ከመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ጥቅም ማግኘታችሁን ቀጥሉ
መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ከአሁን በኋላ በኮንትራት ስለማናገኝ እኛም ሆንን የምንመሰክርላቸው ሰዎች አንዱም እትም እንዳያልፈን ጥረት ማድረግ ያስፈልገናል።
የግል ቅጂዎች፦ በኮንትራት ይደርሳችሁ የነበረው መጽሔት መምጣቱን ሲያቆም በጉባኤያችሁ በኩል ታገኙ የነበረውን የመጽሔት ትእዛዝ ከፍ አድርጉ። ወላጆች እያንዳንዱ የቤተሰቡ አባል የራሱ ቅጂ እንዲኖረው ለቤተሰቡ የሚበቃ መጽሔት ማዘዝ አለባቸው። የግል ቅጂያችሁን በአገልግሎት ላይ ሳታውቁ እንዳታበረክቱት ስማችሁን ጻፉበት። መጽሔቶች ጉባኤያችሁ ሲደርሱ ኃላፊነት የተሰጣቸው ወንድሞች እያንዳንዱን እትም ወዲያውኑ አስፋፊዎች እንዲወስዱ ማድረግ አለባቸው።
የመጽሔት ደንበኞች፦ አስፋፊዎች እያንዳንዱን እትም ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎችን የመጽሔት ደንበኛ ለማድረግ መጣር ይኖርባቸዋል። ለእነዚህ ሰዎች መጽሔቶቹን ሄደን መስጠታችን ፍላጎታቸውን ለማሳደግና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምሩ ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ይከፍታል።—የጥቅምት 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 12 ተመልከት
የተለየ ዝግጅት፦ አንድ ሰው እውነተኛ ፍላጎት ቢያሳይና የሚኖረው ግን ለማንም ባልተመደበ የአገልግሎት ክልል ውስጥ ቢሆን ይህ ሰው መጽሔቶችን በኮንትራት እንዲያገኝ የተለየ ዝግጅት ማድረግ ይቻላል። በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ የሚኖር ሰው እውነተኛ ፍላጎት ቢኖረውና የመጽሔት ደንበኛ ማድረግ የማይቻል ቢሆን ጉዳዩን ከጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ ጋር ተወያዩበት። እነሱ ከተስማሙበት ፍላጎት ያሳየውን ሰው ኮንትራት ማስገባት ይቻላል። ለዚህ ዓላማ መደበኛውን የኮንትራት ማስገቢያ ቅጽ (M-1-AM and M-101-AM) መጠቀም ይቻል ይሆናል።
ይሖዋ በመጠበቂያ ግንብ እና በንቁ! መጽሔቶች አማካኝነት መንግሥቱን ለማስታወቅ የምናደርገውን ጥረት መባረኩን እንደሚቀጥል እርግጠኞች መሆን እንችላለን።