይያስ 21:6 ላይ እንደተገለጸው “ጉበኛ” የሆነው እንዴት ነው? (ማቴ. 24:45) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ ip-1 ገጽ 221-3 አን. 11ን ተመልከት።]
16. ምሳሌ 31:10 የትዳር ጓደኛ ማግኘት ለሚፈልግ አንድ ወጣት ምን ጥበብ ያዘለ ምክር ይዟል? [w00 2/1 ገጽ 31 አን. 1]
17. ኢሳይያስ 43:9 ላይ ለአሕዛብ አማልክት የቀረበላቸው ግድድር ምንድን ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 2/1 ገጽ 16 አን. 3ን ተመልከት።]
18. የአምላክን መንግሥት ምሥራች የሚያውጁ ሰዎች እግሮቻቸው ‘ያማሩ’ የሆኑት በምን መንገድ ነው? (ኢሳ. 52:7) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w97 4/15 ገጽ 27 አን. 6ን ተመልከት።]
19. ልባችን እንዳያታልለን ምን ማድረግ አለብን? (ኤር. 17:9) [w00 3/1 ገጽ 30 አን. 4]
20. ‘በይሖዋ መንገድ የሚሄዱ’ ሰዎች ምን ማድረግ አለባቸው? (ኤር. 7:23) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w99 8/15 ገጽ 29 አን. 6ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር የሚያሟላውን ቃል (ቃላት) ወይም ሐረግ ስጥ:-
21. “የጠቢብ ልብ በስተ ቀኙ ነው” ሊባል የሚችለው አብዛኛውን ጊዜ “ቀኝ እጅ” _________________________ ስለሚያመለክት ነው። በመሆኑም የሰውዬው _________________________ መልካምና ተቀባይነት ያለው አካሄድ እንዲከተል እንደሚያነሳሳው ያሳያል። (መክ. 10:2፤ ማቴ. 25:33) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w87 9/15 ገጽ 25 አን. 8ን ተመልከት።]
22. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ከያዛቸው ጠቃሚ ትምህርቶች መካከል ለአምላካዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች _________________________፣ _________________________ እና _________________________ ይገኙበታል። [si ገጽ 117 አን. 16]
23. ኢሳይያስ 33:1 [NW ] ላይ የተጠቀሰው የይሁዳን ከተሞች የሚበዘብዘው _________________________ ሲሆን እሱም በ632 ከዘአበ ሽንፈት ደርሶበት ‘እንደ አንበጣ ለሚሰበስቡት’ _________________________ ነዋሪዎች ከፍተኛ ምርኮ ትቶ ሸሽቷል። (ኢሳ. 33:4) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ ip-1 ገጽ 343 አን. 4ን፤ ገጽ 345 አን. 6ን ተመልከት።]
24. ኢሳይያስ 54:1ን ከገላትያ 4:26, 27 ጋር በማወዳደር “መካን” የሆነችው ሴት “_________________________”ን እንደምትወክል፣ ‘ባል ያላት’ ሴት ደግሞ _________________________ እንደምታመለክት ያሳያል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 8/1 ገጽ 11 አን. 8ን ተመልከት።]
25. በሕዝብ ፊት አገልግሎታችንን በምናከናውንበት ወቅት ፌዝና ተቃውሞ ሲያጋጥመን እንዲህ ዓይነቱ ተቃውሞ የሚሰነዘረው _________________________ ላይ ሳይሆን ይዘነው የሄድነው መልእክት ምንጭ በሆነው _________________________ ላይ እንደሆነ ማስታወስ ይኖርብናል። (2 ቆሮ. 4:1, 7) [w00 1/15 ገጽ 21 አን. 2]
ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ትክክለኛውን መልስ ምረጥ:-
26. ጳውሎስ የኢየሱስን ሰማያዊ ክብር በራእይ ስለመመልከቱ በጻፈበት ጊዜ እንደ “ጭንጋፍ” ለምሆን ብሎ ስለ ራሱ ሲናገር (በቅርቡ በመንፈስ መወለዱን፤ ቀደም ሲል የአሕዛብ ሐዋርያ ሆኖ መመረጡን፤ ጊዜው ከመድረሱ በፊት ተወልዶ ወይም ትንሣኤ አግኝቶ መንፈሳዊ ሕይወት ያገኘ ያህል መሆኑን) መግለጹ ነበር። (1 ቆሮ. 9:1፤ 15:8) [w00 1/15 ገጽ 29 አን. 6]
27. “የዘላለም አባት” የሚለው የማዕረግ ስም መሲሐዊው ንጉሥ ለሰው ልጆች (መንፈሳዊ ብርታት፣ በሰማይ ላይ የማይሞት ሕይወት፣ በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ) የመስጠት ኃይልና ሥልጣን እንዳለው ያመለክታል። (ኢሳ. 9:6፤ ዮሐ. 11:25, 26) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ ip-1 ገጽ 131 አን. 26ን ተመልከት።]
28. በኢሳይያስ 66:7 ዘመናዊ ፍጻሜ መሠረት የተወለደው “ወንድ ልጅ” (ኢየሱስ ክርስቶስን፤ መሲሐዊውን መንግሥት፤ በ1919 የተገኘውን አዲስ መንፈሳዊ ብሔር) ያመለክታል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 1/1 ገጽ 11 አን. 3ን ተመልከት።]
29. ማቴዎስ 10:28ን በጥንቃቄ ስናነብብ ገሃነመ እሳት (እየሰሙ የሚሰቃዩበት ቦታ እንደሆነ፣ ዘላለማዊ ጥፋትን እንደሚያመለክት፣ ከአምላክ መራቅን እንደሚያሳይ) መረዳት እንችላለን። [rs ገጽ 174 አን. 1]
30. በዘመናዊው ፍጻሜ መሠረት ኤርምያስ 7:28 ላይ የተነገረው ‘የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማው ሕዝብ’ (ታላቂቱ ባቢሎንን፣ ሕዝበ ክርስትናን፣ ሰባተኛውን የዓለም ኃይል) ያመለክታል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w88 4/1 ገጽ 18 አን. 10ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያሉትን ጥቅሶች ከታች ካሉት ሐሳቦች ጋር አዛምድ:-
ምሳሌ 24:16፤ መክ. 3:11፤ ኢሳ. 40:8፤ ሮሜ 10:15፤ 1 ጴጥ. 4:6
31. ጊዜው ሲደርስ እያንዳንዱ የአምላክ ሥራ በዓላማው ውስጥ የሚኖረው ትክክለኛ ቦታ ይታወቃል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w87 9/15 ገጽ 24 አን. 8ን ተመልከት።]
32. በመንፈሳዊ ሙታን ለሆኑ ሰዎች ምሥራቹ መሰበኩ ንስሐ እንዲገቡ አጋጣሚ ይሰጣቸዋል። [rs ገጽ 164 አን. 2]
33. በሕይወት የሚያጋጥሙ እንቅፋቶችን ማስወገድ ባይቻልም እንኳ አምላካዊ የሆነ ግለሰብ መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ከመጣጣር ወደኋላ አይልም። [w00 2/1 ገጽ 4 አን. 4]
34. የአምላክ ቃል ወይም የተገለጠው ዓላማው ሊሻር ወይም እንዳይፈጸም ሊታገድ አይችልም። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ ip-1 ገጽ 401-2 አን. 10ን ተመልከት።]
35. የኢየሱስ ሐዋርያት የኢሳይያስን ትንቢት በአገልግሎታቸው ተግባራዊ በማድረግ በጥሩ ሁኔታ ተጠቅመውበታል። [si ገጽ 123 አን. 37]