የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ሰኔ 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 28 (58)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሰኔ 24 በሚጀምር ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ መላው የወንድማማች ማኅበር በተባለው ቪዲዮ ላይ ውይይት ስለሚደረግ ሁሉም አስቀድመው ፊልሙን እንዲመለከቱ አበረታታ። በገጽ 4 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም መጽሔት ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ‘ለሃይማኖት ግድ የለኝም’ ለሚሉ ሰዎች በተለያየ መንገድ መልስ ሲሰጥ የሚያሳዩ ይሁኑ።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 17ን ተመልከት።
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሳጥን። ሁሉንም አንቀጾችና ሐሳባቸው ያልተጠቀሱትን ጥቅሶች አንብብ። ከዚያም በመጋቢት 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከወጣው የጥያቄ ሳጥን ሌሎች ሐሳቦችን ጎላ አድርገህ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “በበረከት መዝራት በረከት ያስገኛል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። ከታኅሣሥ 1, 1992 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 15-16 ከአንቀጽ 14-17 ተጨማሪ ሐሳቦችን አቅርብ።
መዝሙር 98 (220) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 57 (136)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ ለግል ጥናት ቅድሚያ ስጡ። በጥቅምት 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-21 ከአንቀጽ 1-10 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። መደምደሚያህ ላይ የክለሳ ጥያቄ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “ባላችሁ የምትረኩ ሁኑ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ጥቅሶቹን እያነበብክና እያብራራህ ምክሩ የተመሠረተበትን ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረት ጎላ አድርገህ ግለጽ።
መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47 (112)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አብረው የሚያገለግሉ አንድ ባልና ሚስት በገጽ 4 ላይ ያሉትን አቀራረቦች ተጠቅመው መጽሔቶቻችንን ሲያበረክቱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ ያቀርባሉ። እህት መጠበቂያ ግንብ ስታበረክት ወንድም ደግሞ ንቁ! መጽሔት ያበረክታል። በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውንና በሐምሌና በነሐሴ የሚበረከቱ የተመረጡ ብሮሹሮችን ለማበርከት የሚያስችል መግቢያ ተዘጋጅተው እንዲመጡ ሁሉንም አበረታታ።—በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ያለውን “ሌሎች ጽሑፎች” የሚለውን ሳጥን ተመልከት።
12 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
25 ደቂቃ፦ “ለመላው የወንድማማች ማኅበራችን ፍቅር የምናሳይበት ምክንያት።” የመግቢያ ሐሳብ ሳትናገር የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም መላው የወንድማማች ማኅበር በተባለው ቪዲዮ ላይ ከአድማጮች ጋር ውይይት አድርግ።
መዝሙር 41 (89) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 25 (53)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሰኔ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። አስፋፊዎች የአገልግሎት ሰዓታቸው ዝቅተኛ እንደሆነ ቢሰማቸውም እንኳ ሪፖርታቸውን በዚያው ወር መስጠት አለባቸው እንጂ ወደሚቀጥለው ወር ማስተላለፍ አይኖርባቸውም። ይህ በወሩ ውስጥ ስለተደረገው አጠቃላይ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ትክክለኛ አኃዝ እንዲኖረን ያስችለናል። በተጨማሪም ሁሉም መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት በመስጠት ያሳለፉትን ሰዓት (ጥቂት ደቂቃም ቢሆን)፣ ያበረከቷቸውን ጽሑፎችና ያደረጉትን ተመላልሶ መጠየቆች የሚመዘግቡበት ማስታወሻ ደብተር ወይም የሪፖርት ቅጽ እንዲይዙ አበረታታ። ይህ ሁሉ በትክክል ተደምሮ በወሩ መጨረሻ ላይ መሰጠት አለበት። በሐምሌና በነሐሴ የትኞቹን ብሮሹሮች እንደምናበረክትና ምን ዓይነት አቀራረብ እንደምንጠቀም ከአድማጮች ጋር ተወያይ። አድማጮች ከዚህ ቀደም ከወጡ የመንግሥት አገልግሎታችን እትሞች ላይ ያገኟቸውን አቀራረቦች እንዲናገሩ ጋብዝ። በተለይ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር እንዲጠቀሙ አበረታታ። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲነበብ የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ! በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ይህ ብሮሹር ልጆችንና አነስተኛ የትምህርት ደረጃ ወይም የማንበብ ችሎታ ያላቸውን ሌሎች ሰዎች ስለ ይሖዋ እንዲማሩ በመርዳት ረገድ ጠቃሚ የማስተማሪያ መሣሪያ እንዲሆን ያስቻሉትን አንዳንድ ገጽታዎች ጥቀስ። ቀላልና አሳማኝ ከሆኑት ማብራሪያዎቹ ውስጥ አንዳንዶቹን ተናገር። (ትምህርት 2, 8ና 12ን ተመልከት።) ስዕሎቹን ተጠቅሞ የተማሪውን ልብ እንዴት መንካት እንደሚቻል ተናገር። ብሮሹሩን ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም የሚቻልባቸውን መንገዶች ተናገር። ወላጆች ይህን ብሮሹር ለልጆቻቸው ማስጠናት ይኖርባቸዋል። አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ሁሉ በአገልግሎት ላይ እንዲያበረክቱት ሁሉንም አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “ሌሎችን የመርዳት ልባዊ ፍላጎት አለህን?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ሁሉም የጉባኤው አባላት ሌሎችን የመርዳት ዝንባሌ እንዲኖራቸው አበረታታ።
መዝሙር 67 (156) እና የመደምደሚያ ጸሎት።