የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ነሐሴ 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
13 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት የተለያዩ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ‘አዘውትራችሁ የምትመጡት ለምንድን ነው?’ ለሚሉ ሰዎች በተለያየ መንገድ መልስ ሲሰጥ የሚያሳዩ ይሁኑ።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 20ን ተመልከት።
20 ደቂቃ:- “መንፈሳዊ ግብ አውጡ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 5ን ስትወያዩ የዘወትር አቅኚነትንና የቤቴል አገልግሎትን በተመለከተ አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 114-16 ላይ ቀስቃሽ የሆኑ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
12 ደቂቃ:- ከጉባኤው የተገኙ ተሞክሮዎች። የጉባኤው አባላት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ለማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት በመጠቀም ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ያስጀመሩ አሉ? ካሉ እንዴት እንዳስጀመሩ ተናገር ወይም አንድ ወይም ሁለቱን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። በኅዳር 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 ላይ ያለውን “ትራክቱን ለማሰራጨት የሚያስችሉ አጋጣሚዎች” የሚለውን ሣጥን ከልስ።
መዝሙር 50 (123) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 28 (58)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። እንዲሁም የአገልግሎት ክልል ለመሸፈን በተደረገ ልዩ ዘመቻ የተገኙ አንዳንድ አበረታች ውጤቶችን ጨምረህ አቅርብ።
15 ደቂቃ:- ከእኛ ጋር መወያየት የማይፈልጉት ለምንድን ነው? ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይትና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። ስለ እምነታቸው ከእኛ ጋር ለመወያየት የማይፈልጉ ሰዎች በአገልግሎታችን ላይ በተደጋጋሚ ያጋጥሙናል። ይህም የመንግሥቱን መልእክት እንዳንነግራቸው እንቅፋት ይሆንብናል። አንድ ሰው ከእኛ ጋር መነጋገር የማይፈልግበትን ምክንያት ማወቃችን ሰውየው ሐሳቡን እንዲገልጽ የሚገፋፋ አቀራረብ እንድናዘጋጅ ሊረዳን ይችላል። ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የመሰሉ ሰዎች ሲያጋጥሙን አቀራረባችንን እንዴት ማስተካከል እንደምንችል ተወያዩ። (1) ለሃይማኖት (ለራሳቸውም ሃይማኖት ቢሆን) ፈጽሞ ግድ የሌላቸው። (2) ወላጆቻቸው ወይም የቀድሞ አያቶቻቸው የሚያከናውኗቸውን ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች የሚወዱ። (3) ለእምነቶቻቸው በቂ ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ ማቅረብ ስለማይችሉ ስለ እምነታቸው ለመነጋገር የሚያፍሩ። (4) ተቃዋሚዎች ስለ እኛ በሚሰነዝሩት የተሳሳተ አስተያየት የተነሳ በሩቁ የሚጠሉን። ይህ ዝርዝር ከጉባኤያችሁ የአገልግሎት ክልል ጋር የሚስማማ እንዲሆን ለማድረግ በተደጋጋሚ በሚያጋጥሙ አስተያየቶች ላይ በማተኮር እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያዎች ልታደርግበት ትችላለህ። የአንድን ሰው ትኩረት ስቦ ቅዱስ ጽሑፋዊ ውይይት እንዴት ማድረግ እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ አጭር ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
18 ደቂቃ:- “የቅርብ ዘመድ ሲወገድ ክርስቲያናዊ ታማኝነት አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። (አንቀጽ 1-8) አንድ ብቃት ያለው ሽማግሌ የተዘጋጁትን ጥያቄዎች በመጠቀም ያቀርበዋል። ጥሩ ችሎታ ያለው አንድ ወንድም ድምፁን ከፍ አድርጎ እያንዳንዱን አንቀጽ እንዲያነብልህ አድርግ።
መዝሙር 57 (136) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 92 (209)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን አቀራረቦች በመጠቀም አንድ የዘወትር ወይም ረዳት አቅኚ መጠበቂያ ግንብ ሲያበረክትና አንድ የጉባኤ አስፋፊ ንቁ! ሲያበረክት የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ሁሉም አስፋፊዎች ምሥክርነቱን በሚሰጡበት ጊዜ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንዲያነብቡ አበረታታ።
17 ደቂቃ:- “ምሥራቹን በሚስብ መንገድ ማቅረብ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ስትደመድም አስፋፊዎች ከቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ጥናት 16ን እንዲከልሱ አበረታታቸው።
18 ደቂቃ:- “የቅርብ ዘመድ ሲወገድ ክርስቲያናዊ ታማኝነት አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። (አንቀጽ 9-14) አንድ ብቃት ያለው ሽማግሌ የተዘጋጁትን ጥያቄዎች በመጠቀም ያቀርበዋል። ጥሩ ችሎታ ያለው አንድ ወንድም ድምፁን ከፍ አድርጎ እያንዳንዱን አንቀጽ እንዲያነብልህ አድርግ።
መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 35 (79)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የነሐሴ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በግንቦት 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 25 ላይ “ለልጆቻችሁ አንብቡላቸው” የሚለውን ርዕስ በአጭሩ አቅርብ።
15 ደቂቃ:- ለአገልግሎት ከመውጣታችሁ በፊት ተዘጋጁ። በውይይትና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። ጥሩ እቅድ ማውጣት በአገልግሎት ውጤታማ እንድንሆን ያስችለናል። ስለዚህ በቅድሚያ:- (1) የሚያስፈልጉህን ጽሑፎች አዘጋጅ። (2) ከቤት ወደ ቤት የመመዝገቢያ በቂ ቅጽና ብዕር ወይም እርሳስ ያዝ። (3) መጓጓዣ የሚያስፈልግህ ከሆነ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርግ። (4) ስለምታደርጋቸው ተመላልሶ መጠየቆች አስብ። (5) የምትናገረውን አዘጋጅ። የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባውን የምትመራው አንተ ከሆንክ በቂ የአገልግሎት ክልሎች አዘጋጅ። በመስከረም ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! የተባለውን መጽሐፍ በአገልግሎት ላይ ማበርከት የሚቻልባቸውን አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦች ከአድማጮች ጋር ተወያይ። አንዱን አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። በሠርቶ ማሳያው ላይ ጥቅስ እንዲነበብ አድርግ።—በየካቲት 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 12 ላይ ያሉትን ሐሳቦች ተመልከት።
20 ደቂቃ:- “በአለባበስና በፀጉር አያያዝ ልከኛ መሆን።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንድ ሽማግሌ የሚቀርብ ሲሆን በእያንዳንዱ አንቀጽ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ አንቀጹን ያነብበዋል። ሁሉም ለአለባበሳቸውና ለፀጉር አያያዛቸው ጠንቃቃ መሆን ያለባቸው ለምን እንደሆነ እንዲገነዘቡ እርዳቸው።
መዝሙር 59 (139) የመደምደሚያ ጸሎት።