የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/02 ገጽ 7
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 4/02 ገጽ 7

ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

◼ በቅርብ ወራት ቀጥሎ ባሉ ቦታዎች ተጨማሪ አዳዲስ የመንግሥት አዳራሾች ተጠናቀዋል:- አዲስ አበባ ፈረንሳይ፣ አላወርቄ (ከአዋሳ በስተደቡብ)፣ አኖሌ (ከአዋሳ በስተደቡብ)፣ አየለ (ፊንጫ አቅራቢያ)፣ ባህር ዳር፣ ባኮ፣ በለስቶ (አለታ ወንዶ አቅራቢያ)፣ ደብረ ብርሃን፣ ጋምቤላ፣ መቀሌ፣ መጋራ (ይርጋለም አቅራቢያ)፣ ሲባጫሮ (ጊምቢ አቅራቢያ)፣ ቴፒ፣ ወንዶ ገነት፣ ወንዶ ጢቃ (አዋሳ አቅራቢያ)።

◼ “የአምላክ ቃል አስተማሪዎች” በሚል ጭብጥ ያደረግናቸው ስምንት የአውራጃ ስብሰባዎች ሲጠናቀቁ በድምሩ 11, 399 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የተሰብሳቢ ቁጥርና 240 የሚያህሉ ተጠማቂዎች ነበሯቸው። ይህ ከአምናው 10 በመቶ የሚበልጥ አዲስ ከፍተኛ የተሰብሳቢ ቁጥር ሲሆን ለመለኮታዊ ትምህርት ፍላጎት ያላቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ የሚያሳይ ነው።

◼ በአዲስ አበባ በኮተቤ አካባቢ አዲስ የቅርንጫፍ ቢሮ ሕንጻ ለመገንባት በመንቀሳቀስ ላይ መሆናችንን ስንገልጽላችሁ ደስ ይለናል። ይህ የመንግሥት አገልግሎታችን ሲደርሳችሁ የቁፋሮ ሥራው ተጀምሮ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን። ግንባታው በግምት ወደ ሁለት ዓመት ገደማ የሚፈጅ ሲሆን ፕሮጀክቱን የሚመለከቱ ተጨማሪ ዜናዎች በጊዜ ሂደት ይገለጻሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ