የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/02 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሚያዝያ 8 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 15 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 22 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 29 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 6 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 4/02 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሚያዝያ 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 26 (56)

13 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጉባኤውን የመጋቢት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት ከልስ። በአንዳንድ መልካም ጎኖች ላይ ሐሳብ ስጥ፤ እንዲሁም አዘውታሪነትን አበረታታ። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሁሉም ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን በልዩ የሕዝብ ንግግር ላይ እንዲገኙ እንዲጋብዙ አበረታታ። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች በመጠቀም መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት የተለያዩ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች “የራሴ ሃይማኖት አለኝ” ለሚለው ውይይት ለማስቆም የሚሰነዘር ሐሳብ ምን ብሎ መመለስ እንደሚቻል የሚያሳዩ ይሁኑ።​—⁠ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 18-​19 ተመልከት።

12 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት፤ ወይም “እስራትና ሞት እያለም ቢሆን ቤተሰቤ ለአምላክ ያሳየው ፍቅር” በሚለው በመስከረም 1, 1985 መጠበቂያ ግንብ (እንግሊዝኛ) ገጽ 10-15 ላይ በሚገኘው ርዕስ ተመስርቶ የሚቀርብ ንግግር።

20 ደቂቃ፦ “‘ለሰው ሁሉ መልካም አድርጉ።’” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከጥያቄና መልስ ውይይቱ በኋላ አገልግሎታቸውን በማስፋት ላይ ያሉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ለአንድ ወይም ለሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ።

መዝሙር 68 (157) የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 88 (200)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።

15 ደቂቃ፦ አቅኚዎች ሌሎችን መርዳታቸውን ይቀጥላሉ። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካች፣ ከአንድ አቅኚና ከአንድ አስፋፊ ጋር በውይይት ያቀርበዋል። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በመስከረም 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን በገጽ 8 ላይ ያለውን አቅኚዎች ሌሎችን የሚረዱበትን ፕሮግራም ይከልሳል። ከዚያም እያንዳንዳቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች በዝግጅቱ ውስጥ የእሱ ወይም የእሷ ሚና ምን እንደሆነና ይህ ዝግጅት የታቀደለትን ዓላማ እያከናወነ ያለው እንዴት እንደሆነ ይወያያል። ዝግጅቱ ግቡን እንዲመታ ለማስቻል ምን ተደርጓል? የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ሁሉንም አስፋፊዎች በአገልግሎት እርዳታ እንዲደረግላቸው የሚፈልጉ ከሆነ እንዲነግሩት ይጋብዛል። እስካሁን እርዳታ ሲደረግላቸው የነበሩም በሌላ የአገልግሎት ዘርፍ ተጨማሪ እርዳታ ሊደረግላቸው ይችላል።

20 ደቂቃ፦ “የሙሉ ጊዜ አገልግሎት የሚያስገኘው ደስታ” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ወጣቶች ትምህርት ቤቶች ለእረፍት በሚዘጉባቸው ወራት በረዳት አቅኚነት ለማገልገል ማመልከቻ እንዲያስገቡ አበረታታ።

መዝሙር 43 (98) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 57 (136)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ግንቦት 6 የሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ሁሉም የወጣቶች ጥያቄ ​—⁠እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው? የተባለውን የቪዲዮ ፊልም በማየት እንዲዘጋጁ አበረታታ። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም አንድ የጉባኤ አገልጋይ መጠበቂያ ግንብ አንዲት እህት ደግሞ ንቁ! እንዴት ማበርከት እንደሚቻል በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ የሚያነጋግሩት ሰው ያለውን ፍላጎት ለመቀስቀስ የተጠቀሙባቸውን አንድ ወይም ሁለት የመግቢያ ዓረፍተ ነገሮች በድጋሚ ጥቀስ።

15 ደቂቃ፦ ሰዓት አክባሪዎች ሁኑ! በንግግር የሚቀርብ። ከአምልኮታችንና ከአገልግሎታችን ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎች ‘የተወሰነ ጊዜ’ የሚጠይቁ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው። (መክ. 3:1) ከቲኦክራሲያዊ ዝግጅቶች ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ መሆን እንፈልጋለን። የጉባኤ ስብሰባዎችና የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች ልክ በተወሰነላቸው ሰዓት መጀመር አለባቸው። ይሖዋ ተግባሮቹን ለመፈጸም በፍጹም ዘግይቶ አያውቅም። (ዕን. 2:3) በዚህ ረገድ ማሻሻል ያስፈልገን ይሆን? አልፎ አልፎ አንዳንዶች ከአቅማቸው በላይ በሆነ ሁኔታ ሊያረፍዱ ይችላሉ። ይሁን እንጂ በሚገባ የተደራጀን ከሆንን ሁልጊዜ የስብሰባው የመክፈቻ መዝሙርና ጸሎት ከተደረገ በኋላ ወይም በመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ላይ ወንድሞችና እህቶች ከተመደቡ በኋላ አርፍደን የመድረስ ልማድ አይኖረንም። ለሁሉም መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ሰዓት አክባሪ እንድንሆን የሚያስችሉንን ጥሩ ልማዶች ማዳበር የሚቻልባቸውን ተግባራዊ መንገዶች ተወያዩ።​—⁠12-111 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 29ን ተመልከት።

20 ደቂቃ፦ “በመንፈሳዊ ጠንካራ የሆነ ቤተሰብ መገንባት​—⁠እንዴት?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በርዕሱ ውስጥ ባለው ሐሳብ ከተወያያችሁ በኋላ ከየካቲት 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 10-​12 ተግባራዊ ተሞክሮዎችን ተናገር።

መዝሙር 85 (191) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 70 (162)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በልዩ የአገልግሎት ክልል የመሸፈን ዘመቻ እስካሁን ድረስ ምን እንደተከናወነ ከልስና አንድ ወይም ሁለት ተሞክሮዎችን ጨምረህ አቅርብ። አስፋፊዎች የሚያዝያ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በጤና እክል ወይም በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት ያገለገሉት ሰዓት ዝቅተኛ ቢሆንም እንኳን የአገልግሎት እንቅስቃሴያቸውን ሪፖርት ከማድረግ ወደኋላ ማለት እንደሌለባቸው እባክህ ጨምረህ ተናገር። እንዲሁም ሁሉም በሚቀጥለው ሳምንት ለሚደረገው ውይይት ትምህርት ቤት የተባለውን ብሮሹር ይዘው እንዲመጡ አሳስባቸው።

15 ደቂቃ፦ “የመንግሥቱ ስብከት ሥራ ሕይወት አድን ነው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አድማጮች በጥቅሶቹ ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።

20 ደቂቃ፦ የማመራመር መጽሐፍን በመጠቀም የሚደረግ ምርምር። ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በአገልግሎት ላይ አብዛኛውን ጊዜ በማመራመር መጽሐፍ ውስጥ “ዋና ዋና አርዕስት” (ገጽ 5-6) በሚለው ዝርዝር ውስጥ በሌሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎች ይነሳሉ። በመጽሐፉ ላይ ያለው “ማውጫ” (ከገጽ 439-​45) ለምናምንባቸው ነገሮች ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ ለመፈለግ በጣም ጠቃሚ ነው። አድማጮች ቀጥሎ ለቀረቡት ጥያቄዎች በሰያፍ የተጻፉትን ቃላት በማውጫው ላይ በመፈለግ ለጥያቄዎቹ መልስ በማግኘት እንዲሳተፉ ጋብዝ። ክርስቲያኖች ስለ ብሔራዊ መዝሙሮች እና ባንዲራዎች ያላቸው አመለካከት ምንድን ነው? አምላክ የተፈጥሮ አደጋዎችን የፈቀደው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍቺ ያለውን አመለካከት እንዴት ማስረዳት ትችላለህ? እህቶች ራስን መሸፈን የሚያስፈልጋቸው ለምንና መቼ ነው? የእናቶች ቀን አመጣጡ እንዴት ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 144, 000 ትርጉሙ ቃል በቃል እንደሆነ እንዴት እናውቃለን? የሀብታሙ ሰው እና አልዓዛር ምሳሌ ምን ያመለክታል? ሁሉም የማመራመር መጽሐፍን በአገልግሎት እንዲጠቀሙበት አበረታታ።

መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 6 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 73 (166)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “ከመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ጥቅም ማግኘታችሁን ቀጥሉ” የሚለውን ተወያዩበት።

15 ደቂቃ፦ “ትምህርት ቤትና የሕይወታችን ዓላማ።” ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች በተባለው ብሮሹር በገጽ 4-7 እና 24 ላይ የሚደረግ ውይይት። ሁሉም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱትን እምነቶቻችንን ለሰዎች ሲናገሩ በጥበብና በአክብሮት መሆን እንዳለበት አሳስባቸው። ልጆቻችን የሚያሳዩት ምሳሌ የሚሆን አክብሮት የተሞላበት ባሕርይ ለይሖዋ ስም ውዳሴ እንዴት ሊያመጣ እንደሚችል የሚያሳዩ አንድ ወይም ሁለት ሐሳቦችን ተናገር። እንዲሁም ወላጆች ልጆቻቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከጨረሱ በኋላ ምን ዓይነት ተጨማሪ ትምህርት ወይም ሥልጠና ማግኘት እንዳለባቸው መወሰን እንደሚኖርባቸውና የሕይወታችንን ዓላማ በግልጽ መረዳታቸው ጥበብ የታከለባቸው ውሳኔዎችን በማድረግ ረገድ እንዴት ሊረዳቸው እንደሚችል ጥቀስ።

20 ደቂቃ፦ “ልባዊ ምስጋና!” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ አንድን ስትወያዩ አድማጮች የወጣቶች ጥያቄ​—⁠እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው? ስለተባለው ቪዲዮ አንዳንድ አጫጭር አስተያየቶችን እንዲናገሩ አድርግ። ከዚያም በቀጥታ ከአንቀጽ 2-7 በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ መወያየት ጀምር። በሰኔ ወር መላው የወንድማማች ማኅበር የተሰኘውን ቪዲዮ እንከልሳለን።

መዝሙር 27 (57) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ