ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሚያዝያ እና ግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት ፍላጎት ያሳየ ሰው ስታገኙ የመጽሔት ደንበኛችሁ አድርጉት። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አበርክቱለት። ሰኔ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራው እውቀት። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ጉባኤው ያለውን ሌላ ተስማሚ የሆነ ብሮሹር ማበርከት ይቻላል። ሐምሌ፦ ቀጥሎ ካሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ”፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው የሰብሳቢ የበላይ ተመልካቾችንና የጸሐፊዎችን ወቅታዊ አድራሻና ስልክ ቁጥር ማግኘቱ አስፈላጊ ነው። የአድራሻ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የሰብሳቢ የበላይ ተመልካች/የጸሐፊ የአድራሻ ለውጥ ማሳወቂያ ቅጽ (S-29) በፍጥነት ሞልቶና ፈርሞ ለቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አለበት።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205-AM) እና የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205b-AM) በበቂ መጠን ሊኖራቸው ይገባል። እነዚህ ቅጾች እንዲላኩላችሁ በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) መጠየቅ ይቻላል። ቢያንስ ለአንድ ዓመት የሚበቃ ያህል ይኑራችሁ። የዘወትር አቅኚነት ማመልከቻ ቅጾች ሙሉ በሙሉ መሞላታቸውን ለማየት በደንብ ተመልከቷቸው። አመልካቾች የተጠመቁበትን ትክክለኛ ቀን ማስታወስ ካልቻሉ ቀኑን መገመትና መዝግበው መያዝ አለባቸው።
◼ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ ከተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ለማስተማሪያ ንግግር ወደ አማርኛ የተተረጎሙትን ክፍሎች በሚከተሉት የመንግሥት አገልግሎታችን እትሞች ላይ ማግኘት ትችላላችሁ:-
ኢሳይያስ . ነሐሴ 1995
ኤርምያስ . ታኅሣሥ 1995
ሰቆቃወ ኤርምያስ፣
ሕዝቅኤል . መጋቢት 1996
ዳንኤል . ነሐሴ 1996
ሆሴዕ . ጥቅምት 1996
ኢዩኤል፣ አሞፅ፣ አብድዩ፣
ዮናስ፣ ሚክያስ . ኅዳር 1996
ናሆም፣ ዕንባቆም፣
ሶፎንያስ፣ ሐጌ . ታኅሣሥ 1996
ዘካርያስ፣ ሚልክያስ . የካቲት 1997
◼ መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? የተባለው መጽሐፍ ተጠንቶ ካለቀ በኋላ ከሚያዝያ 29, 2002 ጀምሮ እስከ ሰኔ 9, 2003 ድረስ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ የሚጠናው የኢሳይያስ ትንቢት —ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን የተባለው መጽሐፍ የመጀመሪያው ጥራዝ ይሆናል። የጥናቱን ጠቅላላ ፕሮግራም በግንቦት የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ማግኘት ትችላላችሁ። የመጀመሪያዎቹን ሁለት ሳምንታት የጥናት ፕሮግራም በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።
◼ እንደገና ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው (አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ)